የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ በአንዋር እና በኑር መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙን እንዳልጠራ አረጋገጠ
የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ በአንዋር እና በኑር መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙን እንዳልጠራ አረጋገጠ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 20/2004
የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ አንዋር መስጂድና በኑር መስጂዶች ሙስሊሙን እንደጠራ ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ የተሳሳተ መሆኑ ተገለፀ፡፡
መሀል አዲስ አበባ ዛሬ በስፋት እየተወራ የሚገኘው ይህ መረጃ ከኮሚቴው አባላት እንዳልተላለፈ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለሬዲዮ ቢላል አስታውቀዋል፡፡
ይሁንና ነገ ጁምዐ ህብረተሰቡ በየአካባቢው ባሉመስጂዶች የሚያደርገው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ካለ ሂደቱ ሠላማዊ ሊሆን እንደሚገባው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ህብረተሰቡ ሰላሙን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ያሉት ዑስታዝ አቡበከር አህመድ በየአካባቢው የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሠላማዊ መሠረትና መስመራቸውን የጠበቁ እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡