በላሊበላ ከተማ በመንገድ ላይ ሰላት በመስገድ አንድ አመት የተፈረደበት ወጣት ይግባኝ ጠየቀ
በላሊበላ ከተማ በመንገድ ላይ ሰላት በመስገድ አንድ አመት የተፈረደበት ወጣት ይግባኝ ጠየቀ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 22/2004
የመግሪብ ሰላቱን መንገድ ዳር የካቲት 24/2004 አባ ወልደ ሰንበት ዋሻ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ላይ በመስገዱ ነው ወጣቱ የታሰረው፡፡
ገና በሰላቱ ላይ እያለሁ ከ100 ሰው በላይ ከበበኝ ከዚያም ፖሊስ መጣና ይዞኝ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደ ፡፡ ቃል ስጥ ተባልኩ ቃሌን ሰጠሁ ብሏል፡፡
የሰገድክበት ቦታ የጊዮርጊስ ክልል ነው ቢሉኝም መከለሉን ሳላውቅ መስገዴን አስረድቻለሁ በኋላም እኔ ከቤተ ክርስቲያኑ 600 ሜትር በላይ እርቀት ላይ ነው የሰገድኩት ብያለሁ ነው ያለው፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአካባቢው ነዋሪዎች በአህላል ሻሮች የተሰጠ 476 ካ.ሜ የመስጂድና 2000 ካ.ሜ የቀብር ቦታ እንደተወሰደባቸውም ከስፍራው ያገኘነው የሬዲዮ ቢላል ምንጭ ገልፀዋል፡፡
Details
Category: News In Amharic