ke bezu weyeyet buhala shmgelenawu endemanqebel ena tegelu endemiqetel tenegere

ሰሞኑን ጅምር ላይ ስላለው ሽምግልናና ለሽምግልናው ሂደት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ተቃውሟችንን ለአንድ ጁሙዓ ብናራዝም የሚሉ ሃሳቦች ላይ በሰፊው ውይይት እየተደረገ መሆኑንና የውይይቱን ውጤትም ይዘን እንደምንቀርብ ቃል ገብተን እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በርካታ ወንድሞችና እህቶች በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይቶች ካደረጉ በኋላ በአላህ ፍቃድ ሁሉም የጋራ አቋም ላይ መድረስ የቻሉ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ህብረተሰባችን ጉዳዩ እጅግ አሳስቦት በአካልም በፌስቡክም ሃሳቦችን ለመስጠት የነበረው ርብርብ ሊደነቅ የሚገባውና የደረሰበትንም የብስለት ደረጃ የሚያሳይ መሆኑን ሳናበስር አናልፍም፡፡ 
የተቃውሟችንን ቀጣይነት አስመልክቶ 
• የሽምግልናው ሂደት ከመነሻው ጀምሮ ከሚዛናዊነት ይልቅ ኮሚቴዎቻችንና ሰላማዊ እንቅስቃሴያችንን በመወንጀል የተጀመረ በመሆኑ፤ 
• ከመንግስት ጋር እንዲደራደሩ የመረጥናቸው ኮሚቴዎች አላግባብ ታስረው ያሉ በመሆኑ፤
• መንግስት በአንድ በኩል ሽምግልና እያለ በሌላ በኩል ያለፈውን ጁሙዓ ጨምሮ እስካሁንም በርካታ ወንድሞችና እህቶችን ለእስርና ድብደባ እየዳረገ በመሆኑ፤
• በጥቅሉ ከመንግስት በኩል ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት በጎ ተነሳሽነት ያልታየ በመሆኑ
የጁሙዓ ተቃዉሟችን ከበፊቱ በተጠናከረ ሁኔታ አዳዲስ ስልቶችን አካቶ መቀጠል እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ የሽምግልናው ሂደት ተቀባይነት እንዲያገኝ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስመልክቶ የተደረሰባቸውን ውሳኔዎች በቀጣይነት የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ አላሁ አክበር!
Be the first to comment

Latest Articles

Most Popular