በትግራይ ክልል መሆኒ ከተማ ኢማሙ ባልታወቀ ምክኒያት ታሠሩ
ኢማሙ ትላንት የጁምዓ ሠላት ከተሰገደ በኃላ ነው ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸው፡፡
የሬዲዮ ቢላል ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት ከዛሬ 6 ዓመት በፊት በከተማዋ በሚገኘው ዋና መስጂድ መሰገድ በመከልከላችን ሣቢያ አንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ ለ4 ዓመታት በመድረሳም በመስጂድም መልክ ስንጠቀምበት ብንቆይም በየግዜው የሚመነጡት ማስፈራሪያዎች ስጋት ጥሎብናል ብለዋል፡፡ ኃላም ይህ እየሰገዳቹ ያላችሁት ቤት እውቅና የለውም በሚል እንደወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡
ኢማሙ የታሰሩበትንም ምክኒያት ሲያስረዱ እናንተ አሸባሪዎችና ዋሃቢዮቸ ናችሁ በሚል ምክኒያት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
AS WR WB be mi'irab hararge zoon kefitenya yehona islamawi gubaaee bellefew ihud tekehidowal,,ye ulama'aa komiteem mertowal.