አስደሳች ዜና Ethiopian Muslim be Washington DC yesedeqa ena ye andenet program akahedu
አስደሳች ዜና
በዋሽንግተን ዲሲ ና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጽያዊያን ሙስሊሞች ታላቅ የዓንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም አካሄዱ። በዚህ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ በዋሽንግተን ዲሲ ና አካባቢው የሚኖሩ ሙስሊሞች የተሳተፉበት ፕሮግራም በሃገር ቤት መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚያደርሰውን በደልና ግፍ ከማውገዝ በተጨማሪ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም ገልጾል። ዛሬ ቅዳሜ ጁላይ 28 በተካሄደው በዚሁ ፕሮግራም ላይ በእስር ላይ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች አላህ ከጨቆኞች እስር ነጻ እንዲያወጣቸው እንዲሁም በፖሊስ ድብደባና ጭስ ለተጎዱ ወገኖች አላህ አፊያቸውን እንዲመልስላቸው ዱአ ተደርጎል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ የሚገኙት በድር ኢትዮጽያ፣ ፈርስት ሂጅራ፣ ነጃሽ የፍትህ ካውንስል እና ሰላም ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት የኢትዮጽያ ሙስሊም ቅንጅት መስርተዋል። ቅንጅቱም የመጀመሪያ የጋራ ስራ ያደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ሀሙስ ኦገስት 2 ያካሂዳል። ኢንሻአላህ በቀጣይም ቅንጅቱ የታሰሩ እንዲፈቱና የሙስሊሙ መሰረታዊ መብት እንዲከበር ከፍተኛ የሆነ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል።