**** ግልጽ ደብዳቤ ለሳሞራ ዩኑስ ****
ይድረስ ለኢትዮጵያ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ ዩኑስ በመጀመሪያ የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኩኝ ለጤናዎ አንደምን አሉ እላለሁኝ። በመቀጠልም እርሶ እና የትግል ጓዶ ጫካ በመግባት የታገላችሁለት አንዱ አላማ የእምነት ነጻነት ለማረጋገጥ ነበር። ይህንን የእምነት ነጻነት ለማስከበር እነ ቀሽ ገብሬን የመሳሰሉ ከ60,000 በላይ ሰራዊት መስዕዋት ሆነዋል። ዳሩ ግን አሁን እየፈጸማችሁት የለው ነገር ከታገላችሁለት አላማ ውጪ ነው እንዲያውም በተቃራኒው ነው።
ወደ ዋናው ቁም ነገር ስገባ እርሶ በከባድ ሃላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ ሙስሊም የጦር አዛዥ ኖት ፤ በተለይም በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባልተረጋጋበት ሁኔታ ላይ ከባድ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ ባለስልጣን ኖት። እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰዐት እኛ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መብታችን ተገፎ ብሎም በእስር እየተሰቃየን እና እየተገደልን እንደምንገኝ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በተለይም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚተማመኒባቸው ኡለሞች፣ ዱአቶች፣ ባለሃብቶች እና ሙህሮች በእስር ክፉኛ እየማቀቁ ይገኛሉ።
በጣም የሚያሳዝነኝ እርሶ የህን ኢስላምን ከኢትዮጵያ የማጥፋት ዘመቻን ዝም ብለው ማየቶ ነው። እንዴት ሙስሊም ሙስሊም ላይ ይጨክናል፤ በኢትዮጵያ ሙስሊም ታሪክ ውስጥ ታሪክ ሲወቅሶ የሚኖር ጥቁር ነጥብ አያሳረፉ መሆኖትን አይዘንጉት። ሳስቦት እርሶ አሁን በዕድሜዮት መባቻ ላይ ነው የሚገኙት፤ ታድያ እንዴት ሰው ከአላህ መጋናኛው በቀረበ ሰዐት ለአላህ ዲን(ኢስላም) ጠላት ይሆናል ነገ አላህ ፊት ለኢስላም ምን ሰራሁ ሊሉ ነው?
እኔ ግን አሁን አንድ ነገር ልምከርዎ ፤ እስከ ዛሬ ለኢስላም አንድ የሚታይ ነገር አንዳልሰሩ ግልጽ ነው። ነገር ግን አሁን ሙስሊሙ ኡማ በተቸገረበት ቀውጢ ሰዐት ታሪክ በኩራት ሲዘክሮ የሚኖር ነገር መስራት ይችላሉ ይኸውም እየተደረገብን ያለውን ግፍ በመቃወም እንዲቆም የበኩሎን ጥረት ማድረግ ይችላሉ። አለበለዚያ ግን ነገ ማንም ሰው በማይበደልበት የቂያም ቀን 40 ሚልዮን ህዝብ ይፋረዶታል። በመጨረሻ አላህ ቅኑን ጎዳና እንዲመሮት አለምነዋለሁኝ።
ከሰላምታ ጋር
መህዲ ማይልስ