በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቁርዓንን ክብር ያጎደፈው ግለሰብ ድርጊቱን እንደፈጸመ አመነ፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቁርዓንን ክብር ያጎደፈው ግለሰብ ድርጊቱን እንደፈጸመ አመነ፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 23/2004
በጎንደር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ተቆጣጣሪ የነበረው ግለሰብ የቅዱስ ቁርዓንን ገፆች መፀዳጃ ቤት መጠቀሙን አመነ፡፡
ግለሰቡ ድርጊቱን መፈፀሙን ያመነው ከትላንት በስቲያ ለፖሊስ በሰጠው የእምነት ክሀደት ቃል ነው ለምን ድርጊቱን እንደፈፀመ ሲያስረዳም በመፅሀፉ ስለማያምንበት መሆኑን ገለልጾዋል፡፡
ፖሊስ የእምነት ክህደት ቃን ከተቀበለ በኋላ ከሌሎች ማስረጃዎች በማያያዝ በአቃቢ ሕግ ክስ እንደሚመሰረትበት አስታውቋል ፡፡
ይህንኑ ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ግለሰቡ ስራው በስራው እንዲሰናበት ደብዳቤ በዩኒቨርስቲው ሶስቱም ካምፓሶቹ ለጥፏል፡፡
ከስራ ማሰናበት ብቻም ሳይሆን ጠበቃ በማቆም በህግ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ክትትል እንደሚያደርግ መግለፁን የአካባቢው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡