be alamata 4 gelsboch taseru be ahbash mekniyat
በአላማጣ ከተማ አራት ግለሰቦች መታሰራቸው ተገለፀ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 4 2004 በአላማጣ አካባቢ የአህባሽን አስተምህሮት ለመስጠት የሄዱ ግለሰቦች ለማስተናገድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው፡ የአህባሽን አስተምዕሮት ለመስጠት አላማጣ አካባቢ ግለሰቦቹ የተንቀሳቀሱት ባለፈው ቅዳሜ ነበር፡፡ ሁለት ኢትጲያውያንና አንድ ሊባኖሳውያን የአህባሽ አስተምህሮት ለአምስት ቀናት በአላ አካባቢ ከሚገኘው መስጂድ ለመሰጠት ያሰቡት ጉዞ ግን አልተሳካም፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ የአካባቢው ሰዎች አስተምህሮቱን አንቀበልም በማለታቸው ነበር፡፡
አስተምህሮቱን በኃይል የመጫን እንቅስቃሴው ታዲያ እስር ማስከተሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
ሁለት የመስጂድ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ግለሰቦችም መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡