It is a cake, which looks like a zebra!

 

የ ካካዋ ድብልቅ ምርጥ ኬክ አሰራር

 

 

አሰራር

 


4 እንቁላል
200 ግራም ሱኳር
236 ሚሊ ወተት
236 ሚሊ ዘይት
1 የሻይ ማንኪያ ቫኒልላ
250 ግራም ዱቄት
1 የገበታ ማንኪያ ቤኪንግ ፓዎደር
4 የገበታ ማንኪያ ካካው ዱቄት

 

የሚያስፈልጉ ነገሮች
መጀመሪያ ኦቨኑን ሞቅ ያድርጉት
እንቁላሉና ስኳሩን በ አንድ ላይ በደንብ ይምቱት
ከዛ ወተቱን ዘይቱን እና ቫኒላዉን ጨምረዉ ይደባልቁት
በሌላ ሳህን ዱቄት እና ቤኪንግ ፓውደር ይደባልቁ
ከዛ የተደባለቀዉን ዱቄት ወደ እንቁላል ድብልቁ ቀስ በቀስ ይጨምሩ
ዱቄቱ ኢስኪጠፋ በደንብ ይደባልቁ
ከዛ የተደባለቀዉን ሊጥ በ ሁለት ሰሀን ያካፍሉ
በ አንዱ ሳሀን ላይ ካካዋ ዱቀቱን ጨምረው ከለሩ እስኪቀየር ድረስ ይደባልቁ
ፓትራውን (ኬክ መስሪያ ሰሀን) እንዳይዝ ትንሸ ዘይት ይቀቡት
በ ካካዋ የተቀላቀለዉ ሊጣ እና ያልተቀላቀለዉን ሊጥ ቀስ በቀስ ላይ በ ላይ ይጨምሩ
ለ 40 ደቂቃ ኦቨን ዉስጥ ያስገቡት እና ያውጡት

 

መልካም ኬክ ይሁንሉ
ቢላል ማዓድ