ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለመረጣቸዉ ኮሚቴዎች ሂወቱንም አሳልፎ በመስጠት ጥላ ከለላ እንደሚሆናቸዉ ገለፀ !!
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በኮሚቴዉ ላይ ማንኛዉም አይነት ጥቃት ቢደርስ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ሊያስኬዱ የሚችሉ ተተኪ ኮሚቴዎችእንዲመርጥ ያቀረበዉ ሀሳብ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ በከፍተኛ ቁጭት ተቃዉሞ እየገጠመዉ ነዉ:: ህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎቻችንን መንካት እና ማጥቃት ሙስሊሙን በሙሉ ማጥቃት በመሆኑ አንዳች ነገር ቢደርስባቸዉ ህዝቡ በሙላ ከለላ እንደሚሆናቸዉ እየገለፀ ይገኛል:: ህዝበ ሙስሊሙ መርጧቸዉ እንጂ ምረጡን ብለዉ እንዳልሆነ እየታወቀ ኮሚቴዉን ማብጠልጠል ሙስሊሙን መናቅ መሆኑም እየተነገረገ ነዉ:: ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለመረጣቸዉ ኮሚቴዎች ሂወቱንም አሳልፎ በመስጠት ጥላ ከለላ እንደሚሆናቸዉ ነዉ እየገለፀ ያለዉ:: አዲስ ተተኪ ኮሚቴ መምረጥ ህዝቡ ለኮሚቴዉ እያሳየ ያለዉን ታዣዥነት እና መከታነት እንደሚጋርደዉ በመግለፅ ማንም አካል ኮሚቴዎቹን ቢተናኮል እስከ ሂወት ፍፃሜያቸዉ እንደሚታገሉ ነዉ እየገለፁ ያሉት :: በመሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ ለኮሚቴዎቹ ያለዉን ድጋፍና መከታነት ከመቼዉም ጊዜበላይ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት ነዉ እየተገለፀ ያለዉ::