በአዲስ አበባና በጅማ ከተማ በሚገኙ መስጂዶች ከፍተኛ የተክቢራ ስነ ስርዓት ማካሄዳቸው ተገለፀ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 21/2004
ለተከታታይ 11 ሳምንታት በአወሊያ ተካሂዶ በነበረው የመጅሊስን ተቃውሞ እንቅስቃሴ ለሶስት ሳምንታት መቋረጡንና ህዝቡ የመስጂዱ ሰላማዊ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል በኮሚቴዎቹ መልዕክት መተላለፉ ይታወሳል፡፡
ይህንኑ ተከትሎ ዛሬ በአንዳንድ የአዲስ አበባ መስጂዶች እና በክልል መስጂዶች መጅሊስና የአህባሽ አስተምህሮት በመቃወም የተክቢራ ሰነ-ስርዓት መካሄዱ ተገለፀ፡፡
በባዩሽ በአንሱር፣በተባረክ ፣መስጂዶች የተካሄዱ እንቅስቃሴዎች ከአዲስ አበባ መስጂዶች ይጠቀሳሉ ይህ በእንዲህ እንዳለ በኑር መስጂድና በታላቁ አንዋር የተገኙ ዱዓና የድምፃችን ይሰማ የሚል ፅሁፍ በህብረተሰቡ መበተኑን በስፍራው ወነበሩ ሪፖርተሮቻችን ዘግበዋል በተመሳሳይ በጅማ ከተማ በሚገኙ ሁሉም መስጂዶች ዛሬ በተካሄደው የጁምዐ ሰላት ስነስርዓት መጠናቀቅ በኋላ ምዕመናኑ ተክቢራ ማሰማታቸውን ከምንጮቻችን ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡