how i got rid of acne scars naturally
ቡጉር እንዴት ይመጣል እንዴትስ ማጥፋት ይቻላል
ቆዳ ትልቁ የሰውነት አካል ክፍል (Organ) ሲሆን እጅግ በጣም ብዙ ጠቀሜታዎችም አሉት:: የቆዳ ህዋሶች (cells) ከውስጠኛው የቆዳ ክፍል (derms) ወደ ውጨኛው የቆዳ ክፍል (epidermis) በሚያደርጉት ጉዞ በየጊዜው ይቀየራሉ:: እነዚህ ህዋሳት በሚያረጁ ሰዓት ወደ ውጨኛው የቆዳ ክፍል ይቀርባሉ:: ከዚህ ላይ ከሌሎች ተመሳሳይ ህዋሳት ጋር በመሆን ጠንካራ የሆነ ቆዳን ከተለያዩ bacteria እና viruses የሚከላከል layer የፈጥራሉ::
ከ hair follicle ዉስጥ, ትንንሽ ወዝ (sebeum) አመንጭ እትዕኢ (glands) አሉ:: ወዝ ከ ቆዳ ህዋሳት ጋር በመሆን ወደ ውጨኛው የቆዳ ክፍል (epidermis) ይጉአዛል:: ነገርግን ብዙ ወዝ : የሞቱ የቆዳ ህዋሳት ወይም ቆሻሻ ከቆዳችን ላይ በሚኖርበት ሰዓት ጉዞውን ይረብሻል:: በዚህ ጊዜ የጉዞ መስመሩ ይዘጋል:: ባክቴሪያዎችም በዚህ ምቹ ሁኔታ ተሳታፊ ይሆናሉ:: ይህ መንስኤ acne vulgaris የተባለ ሁኔታ የፈጥራል:: acne vulgaris ብዙዉን ጊዜ የሚከሰት የቡግር አይነት ነው::
ቡግር ብዙን ጊዜ ጎረምሳ/ኮረዳ (teenagers) የሚታይ ቢሆንም በማንኛዉም የእድሜ ደረጃ ያሉትን ህፃናትም ላይ ሳይቀር ይታያል::
እናም ቡግርን ለማጥፋት ምን ማድረግ አለብን? እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት::
1. ፊትዎን በእጅዎ መነካካትያቁሙ!
o እጃችን ብዙ ስራዎችን የምንሰራበት እና በቀላሉ በባክቴሪያ የሚጠቃ የአካል ክፍል ነው::
እጅዎን በየጊዜው ይታጠቡ:: (እንዴት መታጠብ እንዳለበዎት ከዚህ በፊት በለጠፍነው ፎቶ ማየት ይችላሉ)
2. ፊትዎን በቀን ሁለቴ የታጠቡ
o ጧት እና ማታ ሞቅ ባለ ዉሃ በሳሙና ይታጠቡ::
3. የምተቀሙትን cosmotics በደንብ ይመልከቱ
•Cosmotics ብቻውን ቡግር ባያስከትልም ሲገዙ “oil-free” ወይም “noncomedogenic” የሚል የተፃፈባቸው ቢሆን ይመረጣል:: ከዚህ በተጨማሪ ለቆዳዎ የሚስማማውን የፋብሪካ ውጤት በደንብ ለየተው ይዎቁ::
ከላይ የተጠቀሱትን አድርገው አሁንም ችግሩ ካልተቀረፈ የሚከተለዉን ጥቆማ ይመልከቱ
4.. ጭንቀትን ያስዎግዱ
o አንዳንድ የጭንቀት ባህርያት ቆዳን ይጎዳሉ:: ለምሳሌ ፊትን መንካት ማሸት: የግል ንጽሕናን አለመጠበቅ: የተዛባ የአመጋገብ ስርዓት..
o በተጨማሪም ሰውነታችን በጭንቀት ጊዜ በሚካሄደው የchemical ዉህደት የቆዳችንን መልክ የመቀየር አቅም አለው:: ለምሳሌ:- ወዝ የማመንጨት ደረጃ ይጨምራል::
የሄን ሁሉ አድርገው አድርገው ለውጥ የለዉም? እንግዲያውስ የመጨረሻዉን መፍትሄ ይመልከቱ!
5. የጤና ባለሙያ ያማክሩ!
ማጋራት ደግ ነው!
sharing is caring!
ምንጭ: positivemed. com
@ ወይ ማወቅ ደጉ