berari wereqet betenewal yetebalut tefetu
በራሪ ወረቀት በትናችኋል በሚል ታስረው የነበሩት ወጣቶች ተፈቱ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል የካቲት 16/2004
ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ምንጩ ያልታወቀ በራሪ ወረቀት አወለያ መስጂድ አካባቢ በትናቹኋል በሚል ታስረው የነበሩት ወጣቶች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ተፈቱ፡፡
በአወልያ እየተሰገደ ባለው የጁምዓ ሰላት ላይ አህባሽንና መጅሊስን የሚቃወም በራሪ ወረቀት ለህዝበ ሙስሊሙ ለመበተን ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ነበር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ፡፡
ከታሰሩት ውስጥ ሰሚር የተባለ ወጣት ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበረና እህቱን በስልክ አነጋግረን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ይህ ምንጩ አልታወቀም ተብሎ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የተደረጉት ወጣቶች ወረቀቱን እንዲበትኑ ያዘዟቸውን ሰዎች እስካልጠቆሙ ድረስ በእስር እንደሚቆዩ ተገልፆላቸው ነበር፡፡ በፖሊስ ጥቆማ ሲፈለግ የነበረው አብዱረዛቅ የተባለው ወጣት ፖሊስ ጣቢያ ቀርቧል፡፡ እርሱ ከቀረበ በኋላም እሱና ሌሎቹ ቀድመው የታሰሩት ጓደኞቹ ተፈተዋል፡፡