የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ቢታሰሩም ተቃዉሞዉ አልተቋረጠም <
ለጁመዓ ጸሎት በአዲስ አበባዉ የአንዋር መስጊድና በአካባቢው የተሰባሰቡ በብዙ ሽህዎች የሚገመቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዛሬም ተቃዉሞአቸዉን አካሄደዋል
አስራ ሰባቱም ሙስልም ማህበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና በርካታ የእምነነቱ ተከታዮች ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ መተሰራቸዉ ይታወቃል። ለጁመዓ ጸሎት በአዲስ አበባዉ የአንዋር መስጊድና በአካባቢው የተሰባሰቡ በብዙ ሽህዎች የሚገመቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዛሬም ተቃዉሞአቸዉን አካሄደዋል። አፋቸዉ እንደተሸበበ በማመልከትና እጆቻቸዉን የፊጢኝ ወደሁዋላ በማሰር መልክና ሌሎች ምልክቶች ጭምር ተቃዉሞአቸዉን እንደገለጹ ተመልክቶአል።
የፌድራል ፖሊስ ኮምሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ወርቅነህ ገበየሁ ሰሞኑን ለመንግስት የመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በቁጥጥር ሥር በዋሉት የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ተጀመረ ያሉትን እንቅስቃሴ ከአክራሪነት ጋር የተያያዘ ብለውታል።