መልካም ጥርጣሬ !!
መልካም ጥርጣሬ by Ibrahim Abdulaziz
ሰውዬው እጅግ ታታሪ የሆነ የታክሲ ሹፌር ነው ፡፡ደከመኝ ሰለችኝ ሳይል ሌት ተቀን ይሰራል፡፡ታዲያ አንድ ቀን ሚስቱ “ውዴ ሆይ ለምን ይህን ያህል ትደክማለህ፡ያለንን እያብቃቃን ብንኖር ይሻለናል፡እኔም ቢሆን ካንተ ጋር ሰፊ ጊዜ ማሳለፍ እፈልጋለሁ አለችው፡፡” “ማሬ እኔም እኮ የምለፋው እንደምንም ብዬ የራሳችን ታክሲ ለመግዛት እና ከዛም እርፍ ብለን በርካታ ጊዜያትን አብረን እንድናሳልፍ ነው፡፡”ሰውዬው መለስ፡፡ሚስትም ታዲያ “ብቻህን አትችለውም በዛ ላይ ገቢውን ታውቀዋለህ በዚ መልኩ ሰርተህ ደግሞ ታክሲ ለመግዛት ረጅም ጊዜ ይፈጅብሀል፡ስለዚህ እኔን አረብ አገር ላከኝና ጠንክሬ ስርቼ ለምን ከዛ አልክልህም ቢበዛ ሁለት አመት ቢፈጅብኝ ነው፡፡”አለችው ፡፡ሰውዬውም ከሚስቱ መለየት ቢከብደውም ነገን የተሻለ ህይወት ለመኖር አማራጭ የለምና በሀሳቧ ተስማምቶ ሌት ተቀን ለፍቶ አልበላም አልጠጣም ብሎ ያጠራቀመውን ገንዘብ አውጥቶ ላካት ታዲያ በመጨረሻ ስንብታቸው ወቅት፡ሆዴ ቃል እገባልሀለው በሁለት አመት ውስጥ ታክሲ ገዝቼ እልክልሀለው፡እስከዛው ግን በጣም ትናፍቀኛለህ ብላው ተላቅሰው ተሰነባበቱ፡፡ታዲያ ቀን ቀንን እየወለደ በዋዛ ፈዛዛ አንድ አመት አለፋ ግን በሰላም ደርሻለሁ ከሚለው የመጀመሪያ መልዕክቷ ውጭ ድምጽዋ ጠፋ ፡፡ታዲያ ይህ ሰው ቢጨንቀው አንድ አሊም ነው ብሎ የሚያሰበው ሰው ጋር ሄዶ ”ባለቤቴ ውጭ ላከኝና ስርቼ ታክሲ ልላክልህ ብላኝ ነበር ግን ይሀው አንድ አመት ሞላት በሰላም ደርሻለው ከማለት ውጪ ደውላ አታውቅም፡ምን አሰባ ይሆን ሲል ጠየቀው” ፡፡ አሊም ተብዬም “ወዳጄ እስኪ ሁሰነ ዘን(መልካም ጥርጣሬ) ይኑርህ ምንአልባት አልተመቻት ይሆናል” ሲል መለሰለት ፡፡ሰውዬውም መልሱን ተቀብሎ አዎ በሚስቴ ላይማ መልካም ጥርጣሬ ሊኖረኝ ይገባል፡ሳይመቻት ቀርቶ ነው ብሎ ተመለስ፡፡ቀናት መቼም ማቆሚያ የላቸውምና አሁን ድምጽዋ ሳይሰማ ሁለተኛው አመት ደረስ፡ታዲያ ባል ቃል የተገባለት ጊዜ ቢያልፍበት አሊም ተብዮው ጋር ዳግም መፍትሄ ፍለጋ አቀና፡አሁንም አሊም ተብዬው “ወዳጄ ሁስነ ዘን (መልካም ጥርጣሬ) ይኑርህ ምን አልባት የሰራቸው ገንዘብ ታክሲ ለመግዛት በቂ ስላልሆነ ይሆናል”;; አሉት ታዲያ ባልም ዳግም የመልካም ጥርጣሬን ሀሳብ አጽድቆ ተመለሰ፡፡ሀይ ባይ የሌለው ቀን አሁንም ነጎደና ሶስተኛው አመት ደረስ፡፡ታዲያ ባልም የመልካም ጥርጣሬ እሳቤው ላይ ጥርጣሬ ቢያድርበት ተመልሶ የእሱ አሊም ጋር ሄደ ፡ታዲያ አሊሙም “ተረጋጋ እንጂ ወዳጄ መልካም ጥርጣሬ ይኑርህ ፡ምናልባት የተሻለ ታክሲ ልትገዛልህ አስባ ይሆናል አለው”፡፡ሰውዬውም አምኖ ተመለስ፡፡ታዲያ እንደ ጅረት የሚፈሱት ቀናት አራተኛ አመት ሊሞላቸው ሲቃረብ ፡ሚስት ለባል እንዲህ ሰትል ደወለች “ሆዴ እስከዛሬ ድረስ የጠፋሁት ልንገርህ ፈርቼ ነው፡፡አሁን ግን አማራጭ የለኝም ፡እዚህ ከሌላ ሰው ልጅ ወልጃለሁ ልጁን ይዤ መስራት ስላልቻልኩ ነገ በሚመጣው አየር ልኬዋለሁ ተቀብለህ እንደልጅህ እንደምታሳድግልኝ ተስፋ አደርጋለሁ “ብላው የሱ ድምጽ ሳይሰማ ስልኩ ተዘጋ፡፡ታዲያ ሰውዬው በብስጭት አሊም ተብዬው ጋር ይሄድና ጉዳዩን ያወጋዋል፡፡አሊም ተብዬውም “ተረጋጋ ወዳጄ ሁስነ ዘን (መልካም ጥርጣሬ) ይኑርህ ምን አልባት ከታክሲው ቀድማ ረዳቱን(ወያላውን)ልካልህ ይሆናል” አለው፡፡አሁን ግን ሰውዬው መልካም ጥርጣሬ የሚይዝበት አንጀት ራቀው፡፡እኛ ሙስሊሞች ባለፉት መሪዋቻችን የጭቆና ቀንበር ተጭኖብን አጎንብስን ኖረናል፡፡በበደል ሸክም ጀርባችን ጎብጧል፡፡ታዲያ እነዛ አምባገነኖች በህዝብ ትግል ከተወገዱ በኃላ በዘመነ ኢ.ህ.አዲ.ግ. ጭቆናው መልኩን መቀየሩን እንጂ አለመወገዱን ልብ ያላልን ኢህአዲግን በበጎ የምንጠረጥር የዋሆች ቁጥራችን ቀላል አይደለም፡፡ሌላው ይቅርና የሠሞኑ እንቆቅልሽ የታሪክ ጥራዞችን የሚሞላ ሆኖ ሳለ ፡ኢ.ህ.አ.ዲ.ግ.ን በበጎ በመጠርጠር የመጀመሪያ እጃችንን የጠቆምነው ወደ መጅሊስ ነበር፡፡አሁንም ኢህአዲግ ችግራችንን ይፈታልናል በሚል በጎ ጥርጣሬ ደጃቸውን ጠንተን ፡በቀጠሮዋቸው ተመላልስን የተሰጠንንም መልስ አሁንም በበጎ በመጠርጠር የግለሰቦችና የአንድ ሚኒሰቴር መ/ቤት አቋም ነው ብለን ሳንጨርስ ፡ከጠ/ሚኒስተሩ መልሱ ቃል በቃል ተደገመልን፡፡ ለአላማው ማስፈጸሚያ ያሰቀመጣቸውን የመጅሊስ አመራሮች አስወገደልን ይህ ትልቅ ድል ነው በሚል በጎ ጥርጣሬያችን አሁንም እንደቀጠለ ነው ፡፡ለኔ ግን ኢ.ህ.አዲግ አቅጣጫውን ቀይሮ እኛን የሚበታትንበት አዲስ መንገድ አምጥቷል፡ምን አልባትም መጂሊስ ይሀው ተወገደላችሁ ከዚህ በኃላ ተቃውሞ አልቀበልም ሊል ይችላል :: እኛንም ጉዳዩ ለሁለት እንዳይከፍለን እፈራለሁ ምክኒያቱም የመጅሊስ መባረር ብቻ በቂ አድረግን አስበን ፡መጂለስ መባረሩ ብቻ በቂ አይደለም ሙስሊሙ በሚፈልጋቸው አመራሮች መተካት አለበት ከሚለው ሀሳብ ጋር እንዳንጣረስ ፍርሀቴ ነው፡፡በዛ ላይ ጉዳዩን ከተለያዩ ሚዲያዎች ሽፋን ለማሳጣትና ሙሰሊሙን ጸብ አጫሪ ለማስመስልም ይሆናል፡፡የሆነ ሆኖ በጎ ጥርጣሬያችንን አቁመን ከሚተጣጠፈው የኢህአዲግ ዕቅድ ጋር የሚተጣጠፍ ዕቅድ ከሌለን የመጨረሻው ውጤት እንደ ሰውየው ለመቀበል የከፋ መርዶ ነው የሚሆነው፡፡