ሽንኩርት እና ሀይላንድ ዉሀ በደረሰኝ መግዛት መግዛት ነበረባቹ << የኩታበር ወረዳ ፓሊስ

በአማራ ክልል ከደሴ ከተማ 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘዉ ኩታበር ወረዳ የፊታችን ቅዳሜ ታላቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ለማዘጋጀት የወረዳዉ ሙስሊሞች እየተዘጋጁ መሆናቸዉ ተገለፀ:: ሆኖም የኩታበር ወረዳ ሙስሊሞች ለፕሮግራሙ መሳካት ደፉ ቀና እያሉ በሚገኝበት ወቅት ለዝግጅቱ የሚሆን ሽንኩርት,ሀይላንድ ዉሀ እና እንዲሁም የተለያዩ እህሎችን ከገበያ ገዝተዉ ሲመለሱ መንገድ ላይ ፓሊስ ይዞአቸዉ የገዛችሁት ሽንኩርት,ሀይላንድ ዉሀ እና እህሉ ደረሰኝ የለዉም በማለት ፓሊስ የተገዛዉን ዕቃ በሙላ እንደያዘባቸዉ የወረዳዉ ሙስሊሞች አስታዉቁ:: የወረዳዉ ሙስሊሞች እንዳስታወቁት የገዙት ዕቃ የተያዘባቸዉ ሆን ተብሎ ፕሮግራሙን ለማጨናገፍ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ሽንኩርት በደረሰኝ መግዛት ነበረባቹ መባላቸዉ እንዳስገረማቸዉ ገልፀዎል:: በተመሳሳይም ባለፈዉ ሳምንት በደሴ ከተማበተካሄደዉ ታላቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይም የደሴ ሙስሊሞች ለፕሮግራሙ የሚሆን እንጀራ ለእንጀራ ጋጋሪዎች እንዲያዘጋጁ ቀብድ ከፍለዉ የደሴ ከተማ ፓሊስ እንጀራ ጋጋሪዎቹን በማስፈራራት እንጀራዉን እንዳይጋግሩ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የደሴ ከተማ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ይህንን ሲሰሙ በአንድነት በመሆን ለፕሮግራሙ ከሚያስፈልገዉ እንጀራ በላይ ከየቤታቸዉ በማምጣት ፕሮግራሙን ለማሰናከል የተደረገዉን ጥረት ማክሸፉቸዉ የሚታወስ ነዉ:: የኩታበር ወረዳ ሙስሊሞችን አላህ ይርዳቸዉ!!!
Be the first to comment

Related Articles

Latest Articles

Most Popular