Saudi Arabia executes prince

በሳውዲ አረቢያ የንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት ልዑል ቱርኪ ቢን ሳዑድ አል ቱርኪ በፈጸሙት የግድያ ወንጀል  በ ሞት ተቀጡ

 

በሳውዲ አረቢያ የንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት ልዑል ቱርኪ ቢን ሳዑድ አል ቱርኪ በፈጸሙት የግድያ ወንጀል በተላለፈባቸው ውሳኔ መሰረት በትናንተናው እለት የሞት ፍርዱ መቀጣታቸዉን የሳውዲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል ። የሳውዲው ልዑል የሞት ፍርዱ የተፈፀመባቸው አድል ቢን ሰልማን አብድልከሪም መሀመድ የተባሉ ሳውዲ ዜጋን መግደላቸው በመረጋገጡ መሆኑን መረጃው ያትታል ።፥ ልዑሉ ግድያውን የፈጸሙት ከሪያድ ወጣ ብሎ በሚገኝ አል ቱማማ ኣል፡ጥሁማማ በተባለ ስፍራ በተፈጠረ ግጭት መሆኑንም ተጠቁሟል። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መግለጫ በማከልም የግድያው ወንጅል ከተፈጸመ ጀምሮ በተደረገው ከፍተኛ ማጣራት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከሶስት አመት በፊት ልዑሉን ጥፋተኛነት አረጋግጧል ። ፍርድ ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረትም ጉዳዩ ለከፍተኛ የሳውዲ መንግስት አካላት ቀርቦ ይሁንታ ማግኘቱን ሲታወቅ የሟች አድል ቢን ሰልማን አብድልከሪም መሀመድ ቤተሰቦች ካሳ ቀርቦላቸው ነበር ነገር ግን  ፍርድ እንዲፈፀም እንጅ የቀረበላቸውን ካሳ እንደማይቀ በሉ በማሳወቃቸው የልዑሉ አንገት በትናንትናው እለት መቀላቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሲያስረዳ በንጹሃንን ላይ ወንጄል የሚፈጽ ም ማናቸውም ሰው ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ መግለጫው አስታውቋል ።