the amazing demonstration at anwar today 20/7/2012
ሕዝቤ እና ውሎው በአንዋር!
ሐምሌ 13/2004“ድንቅ” የሚለው ቃል ዛሬ ህዝበ መስሊሙ በአንዋር ያሰየውን ይገልጠው ይሆን? በፍፁም!ኮሚቴዎቻችንን እና ታላላቅ ዳዒያንነንና የተከበሩ ዓለሞችን ሲያዋክቡ እና ሲያስሩ ያደሩ የመንግስት ኃይላት በአንዋር ዛሬ ጁምዓ ላይ የጠበቁት ከዚህ የተለየ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ወኪሎቻቹ በእንግልት እና እገታ ስር ሁኔታው የእግር እሳት ቢሆንበትም መስሊሙ የመረጠው ምላሽ ዝምታ እና ቀጣይነት ያለውን ሰላማዊ የትግል ስልት ብቻና ብቻ ነው፡፡ ምንግዜም ከአላህ ራሕመት ተስፋ አንቆርጥም፡፡አላህ ከእኛ ጋር ነው፡፡ ጥሎ አይጥለንም፡፡አንዋር መስጂድ ጁምዓ ከተሰደ በኋላ የታየው ትዕይንት ለአገራችን ህዝባዊ የተቃውሞ ታሪክ አዲስ እና እንግዳ ብቻ ሳይሆን አርዓያም ጭምር ነው፡፡ ልክ በላለፈው መልዕክት መሠረት ህዝቤ እጅ ለእጅ ተሳስሮ ፣አንደበቱን ለጉሞ እና ትንፍሽ ሳይል በአንድነት እና ትግል አይሞትም በሚል ስሜት ያቆላለፈውን ክንዶቹን ወደ ላይ በማንሳትና በማርገብገብ ተቃውሞውን ገልጧል፡፡ ይህም እንደባለው ከ15 እስከ 20 ደቂዎች ቆይታ ነበረው፡፡ ኮሚቴዎቻችንን በአካል ተገኝተው ይህን አይተውት ይሆን ስንል ጠይቅን፡፡ ኢንሻ አላህ! ሕዝቤ ተቆጥቷል! ሙስሊሙ ተቆጥቷል! ረብ የሌሽ እና የፖለቲካ ጠገግ ያላቸውን ዘዴዎች በመጠቀም ሙስሊሙን ከአቋሙ እንዲያፈገፍግ የሚደረጉ ሙከራዎች እውነት ለዲናችን ከሆነ እንዲህ የምንሆነው አላህ ያግዘናል፡፡ልብ በሉ ጥያቄያችን ሐይማኖታዊ እና ሐይማኖታዊ ብቻ ነው፡፡ ነገሩ እጅግ ቀላል እና ቀላል ነው፡፡ ሦስት ጥያቄ ሦስት መልስ ብቻ ነው የሚሻው፡፡ ያኔ የሁሉም ነገር መቋጫ ይቀርባል፡፡ኮሚቴዎቻችንን መገት፣ማንገላታት እና ለእስር መዳረግ ብሎም በየቦታው ሰዎችን በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በመሰብሰብ የሙስሊሙን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ስላሸት ለመቀባት ሞከርና ኮሚቴው የጥፋት ሃይል ነው ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ፕሮፓጋንዳ መንዛት ቦታውን ለለይ ይገባል ብቻ ሳይሆን ህዝብ እነኚህን ግለሰቦች ምን ያክል እንደሚያምናቸው፣ እንደሚወዳቸው እና እንደሚያከብራቸው ያለማወቅ ነው፡፡ ይህ አካሄድ ለፖለቲካ ሊበጅ/ሊሰራ/ ይችላል ለሐይማኖት ግን ቢያንስ ያጠራጥራል፡፡ ባይሆን የሚበጀው ለጥቂቶች አሉታዊ እና አፍረሽ አጀንዳ ከመሮጥ ሰፊው ህዝ ሙስሊም ከያዘው ሀቅ ጎን በመወገን ነገሩን ማብረድና መታረቅ ብሎም ፊታቸችንን ወደጀመርነው የልማት መንገድ ማዞር ነው፡፡አላህ ከኛ ጋር ነው፡፡ ሠላማዊ መብታችንን የማስከበር ሂደት በአላህ እርዳታ እስከ መጨረሻው ቀጥላል፡፡ህዝቤ ታዛዥነቱ ትላንትም ተመስክሮለታል፣ ዛሬም ተመስክሯል፣ ኢንሻ አላህ ነገም ይመሰከርለታል! አላሁ አክበር!