Mashallah >> Ethiopian ዘቢብ ዩኑስ ለካርቦን ልቀት ይረዳል ለተባለው አዲስ ቴክኖሎጂ ግኝት ባለቤት መሆኗ ተነገረ<< Allahu Akber

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ስራዋን በማከናወን የምትገኘው ዘቢብ ዩኑስ በበላይነት የምትመራው ቡድን በካርቦን ነፃ ቴክኖሎጂ ላይ ባደረገው ጥናት ያቀረበው አዲስ ግኝት ተቀባይነት አገኘ፡፡ ፕሪቶሪያ የሚገኘው ቨርቲካል ኒውስ ጋዜጣና ናኖ ቴክኖሎጂ የተባለው የምርመራ መጽሄት እንደዘገቡት በኢትዮጲያዊቷ መሪነት የተገኘው ግኝት “ሴራሚክ ሜታል” በመባል የሚጠሩ ንጥረ ነገሮች የፀሀይን ብርሃን የመቀበል ብቃትና አቅም የላቀ መሆኑን ያረጋግጣል ፡፡ የላቀ ቴክኖሎጂ በመፍጠር ረገድም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል የተባለው ግኝት በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ምርምር ጆርናሎች ላይ ታትሟል፡፡ ከግኝቱ ጋር በተያያዘ በዚህ ወር መጨረሻ በጀርመን አገር በሚካሄደው አለም አቀፍ ሳይንሳዊ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ እንደተዘጋጀች ተፅፏል፡፡ ስብሰባው ለ62ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ምርጥ ወጣት ተመራማሪዎች በማገናኘት ዕውቀት እንዲለዋወጡ የማድረግ ዓላማ አለው፡፡ ዘቢብ ዩኑስ በትግራይ ክልል በአዲግራት ከተማ ተወልዳ ትምህርቷን እዛው ተከታትላ የመጀመሪያ ድግሪዋን በሒሳብ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በ1997 ማግኘቷን ለማወቅ ተችሏል፡፡
Be the first to comment

Latest Articles

Most Popular