ጠላታችን ኢሃዲግ ወይስ መጅሊስ?
ጠላታችን ኢሃዲግ ወይስ መጅሊስ?
~~~~~~~~~~~~~~~~
“እኛ ድል ያደረግነው ለጥያቄያችን መልስ በማግነታችን ሳይሆን ማን ጠላታችን እንደሆነ ማወቃችን ነው”።
ብዙዎቻቹህ ይህንን ርዕስ ስትናቡ ልተካፉ ወይም ሌላ ነገር ታስቡ ይሆናል።ያም ሆነ ይህ “እውንትን ትናግሮ የመሸበት ማደር “ እንዲሉ የሚከፋ ሰው በኖርም የመከፋት መብቱን እያከበርኩ እኔ ግን ለቀጥል:--
ወደ ርዕሴ ስገባ :-ባለፈው አንድ ክርስቲያን ወዳጄ እንዲህ አለኝ “እናንተ ሙስሊሞች! ለምንድን ነው መንግስት አህባሽን በናንተ ላይ መጫኑን እያወቃቹህ መንግስትን በመቃዎም ፋናታ ለምን መጅሊስን ትቃወማላቹህ? አሃያውን ፈርቶ ዳውላን አይሆንም ? የመጅሊስ አመራሮችን የሾመው መንግስት መሆኑን አያወቃቹህ እነዚህን አመራሮች የሾመውን መንግስትን ከመተቸት ይልቅ ለምን የመጅሊስ አመራሮችን ትትቻላቹህ ?“ ብሎ ጠየቀኝ! ይህ ጥያቄ የ አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ ሰውች ብቻ ሳይሆን የኔም በመሆኑ ለናንተ ለማቅረብ ወደድኩ።
እንደሚታወቀው ዶክተር ሰሚር በጊዎን በተደረገው ስበሰባ ላይ በመንግስት(በ ኢሃዲግ) ተጋብዘው በመምጣታቸው ለመንግስት ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረባቸው ይታወሳል።ሰለዚህ “አህባሽን መጅሊስ ነው ያመጣው “ የሚለው አባባል ተረት ያደርገዋል።
እንዲሁም በተደጋጋሚ ሙስሊሞን የመከፋፈል እና የሙስሊምን ስም የማጥፋት ዘመቻ ሲሰራብን የነበረው የመንግስት ሚዲያዎች እንጂ የመጅሊስ ሚዲያዎች አልነበሩም።ሙስሊምን ለመከፋል የሚሞክሩ አካላት የኛ ጠላት ከሆኑ ታዲያ ጠላታችን ማን ነው?ይህ ብቻም አይደለም ሙስሊምን ለሁለት በመክፈል ከፊልን “ሱፊ” ከፊልን “ውህቢያ” ብለው ሲያበቁ “ዋህቢያ” ያሉትን ክፍል ከመድረ ገጽ እናጠፋለን ብለው በተደጋጋሚ የፎከሮት እነ ዶክተር ሺፈርውን የያዘው የ ኢሃዲግ መንግስት ነው።
ሙስሊም ይህንን ሁሉ እያወቀ ሰላም ወዳድ ከመሆኑ የተነሳ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ሲል ።መንግስት መበደሉን እያወቀ “አይ! እኛን የበደለን መጅሊስ እንጂ መንግስት አይደለም”እያለ ።አንድ ዲንጋይ ሳይወረውር የማንንም መበት ሳይገፋ ፤በኢትዮዲያ ታሪክ ውስጥ ማንም ያላደረገውን ከ አራት ወር በላይ የፈጀ ታላቅ ሰላማዊ ታቃውሞ አድርጓል።ይህንን ፍጹም የሆነ ተቃውሞ ለማደናቀፍ መንግስት የተለያዩ ደህንነቶች በመላክ ለማደናቀፍ የልፈነቀለው ድንጋይ የለም።በ አላህ እርዳት ሊከሽፍ ችሏል !!አላሁ አክበር!!
መንግስት ይህንን ታላቅ ፤ለረጅም ጊዜ የፈጀ ተቃውሞ ፍጹም ሰላማዊ መሆኑን እያወቅ “በሃያማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ጸረ ህገመንግስት ፤ጸረ ሰላም ናቸው” ሲል አድምጠነዋል!ለመሆኑ ጸረ ህገመንግስት ማለት ምን ማለት ነው? ህግን አክብሮ በሃጋዊ መንገድ ሂዶ ህገመንግሳታዊ መብቴ የከበር ማለት እንዴት ሆኑ ነው ህገወጥነት የሚባለው? እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ህገወጥነት ማለት ህግ ይከበር ያለ ሳይሆን ህግን በመጣስ በሃያማኖታችን ውስጥ “ሸህ ነኝ” እያለ ልክ እነደዓሊም ፈትዋ እየሰጠ ያለው እንደነ ዶክተር ሸፈርው አይነቱን የሰበሰበው የኢሃዲግ መንግስት ነው።አላህ ሂዳያ ይስጣቸው ከማለት ውጪ ምን አንላቸው።እኛ እንደነሱ አይደለንምና ።
በሰተመጨረሻም እኛ ሙስሊሞች ባደረግነው እልክ አስጨራሽ ትግል ትልቅ ድል አግኝተናል ከድሎች ሁሉ ድል የጠላቶቻችንን ሴራ ማክሸፋችን ነው።እነሱ አህባሽን ያመጡልን አንድነታችንን ለመናድ፤የሙስሊሙን ንቃተ ሂሊና ለመግደል፤ባለፈው ጠቃላይ ሚኒስቴሩ እንደገለጹን ታቦት ሸኚ መስሊም ለማድረግ ነበር።በ አላህ እርዳታ ግን ይህ ሁሉ ሊከሽፍ ችሏል።አላሁ አክበር!! ሙስሊም በ አሁን ሰአት ከየትኛውም ጊዜ በላይ እንደነቱን ጠብቃል፤ነቃተ ህሊናውም በጣም ከፍ ብሏል ።አላህምዱሊላህ ።
يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ
የ አላህን ብርሃን በ አፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ አላህም ከሐዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑ ገላጭ ነው። (ቁርኣን ሱረቱ አል -ሶፍ 8)
አላሁ አክበር!!አላሁ አክበር!!!አላሁ አክበር!!