BE DESE 10 WETATOCH TASERU በደሴ 10 የሚሆኑ ወጣቶች ታሠሩ

በደሴ 10 የሚሆኑ ወጣቶች ታሠሩ የሸዋ በር መስጂድ ኢማም ዛቻና ማስፈራሪያ ደረሰባቸው በደሴ ከተማ ሰሞኑን በተለያየ ጊዜ 10 ወጣቶች በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ወህኒ መውረዳቸውን ምንጮች አስታወቁ ታማኝ የሬዲዮ ቢላል ምንጮቻችን ከሥፍራው እንዳደረሱን ወጣቶቹ የታሰሩት ህዝበ ሙስሊሙ ከሕገመንግስቱ ጋር የተያያዙ የኃይማኖት የመብት ጥያቄዎቹን ማሰማት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ይሁንና በተጨማሪ የተያዙት ጉዳይ ምን እንደሆነ በግልፅ የታወቀ ነገር አለመኖሩን አመልክተዋል ወጣቶቹ ባለፈው ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ፖሊስ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ይሠጠኝ በማለቱ ክስ ሳይመሰረትባቸው ቀርቷል ፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የሸዋ በር መስጂድ ታዋቂ አሊም የሆኑት ሼህ ያቁት በደሴ ከተማ ወረዳ እስተዳደር አካላት ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ሬዲዮ ቢላል የካቲት 30/2004 MARCH 9, 2012
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular