የፖሊስ አባላት የሆኑ ሙስሊሞች መለዮ አድርገው መስጂድ እንዳይገቡ የክልከላ ትዛዝ ተሰጣቸው
የፖሊስ አባላት የሆኑ ሙስሊሞች መለዮ አድርገው መስጂድ እንዳይገቡ የክልከላ ትዛዝ ተሰጣቸው
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 24/2004
በአዲስ አበባ አስተዳደር የሚገኙ ሙስሊም ፖሊሶች መለዮ አድርገው ወደ መስጂድ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የሬዲዮ ቢላል ምንጮች አስታወቁ፡፡
ምንጮቻችን ዛሬ እንዳስታወቁት መለዮ አድርገው ወደ መስጂድ እንዳይገቡ የተከለከሉት 22አካባቢ በሚገኘው የትራፊክ ፅ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ባለፈው አርብ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በተሰጠው አዲስ መመሪያ ነው፡፡
በስብሰባው የተሳተፉ ሙስሊም የትራፊክ ፖሊስ አባላት በወቅቱ በሰጡት አስተያየት እገዳውና ክልከላው ህገ መንግስታዊ የሀይማኖት ነፃነትና መብት ድንጋጌዎች እንደሚፃረር ገልፀዋል፡፡
ይሁንና የመድረኩ መሪ የሆኑ አዛዦች መመሪያው ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ የፀና መሆኑን ገልፀዋል፡፡በእለቱ በስራ ላይ የነበሩ ሙስሊም የፖሊስ አባላት የጁምዐ ሰላት ለመስገድ መለዮአቸውን ሌላ ቦታ አስቀምጠው ለመስገድ የተገደዱ ሲሆን አንዳንዶቹ ማዕረጋቸውን ብቻ በማውለቅ ወደ መስጂድ ሲገቡ መታየታቸውን ምንጮቻችን አስረድተዋል፡፡