YE USTAZ NURU TURKI METSEHAF TEMEREQE

 የኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ መጽሃፍ በዛሬው እለት በልዩ ዝግጅት ተመረቀ
የታተመው ሶስት ሺ መጽሃፍ በዛሬው ምረቃ ስነ-ስርአት ላይ ተሸጦ አለቀ

 

 

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በእምቢልታ አዳራሽ በየቲምነት አድጎ የቲሞችን ሲንከባከብ የነበረው በግፍ ታስሮ በቅርቡ ከኡማው ጋር የተቀላቀለው የኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ "የቲምነት" መፅሃፍ በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል:: 
የኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ሁለት እናቶች (የራሱ እናት እና የባለቤቱ እናት) በይፋ መፅሃፉን የመረቁ ሲሆን:: በርካታ የክብር እንግዶችና በቅርቡ የተፈቱት የሙስሊሙ ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በተገኙበት 3000 ብዛት ያለው የመጀመርያ እትሙ 400 ሰዎች ብቻ በተገኙበት በአስገራሚ ሁኔታ ሊያልቅ ችሏል:: 
ይህ መፅሃፍ በአይነቱ የመጀመርያ እንደሆነ ተገልፆ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ይህንን መ ፅሃፍ ከቂሊንጦ ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ሲዘዋወር አቋርጦት እንደነበረ ተናግሮ ቡሃላም በዝዋይ በአላህ ተዓምር ከተረፈበት የግድያ ሙከራ ቡሃላ ግን "እውነት ዛሬ ሞቼ ቢሆን ኖሮስ?ለሙስሊሙ ኡማ ያስቀመጥኩት ምን አለ?" ብሎ እራሱን በመጠየቅና በአዲስ መንፈስ መፅሃፉን በመጀመር ከእስር ለመፈታት 20 ቀናት ሲቀሩት መፅሃፉን እንደጨረሰው ተናግሯል:: 
በፕሮግራሙ ላይ ከኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ለአራት ሰዎች የምስጋና ስጦታና እስከዛሬ ለኡማው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል:: እነሱም ሃጂ መሃመድ አወል ረጃ ወንድም ዲኑ ዓሊ ኡስታዝ አ/ፈታህ ሙስጠፋ እና ወንድም ሃሺም ናቸው:: በማያያዝም በቅርቡ እጅግ ልዩ በሆነ ሁኔታ የአንድ አይናችን አፍሪካ ቲቪ ደጋፊ የሚሆን ተጨማሪ አንድ ሃገር በቀል ኢስላማዊ የዳዕዋ ቻናል ለአየር እንደሚበቃና ህዝቡም አለኝታውን እንዲያሳይ ተነግሯል::
ፕሮግራሙ በወንድም ዲኑ እና ሙሳ የተመራ ሲሆን በቀጣይ ሳምንታትም በዱባይ እና በሱዑዲ አረቢያ ከነዚሁ ወንድሞች ጋር የመፅሃፉ የምርቃት ፕሮግራም እንደሚዘጋጅ ተበስሯል:: 
እንግዲህ ዱባዮች እና ሳውዲዎች ይህንን በአይነቷ የመጀመርያና ታሪካዊ የሆነ መፅሃፍ ቀጣይ ስራዎችን ለማገዝና በኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ስር የሚገኙ የቲሞችን ለመታደግ ይህንን ፕሮግራም በሃገራችሁ ላይ ለመታደም ተዘጋጁ!
"የቲሞችን የተንከባከበ እኔና እሱ በጀነት ጎረቤት ነን" ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
@ musa muredin