Alhamdulila zare ye comitewochachne beteseboch ziyara endeteyequwachewu tesema
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በእስር ላይ ቢገኙም እስከዛሬ ድረስ ቤተሰቦቻቸዉ እንዲጠይቖቸዉ የማይፈቀድ የነበረ ሲሆን ዛሬ ግን በአላህ ፈቃድ የኡስታዝ አቡበከር አህመድ, የኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና የኡስታዝ አህመድ ሙስጠፉ ባለቤቶች ዘይረዎቸዎል:: በሚያስደንቅ ሁኔታም በእስር ላይ ሆነዉም የቁርአን ተፍሲር በታላቁ አሊም በዶ/ር ከማል እየቀሩ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል:: የታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበልም የቁርአን ሂፍዝ እየተማረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል:: ከራሳቸዉ አልፈዉም በእስር ቤት አብረዎቸዉ ለሚገኙ ሙስሊም ታሳሪዎች እየጠቀሙ ይገኛሉ:: በተጨማሪም ኮሚቴዎቻችን, ዳኢዎቻችን እንዲሁም አሊሞቻችን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል:: አልሀምዱሊላህ!!! ይህ ሁላ የአላህ ችሮታና ፀጋ ነዉ!! ከእስር አላህ ያወጣቸዉ ዘንድም ዱአ እናድርግላቸዉ!!!
ድምፃችን ይሰማ