Yemen's Houthi rebels fire missile towards Mecca

የመን ሁቲ አማጽያን ወደ መካ የላኩት ሚሳኤል ከሸፈ !
===================================

 

* ሚሳዬሉ ከመካ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት በመቃዎሚያ ከሽፏል 

* ከኢራንና ሊባኖስ በየመኑ ፕሬዘደንት ተወግዘዋል 
* የሳውዲ መከላከያ ተመሳሳይ ጥቃቶችን ለመከላከል ተዘጋጅቷል

የመን ሁቲ አማጽያን ከየመን የሁቲ አማጽያን ይዞታ ከሳአዳ Saada ወደ ቅዱስ መካ የላኩት ምድር ለምድር ተወንጫፊ እስከድ ሚሳኤል መክሸፉን የአረብ ህብረት ጦሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ። ከየመን በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ቅዱስ ከተማዋ መካ ያነጣጠረው የሚሳዬል ጥቃት ከመካ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ሲደርስ መክሸፉ ተነግሯል። ይህው ትናንት ከቀትር በኋላ በግምት 9 p.m በሳውዲ መከላከያ ሰራዊት የምድር ጦር መቃዎሚያ የከሸፈው ጥቃት ጉዳት አለማድረሱን ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ መግለጫ ያስረዳል ።

ካሳለፍነው አመት ጀምሮ በየመን የሚገኙትን አማጽያን ለማንበርከክ ሳውዲና ሳውዲ መራሽ አረብ ሀገራት የአየር ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ይታወቃል ። ይሁን እንጅ የህብረት ጥቃቱ አብዛኛው የመንን ተቆጣጥረው ያሉትን የሁቲ አማጽያን እና የቀድሞው መሪ የአሊ አብደላህ ሳላህን ደጋፊዎች መቆጣጠር አልቻላቸውም ። ሳውዲ መራሹ ጦር በአማጽያኑ ላይ ከበድ ያለ ኪሳራና ጥቃት ቢያደርስም አማጽያኑ ድንበር አሻግረው የሚልኳቸውን ሚሳኤሎች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አለመቻላቸው ይነገራል ።

ከድንበር ከተማዎች አልፈው ከመካ የቅርብ ርቀት በምትገኘው የጣይፍ ከተማ የቅርብ ርቀት ሚሳዬል ባስወነጨፉ በሳምንታት እድሜ ዛሬ መካን ኢላማን ማድረጋች የሰማነው መረጃ አነጋጋሪ መሆኑ አልቀረም ። አማጽያኑ ከቅዱስ ከተማዋ መካ የ65 ኪሎ ሜትር ርቀት ሚሳዬል መተኮሳውና መክሸፉ በሚነገርበት በዚህ ሰዓት በሳውዲና በህብረት ጦሩ በኩል የሚሰጠው ምላሽ የከበደ እንደሚሆን ይገመታል። የሳውዲ መከላከያ ሰራዊት ተመሳሳይ የሚሳኤል ጥቃትን ከመመከት የሚያስችሉ እጅግ ዘመናዊ የሚሳኤል መከላለከያ Patriot missiles በተለያዩ ቦታዎች በመትከል ተመሳሳይ ጥቃቶችን ለመከላከል መዘጋጀቱም ታውቋል ።

የሁቲ አማጽያን በሳውዲ ድንበር ከተማ በጀዛን በሰነዘሩት ተመሳሳይ ጥቃት የመኖሪያ ቤቶች ጥቃት የደረሰባቸው ቢሆንም በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱ የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው ። ይህ በእንዲህ አንዳለ ኤደን ላይ ሆነው የቀድሞዋን የመን መልሰው ለመቆጣጠር በሳውዲና በአረብ ሀገራት የሚገፉት የመን ፕሬዚደንት አብድል ረቡ አማጽያኑን ይረዳሉ ያሏቸውን ኢራንና ሊባኖስን አውግዘዋቸዋል!

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ 
ጥቅምት 18 ቀን 2009 ዓም