ትኩስ መረጃ leak from government about mejlis mercha
ወንድሞችና እዚህ የሚገለጹ መረጃዎች ዝም ብለው እንዲነበቡ ብቻ ሳይሆን ከተነበቡ በሁዋላ ሁሉም በተቻለው አቅም መረጃውን በማዳረስም ሆነ የጸረ ሙስሊሞችን ሴራ ለማኮላሸት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ሀላፊነታችንን እንድንወጣ ጭምር ነው፡፡
ትኩስ መረጃ 1. የፌዴራል ጉዳዮች የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ ከሰኔ 13 እስከ 15 እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል፡፡ ምርጫውን በድንገት ህዝቡ ሳያስበው ለማካሄድና ቶሎ ለማጠናቀቅ ጥድፊያ ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ምርጫውን በቀበሌ በኩል ለማድረግና ህዝቡን ከረመዳን በፊት ለመሸወድ ስላሰቡ በገጠርም በከተማም የምንገኝ ሁሉ በየቀበሌያችን ያሉ እንቅስቃሴዎችን በጥብቅ መከታተል አለብን፡፡ በየወረዳችንና ዞናችን የሚገኙ የመጅሊስ ተወካዮችንም እንቅስቃሴ በደንብ እንቃኝ፡፡ ምክንያቱም የሽወዳ ስራ ለመስራት እንዳሰቡ ታውቆባቸዋል፡፡
ትኩስ መረጃ 2. ምርጫን በተመለከተ ጨምሮ የደረሰን መረጃ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ በድጋሚ ለምርጫ መወዳደር መወሰኑንና ለምርጫ ቅስቀሳም ከሰሞኑ ሀረር ኮምቦልቻ ለሳምንት ያህል ከርሞ መመለሱ ተሰምቷል፡፡ ብር ለአካባቢው ህዝብ ሁሉ ሲበትንም እንደነበር ይነገራል፡፡ ፌዴራል ጉዳዮች ከኦሮሚያ ከሚመረጡ 50 የኦሮሚያ ተወካዮች 30 ሰዎችን መርጦ የጨረሰ ሲሆን 20ዎቹ ግን በህዝብ ይመረጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ሆኖም ከእነዚህ ህዝብ ከሚመርጣቸው 20 ተወካዮች መካከልም ፌዴራል ጉዳዮች የራሱን ሰዎች ለማስረግ ጥረት ያደርጋል፡፡ የመጅሊስ አመራሮችም በሙሉ ከሰሞን ለቅስቀሳ ወደየክልላቸው ይጓዛሉ፡፡ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ ሰሞንን ለመጅሊስ ሰራተኞች እኛ ሰልጣን ብንለቅ እንኳ ተመርጠው የሚመጡ ሰዎች እኛ ካስቀመጥነው መንገድ ውጪ የመሄድ አማራጭም መብትም የላቸውም ብሎ ተናግሯል፡፡ አስመራጮችን በተመለከተ ፌዴራል ጉዳዮች ከኦሮሚያ ለሚመጡ 190 የአህባሽ ስልጠና የወሰዱ አስመራጮች ከዚህ ሰምንት ጀምሮ የ9ቀን ስልጠና ይሰጣል፡፡
ትኩስ መረጃ 3. በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ አባዲ ዘሙ መንግስት የአህባሽን ስልጠና እንዲያካሂድ ከአሜሪካ መንግስት 250 ሚሊዮን ዶላር መቀበሉንና ስልጠናውንም ሊያቆም እንደማይችል ሱዳን ኤምባሲ ውስጥ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ ጨሎም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሊባኖስ ቤሩት ከሚገኘው የአህባሾች ግሎባል ዩኒቨርሲቲ ጋር የአህባሽን ስልጠና በዘላቂነት ለመስጠት ፍርርምና ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከሰሞኑ ሀረር ውስጥ ገልጧል፡፡ አወሊያንም ትናንሽ ስልጠናዎች ሰጪ በማድረግ በሂደት ግን የአህባሽ ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ መታሰቡም የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን ተናግሯል፡፡
ትኩስ መረጃ 4. የመጅሊስ አመራሮች በአሁኑ ሰአት የብር ፈሰስ የሌላቸው መሆኑ የታወቀ ሲሆን ሳኡዲ ለሐጅ በሄዱበት ወቅት ዘርፈው በኢትዮጵያ ቆንስላ በአደራ ያስቀመጡትን 8 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ አልቁድስ ጋዜጣም በብር እጥረት ምክንያት ክፍያው ቆሞበታል፡፡ ለዚህም ነው ከባለፈው ሳምንት ወዲህ ወሃቢያ እያለ ማላዘኑን ያቆመው፡፡
ትኩስ መረጃ 5. የመንግስት ሚዲያዎች በተለይም አዲስ ዘመን ሙስሊሞችን ማሻማቀቁን ቀጥሎበታል፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ ዘመን ወሀቢያ እና ሱፊያ እያለ የሂላፍ አጅንዳዎችን በተከታታይ ለማተምና የተገኘውን አንድነት ለመናድ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡
ትኩስ መረጃ 6. የአዲስ አበባ መጅሊስን አስመልክቶ ፕሬዚዳንቱ ሰይድ ግዛውና ዋና ጸሐፈው ሁሴን ኑረዲን ከፍተኛ ጸብ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ የፀባቸው መንስኤ ብር ሲሆን ሁሴን ኑረዲን በግሎ መልምሎ ባስቀጠረው ምክትል ፕሬዚዳንት በኩል የፈለገውን ደብዳቤ እያስፈረመ ፕሬዚዳንቱን ድጋፍ አልባ ያደረገው ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ሰይድ ግዛውም ሁሴን ኑረዲን በመርዝ ይገድለኛል ብሎ በመስጋት አዲስ አበባ መጅሊስ ውስጥ ማኪያቶ እና ቡና እንኳ መጠጣት ማቆሙ ተሰምቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁሴን ኑረዲን ምርጫ እንዳይወዳደርና በምትኩም ሌላ ስራ እንደሚሰጠው በመንግስት ቃል ተገብቶለታል፡፡ የአዲስ አበባ መጅሊሱ ሁሴን ኑረዲን በየቦታው ቲሸርት የለበሱና ተክቢራ ያሉ ሰዎች ላይ በማስመስከር ለእያንዳንዱ መስካሪ 1300 ብር እየከፈለ ይገኛል፡፡ መስካሪዎቹ ፍርድ ቤት ሄደው ከመመስከራቸው በፊት ምን ብለው መመስከር እንዳለባቸው የአዲስ አበባ መጅሊሱ ሁሴን ኑረዲን እና አቶ ሰይድ ኢብራሂም የተባለ ለምስክርነት በመጅሊሱ የተቀጠረ ሰው ገለጻ እንደሚሰጧቸው ታውቋል፡፡
ትኩስ መረጃ 7. የአዲስ አበባ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስብሰባ ጠርቶ የነበረ ቢሆንም በብዙዎቹ ቦታዎች 500 ሰው ተጠርቶ የተገኘው 30 እና 40 ስው ብቻ በመሆኑ በብዙዎቹ ቦታዎች ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ስብሰባዎቹ በተካሄዱባቸው ቦታዎች በየመስጊዱ ተክቢራ የሚሉና የሚያስብሉ ሰዎችን አሳልፋችሁ ስጡን ብለው ጠይቀዋል፡፡ ግን ስብሰባዎች ብዙም ሳይሳካላቸው ቀርተዋል፡፡