half million Ethiopian Muslim in awollya today 500,000 የሚጠጋ ሙስሊም ህብረተሰብን የአወልያ ዉሎ
አላሁ አክበር!!!አላሁ አክበር!!! አምስ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሙስሊም ህብረተሰብን ያስተናገደዉ የአወልያ የጁምአ ዉሎ!!!! በዛሬዉ እለት በአወልያ አምስ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሙስሊም ህብረተሰብ ለጁምአ ሰላትእና ዉጤት ለመስማት እንደተገኘ ተገለፀ::የጁምአ ሁጥባ በአወልያ መስጂድ ምክትል ኢማም በኡስታዝ ሱለይማን የቀረበሲሆን ሁጥባዉም የአህባሽን ጥመት በማስመልከት የቀረበ ነበር::ሁጥባዉም እንደተናቀቀ የጁምአ ሰላት በኡስታዝ ሱለይማን ኢማምነት የተሰገደ ሲሆን በሰላቱም ላይ በተደረገዉ የቁኑት ዱአ የአብዛኛዉ ሙስሊም አይን በእንባ እንደታጠበ ተመልክቷል:: ሰላቱም ከተጠናቀቀ ቡሀላ መድረክ መሪዉ መድረኩንበመረከብ ህዝቡ አንድነቱን እስከመጨረሻዉ ለመጠበቅ እጅ ለእጅ በመያያዝ ቃልኪዳን እንዲገቡ በማድረግ ፕሮግራሙን መጀመሩን በተክቢራ አብስሯል::የመጀመሪያዉ ፕሮግራም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ከመንግስት ጋር የሙስሊሙ ተወካዮችያደረጉትን ዉይይት ምን ይመስል እንደነበር በደንብ አብራርቷል:: በፌደራልጉዳዮች ሚኒስተር ለኮሚቴዎቹ ተገብቶላቸዉ የነበረዉን ቃል በሙሉ ያልፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል:: ከዚህም መካከል የስም ማጥፉቱ እንደሚቆም እና ማንኛዉም ሰዉ አይታሰርም ብሎ ቃል የገባ ቢሆንም ከዛ ቡሀላ ግን በጣም ብዙ ሰዎች መታሰራቸዉን እና የኮሚቴዎቹን ስም ማጥፉት መቀጠሉንም ገልፀዎል::በየካቲት 26ቱም ስብሰባ ሚዲያዎች የቀረፁትን ለህዝብ ከመቅረቡ በፊት ኮሚቴዎቹ እንደሚያዩት ቃል ቢገባላቸዉም ስብሰባዉ ሳያልቅ ኮሚቴዎቹ ለመግሪብ ሰላት በወጡበት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ዴታአቶ ሙሉጌታ ለሚዲያ ዉጤቱን ማስተላፉቸዉን ጨምረዉ ገልፀዋል:: በሁለተኛዉ ፕሮግራም ህዝበ ሙስሊሙ በጉጉት ሲጠብቀዉ የነበረዉ የየካቲት ሀያስድስቱን የመንግስት ምላሽን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ሰብሳቢ በኡስታዝ አቡበከር አህመድ ቀርቧል:: በሪፓርቱም መሰረት መንግስት ሰጠሁት ያለዉ ምላሽ ሙስሊሙ የጠየቃቸዉን ጥያቄዏች በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም ሲዞዞር እንደነበር ገልፀዎል:: በመንግስት የተሰጠዉ ምላሽ እላዩ ሲታይ መልስ የሚመስል ነገር ግን ምላሹ ብዥታ ያለበት እና ጥልቅ ማብራሪያ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዎል::
ምላሾቹ ግልፅ ባለመሆናቸዉ እንዲብራሩ ቢጠየቁም እንዳልተብራራላቸዉ ገልፀዎል:: በመንግስት ምላሽ መሠረት የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ በተቻለ መጠን በፍጥነት በገለልተኛ ወገን ይካሄዳል የሚል የተዳፈነ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አህባሽን በተመለከተ አህባሽ አዲስ ሳይሆን የቀድሞዉን እስልምና የሚያስተምር ነዉ:: በማንም ሰዉ ላይ ጫናም ሆነ ግዳጅ አላደረገም ስለዚህ አህባሽ ይቀጥላል ማለታቸዉን እና አወልያ አክራሪዏችን ሲፈለፍል የኖረ ተቖም ስለነበር መጅሊስ ተረክቦት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱቀጥሎ ሳላ ለህዝብ ይሰጥ ብሎ ማለቱ ተገቢአይደለም በመሆኑም በመጅሊስ ስር እንዳለይቀጥላል በማለት መንግስት ምላሹን የሰጠመሆኑን ገልፀዎል:: በዉይይቱ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ዉይይቱን ወደሌላ አቅጣጫ ለመዉሰድ ጥረት ሲያደርጉእንደነበር ጨምረዉ ገልፀዎል:: በዉይይቱ መጨረሻ ላይም ኮሚቴዎቹ መንግስት የሰጠዉምላሽ ለጥያቄዎቻችን የተሟላ ምላሽ ባለመሆኑ ለሚቀጥለዉ የመንግስት አካል እስከ ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ድረስ ጥያቄዎቹን እንደሚያቀርቡ በመግለፅ ስብሰባዉን መጨረሳቸዉን እስታዉቀዋል:: ኡስታዝ አቡበከር ሪፓርቱን ከጨረሰ ቡሀላኡስታዝ በድሩ ሁሴን ለፌደራል ጉዳዮች የገባዉን የኮሚቴዉን አቖም የሚገልፅ ደብዳቤ ለህዝቡ አንብበዋል:: በመጨረሻም የመጅሊስን ታሪክ እና ግድፈቶች በማስመልከት ሀሰን አሊ ፕሮግራም አቅርቧል:: የዛሬዉ ተአምራዊ የአወልያ ሰልፍ ዱአ በማድረግ ተጠናቖል:: ሁለተኛዉየትግል ምእራፍ መጀመሩም የዛሬዉ የአወልያ ዉሎ አሳይቶናል::
በመጀመሪየያ ደረጃ ለሰጣችሁን ወቅታዊ መረጃ አላህ ይስጥልን እላለሁ፡፡ በመቀጠልም ሙስሊሙ በዚህ አጋጣሚ የራሱን መሪና ፓርቲ ለመፍጠር ይህ አጋጣሚ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ስለሆም እንቅስቃሴያችን እቅድ ሊኖረው ይገባል፡፡ የመጀመሪያው ያው አሁን አየተሰራ ያለው ተግባር ነው - ለሦሰቱ ጥያቄዎቻችን መልስ ማግኘት፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በዚህ አጋጣሚ እንዴት ሙስሉሙ ህብረተሰብ የራሱ ፓርቲ/ድርጅትና መሪ ያገኛል ለመሚለወው ሰስረራ መሰስረራተት ይጠይቃል፡፡ ሰስለሀሆነመም ረራሰስነን መማደረራጀተትነና ተትገግለላቸችነን ከጠጥነንሰስሰሱ ሀሁለሉነን አቀፈፍ መሀሆነን አለበተት፡፡ የአላህ ነስር ቅርብ ነው እንሻ አላህ
አላሁ አክበር ትግላችን ይቀተላል