Latest Articles

  • እንደ ካሮት እንደ እንቁላል ወይስ እንደ ቡና ?

    አንዲት ወጣት ወደ እናቷ ጋር መጥታ በምሬትና በብሰጭት እንዲህ አለቻት”አልቻልኩም እማ በቃኝ ነገሮች ሁሉ እኔ በምፈልገው መንገድ እየተጓዙ አይደለም፤ችግሮች ተደራረቡብኝ፡አንዱን ችግር ሳቃል ሌላ ሁለት ችግር ይወለዳል፡ሁሉም ነገር ተሰፋ የሚያሰቆርጥ ነው እናም በቃኝ”ብላ ማልቀስ ስትጀምር እናቷ እያባበለች ይዛት ወደ ኩሽና ገባች ፡፡እሰቶቩን ትለኩስና በሶስት ድስት ውሀ ትጥድበታለች፡ከዚያም ካሮት እንቁላል እና የተቆላ ቡና አምጥታ ሶሰቱ ድስት ውሰጥ ለየብቻ ትከተዋለች፡፡ከ20 ደቂቃ በኃላ ውሀው መንተክተክ ጀመረ፡እናትም እሰቶቩን አጥፍታ ከድስቱ ውሰጥ ካሮቱን እንቁላሉን እና ቡናውን አውጥታ ሰሀን ላይ አሰቀመጠቻችው፡፡ከዛም ወደ ልጇ ዞራ እስኪ ካሮተን ንኪው አለቻት ፤ልጅ ሰትነካው ካሮቱ ለስልሶ ና ተልፈስፍሷል፡ከዛም እንቁላሉን ቅርፊቱን ላጪውና እስኪ ስበሪው አለቻት፡እንቁላሉ በጣም ጠንክሯል፡ከዛም ቡናው ቅመሽው አለቻት ፤ልጅም ፈገግ አለች የቡናው ማሪኪ ሽታና ጣዕም ያውዳልና፡፡እሺ ታዲያ ምን ማለት ነው ይዄ ብላ ጠየቀች? አናትም አየሽ ልጄ እነዚህ ሶስቱ ነገሮች አንድ አይነት ችግር ነው የተጋፈጡት ፤በውሀ መቀቀል ነገር ግን ለችግሩ የመለሱት ተለያየ መልኩ ነው፡ካሮቱን እይ መጀመሪያ ደረቅና ጠንካራ ነበር ነገር ግን በውሀ ከተቀቀለ በኃላ ለስላሳና ልፍሰፍስ ሆነ ፡እንቁላሉን ደግሞ ተመልከቺ መጀመሪያ ደካማና ተሰባሪ ነበር እንደውም በውስጡ ያለው እንዳይፈስ ያደረገው ቅርፊቱ ነበር፡ነገር ግን ከተቀቀለ በኃላ ጠንካራ ከመሆኑ በላይ ቅርፊቱን ልጠነው እንኳ ውስጡ ያለው አልፈሰሰም ፡ይህ ማለት ውስጡም በችግሩ የተነሳ በጣም ጠንክሯል ማለት ነው፡ቡናውን ደግሞ ተመልከቺው ጭራሽ እኮ የውሀውን ቀለም ቀየሩት ታዲያ ልጄ አንቺ የትኛው ነሽ ?ችግር በርሽን ሲያንኳኳ በምን መልኩ ነው የምትመልሺው? ካሮት ነሽ ጠንካራ መስለሽ ችግርና መከራ ሲያጋጥምሽ የምትልፈሰፈሽ ? ወይስ እንቁላል ነሽ ችግርና መከራ የሚያጠነክርሽ? ወይስ ደግሞ እንደ ቡናው ነሽ የሚቀቅለው ቡና ውሀ የቀየረው በተቀቀለ ቁጥር ማራኪ ጣዕሙና ማዕዛ የሚወጣው?በርግጥ እንደ ቡናው ከሆንሽ ችግሩ ሲበረታ አንቺ የተሻልሽ ሁነሽ ዙሪያሽን ትቀይሪዋለሽ? ችግሮች ሲደራረቡብሽ እራሰሽን ወደ ተሻለ ደረጃ ታሸጋግሪለሸ?መከራው ሲበዛ እንደ ካሮት እንደ እንቁላል ወይስ እንደ ቡና ትሆኛለሽ? የሚል ማራኪ ምክር መከረቻት እኔም እራሴን ጠየቅኩ ችግራ መከራ ሲበዛ እንዴት ነው የምመልሰው? ስጀምር ጠንካራ መስዬ ከዛም ችግሩ ሲጠነክር የምልፈሰፈሰ፡ወይስ ችግረ ውስጤን የሚጠነክረው?አልያም ከችገሩ በልጬ ችግሩን የማሸንፍ?ትላንት አያቶቼ በእምነታቻው የተነሳ ዛሬ እኔ ላይ ይደርስ ከነበረው ችግር ና መከራ በላይ ደርሶባቸዋል ግን እነሱ አልተልፈሰፈሱም ችግሩን ልቀውት ተገኝተው መከራን ድል አድርገውት ይሀው እምነታቸውን ለኔ አስረከቡኝ ፤መከራና ችግር ያልፋል ጠንካሮች ብቻ ያልፉታል አይደል የሚባለው፡የአጼዋቹ ማሰፈራሪያና ዛቻ እስራትና ግድያ መች በገራቸው አረ እንደው እምነቴን አትንኩብኝ ብለው በነቂስ ሰልፍ ወጥተው እንደነበርስ ዘነጋሁት እንዴ? በፍጹም በፍጹም አልረሳውም እኔም እንደ አያቴ በእምነቴ ጉዳይ የሚደርስብኝ ማሰፈራሪያና ዛቻ እስራትና ግድያ ሊበግረኝ አይችልም ፡፡ልክ እንደ ቡናው ችግርን ማሸነፍ ከአያቴ ተምሬያለውና አልበገረም፡፡በእምነቴ ላይ የሚደርሰው በደል ለመጣል ሆ …ብዬ ለመጣል ፍጹም ጠንካራ መስዬ ሳበቃ አሁን ችግሩ ሲበራታ መልፈስፈ ታዲያ ምን አመጣው?እስኪ እናንተንም ልጠይቃችሁ እንደ ካሮት እንደ እንቁላል ወይስ እንደ ቡና?መልሳችሁ ምንም ይሁን እኔ ግን እንደ ቡናው እሆናለው የአላህም እርዳታ ከኔ ጋር ነውና፡፡ አላህ ሆይ የአዩብን ትዕግስትን የኑህን ጥንካሬን የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ›ወ)ጽናት ትለግሰኝ ዘንድ እማጸንሀለው Read more
  • ሙስሊሙ ምን ታስቦለት ይሆን?

    ሙስሊሙ ምን ታስቦለት ይሆን? በትላንትናው ዕለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተወካዮቻችንን ከሰዓት በኋላ ከማናገሩ በፊት ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ከመጅሊስ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጎ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጦላቸውና ለኮሚቴው የሚሰጠውን መልስም ጭምር አሳውቋቸው እንደነበር ታወቀ፡፡ በሌላ በኩል አቶ ጸጋዬ ቅዳሜ ቀን አቶ አህመዲን ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን መንግስት የሰጣቸውን የቤት ስራ ባግባቡ እንዳልተወጡ ወቀሳ ተሰንዝሮባቸው ለወደፊት እንዲያስተካክሉና መንግስት በአቶ አህመዲን ላይ ከፍተኛ መተማመን እንዳለው ማብራራቱን ከመጅሊስ አካባቢ የተገኙ ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ተጠራርገን መውጣታችን ነው ብለው ስጋት ላይ የነበሩት መጅሊሶች ከመንግስት መተማመኛ ስለተሠጣቸው በደስታ መጅሊስ ጊቢ ውስጥ አርደው መደገሳቸውን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ እንደዚሁም የመስጂድ ኢማሞቻችን በግድ ስለ አህባሽ እንዲያስተምሩ የተደረገባቸው ጫና አላንስ ብሎ አሁን ደግሞ ሙስሊሙ ጥያቄው ስለተመለሰ ለህዝቡ የእንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልእክት በግድ እንዲያስተላልፉ እየታሰበ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም የአህባሽ ስልጠና በሰፊው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ለየካቲት ወር ብቻ 12 ሚሊየን ብር በጀት ተይዞ በአምቦ በውቅሮ በሻሸመኔና ሌሎችም ቦታዎች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል የመጪውን ጁሙዓ የአወሊያ ፕሮግራም ለማሰናከል ከሰላት በፊት መድረክ መሪዎችንና የተወሰኑ የኮሚቴው አባላትን ለተወሰነ ሰዓት አግቶ ለመልቀቅ እቅድ የተያዘ በመሆኑ ሁላችንም በንቃት በመከታተል ይህ እኩይ ዐላማ እንዳይሳካ ጥረት ማድረግና ነቅተን መጠበቅ አለብን፡፡ Read more
  • Wetetu endetebeknew hone!!!! ዉጤቱ እንደጠበቅነዉ ሆነ!!!<< malet mengest tekekelegna meles yesetal belen altebqenm

    << nalet mengest mels tekekelegna meles yesetal belen altebqenm ATO MULUGETA LE FANA 98.1 BESETUT KAL MESERET 1) mejlis hizbe muslimu yemifelgachewn sewoch fthawi behone melku yememret mebt alew yihinin lemadreg mengist asfelagiwn neger liyamuala ychlal gin techemari wuyiyit yasfelgewal 2 ahbash mejlis tru new blo yametaw neger slehone begid sayhon be flagot memar tchlalachu yalfelege metew ychilal 3 awelia timhrtu meketel yichlal gin be arebgna timhrt sebeb akrarinetn mastemar aychalm ye haymanot timhrit mesetet yemichalew betemezegebu medresawoch bcha new cariculemu mestekakel alebet yemil melash setewal. mjilis mengest alewu egna allah alen tegelun eskemecheresha enqetelalen Read more
  • be adewa muslimoch bemskid selat hone quran tekelekelu gud eko newu

    የአድዋ ሙስሊሞች በመስጂዳቸው ሰላት መስገድም ሆነ ቁርኣን መቅራት ተከለከሉ አድዋ አካባቢ የሚኖሩ ሙስሊሞች በመስጂድ ውስጥ ሰላት መስገድም ሆነ ቁርኣን መቅራት አትችሉም ተብለው መታሠራችን እና በፍርድ ቤት ትህዛዝ እያንዳንዳቸው 800 ብር ተቀጥተው ከዚህ በኋላ በስፍራው መስገድም ሆነ ቁርአን መቅራት እንደማይችሉ ተነግሮአቸው መለቀቃቸውን ገለፁ፡፡ Read more
  • alimu yedin temert endayastemru tekelekelu

    አሊሙ የዲን ትምህርት እንዳያስተምሩ ታገዱ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ፊንፍኔ ወረዳ በሚገኘው ቡራዮ ኑር መስጂድ ጀመዓ አባላትን የዲን ትምህርት ሲያስተምሩ የነበሩት ዓሊም በክልሉ መጅሊስ አላግባብ መታገዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ ከስምንት ወራት በፊት ከኢማምነታቸው በክልሉ መጅሊስ አላግባብ እንዲነሱና በሌላ እንዲተኩ ከተደረገ በኋላ ሰሞኑን ደግሞ ቅሪአት እንዲያቆሙ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡ ቀደም ሲል ከኢማምነታቸው እንዲነሱ ሲደረግ የአካባቢው ጀመዓ አባላት ሠላምን በመውደዳቸው መቆየታቸውን ጠቁመዋል በአሁኑ ወቅት የአካባቢው ወጣቶች ያላቸውን የዲን እውቀት እንዲያስተላልፉ የክበቡ መጅሊስ አገዳ መጣሉ እንዳስቆጣቸው ገልጸዋል፡፡ ዓሊሙ ባቸው ተቀባይነት የቸካባቢው ህብረተሰብ በ180 ሺ ብር ወጪ የመኖሪያ ቤት እንደገዛላቸው አስታውቀዋል፡፡ ሼህ ሀሰን መሐመድ በበኩላቸው በመጅሊሱ አመራር አላግባብ ተፅዕኖ እደተደረገባቸው ይገልፃሉ፡፡ ውሃብይና አክራሪ በሚል ታርጋ ከኢማምነታቸው ካነሷው ወራት ቆይተውል፡፡ የቀበሌ አስዳደር አካላትም ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባቸው መሆኑን ተናግረዋል በጉዳዩ ዙሪያ የኦረሮሚያ መጅሊስን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም፡ Read more
  • ye alquds gazeta wana azegaje serawun leqeqe alqudsm yetesasate zena yawetal ale

    የአልቁዱስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ስራን ለቀቀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል የካቲት በማሪያ አልቅዱስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥር በየሳምንቱ ጁምዓ ለንባብ የምትበቃው የአል-ቁድስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሥራውን ማቆሙን አስታወቀ፡፡ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ አቶ መሐመድ ዳውድ ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት ሥራውን በፈቃዱ ሊለቅ የቻለው ጋዜጣው በተከታታይ እያወጣ ያለውን የተሳሳተ መረጃ በመቃወም ነው፡፡ በጋዜጣው ላይ ሲወጡ የነበሩት ዘገባዎች ሆኑ መጣጥፎች በተመለከተ ምንም አይነት እውቅና እንደሌለው የጠቀሰው የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ በስሙ ለተፈጠረው ስህተት ሕዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ ጠይቋል፡፡ በጋዜጣዋ ላይ ካለፉት 7 ወራት በላይ በዋና አዘጋጅነት ስሙ ቢጠቀስም የዋና አዘጋጅነት ሚና እዳልነበረው አቶ መሀመድ አስታውቀዋል፡፡ የአል-ቁድስ ጋዜጣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወቅታዊ የህዝበ ሙስሊሙን ጉዳዮች ላይ የተሳሳቱና ምንጫቸው በትክክል ያልተጠቀሱ ከወገንተኝነት ያልፀዱ ዘገባዎችን በተከታታይ በማውጣቱ በህዝበ ሙስሊሙ በሰፊው ሲወገዝ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ Read more
  • be alem lay yeminoru ethiopian yemuslimun teyaqe degefu

    ኢትዮጵያውያኑ የህዝበ ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እንደሚጋሩት ገለፁ፡፡
    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል የካቲት 
    በላስ ቬጋስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች በአወሊያ ተቋም ተማሪዎችና መላው 
    ሙስሊም ህብረተሰብ መብቱን ለማስከበር ሠላማዊ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ ፡፡
    በላስ ቬጋስ ነቫዳ የሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች ሰሞኑን በወቅታዊ የኢትዮጵያውያን 
    ሙስሊሞች ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያኑ ነቫዳ ላይ ፌብሩዋሪ 22 2012 አስቸኳይ 
    ስብሰባ በማካሄድ በወቅታዊ የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ውይይታቸውን ሲያጠቃልሉ 
    ባወጡት ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫም በአወሊያ ተቋም በተማሪዎችና በመላው ህዝበ ሙስሊም የተጀመረውን መብትን 
    የማስከበር ሰላማዊ ትግል እንደሚጋሩት አስታውቀዋል ፡፡የመጅሊሱ አመራር የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የተወሰነ ቡድን 
    ጥያቄ እንደሆነና የተወሰኑ የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ነው በማለት ህዝቡን ከማደናገር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል ፡፡የኢትዮጵያ እስልምና 
    ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራር አባላት የህዝቡ ተቀባይነት የሌላቸው በመሆኑ ቦታውን ለቀው በህዝበ ሙስሊሙ በሚመረጡ 
    ሕጋዊ መሪዎች እንዲተኩም አጥብቀው ጠይቀዋል ፡፡በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ሕገመንግስቱ ላይ የተቀመጠውን
    የእምነት ነፃነት በመተላለፍ በእስልምና ኃይማኖት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አጥብቀው እንደሚቃወሙ በአቋም መግለጫቸው 
    አመልክተዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች ባወጡት በዚሁ የአቋም መግለጫ በህገመንግስቱ መሰረት የኢትዮጵያ 
    ሙስሊሞች ኃይማኖታዊ ግዴታዎቻቸውን ያለ አንዳች ገደብና ተፅዕኖ በነፃነት እንዲተገብሩምጠይቀዋል ፡፡ለአብነትም የአበባበስ ፣
    በጋራ በትምህርት ተቋማት ውስጥ መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው ሲሉ ጠቅሰዋል ፡፡በቀጣይ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጀመሩትን 
    የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ በሰላማዊና በተደራጀ መልኩ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁመዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ 
    አሜሪካውያን ሙስሊሞች በአገር ቤትና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ከሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ጋር በመተባበር ከሰላማዊ ትግሉ ጎን 
    እንደሚሰለፍምአረጋግጠዋል ፡፡ለሰላማዊና ለተደራጀው ቀጣይ ትግል አመቺ ይሆን ዘንድም ልዩ ኮሚቴ አቋቁመው መንቀሳቀስ መጀመራቸውን
     ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያኑ ለሬዲዮ ቢላል ዛሬ በላኩት በዚሁ የአቋም መግለጫቸው አስታውቀዋል ፡፡
    Read more
  • A new petition has started>> a letter to prime minister meles zenawi

    A new petition has started. Please read the following pettion letter. Then click the link and sign the on line petition. (The letter is written in diplomatic way to assist the work of our committee).
    ለክቡር አቶ መለስ ዜናዊ
    የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር
    አዲስ አበባ
    አቤት ባዮች እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ስንሆን የአቤቱታችንን ፍሬ ነገር እንደሚከተለው አቅርበናል።
    በኢትዮጵያ ህዝቦች ይሁንታና ንቁ ተሳትፎ የጸደቀው የኢ.ፌዴ.ሪ ህገ-መንግስት ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት ማንጸባረቅና የአምልኮ ስርዓታቸውን ያለ አንዳች ገደብ ማከናወን እንደሚችሉ የታወጀበት የህዝቦቻችን የቃል-ኪዳን ሰነድ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት የአምልኮ ስርዓታቸውን በነጻነት ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ሙስሊሞች በሙሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወከሉበትን የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በማቋቋም ለእምነታቸውም ሆነ ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ተግባራትንም ሲፈጽሙ ኑረዋል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በሀገሪቱ ሙስሊሞች የእምነት ነጻነትና የዜግነት መብቶች ላይ ታላቅ አደጋ የደቀነ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል። ይህንን እንቅስቃሴ ፊታውራሪ ሆነው በመምራት ላይ ያሉትም ህዝበ ሙስሊሙ ባልተሳተፈበት ሁኔታ ተመራርጠው የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በሞኖፖል የተቆጣጠሩት ጥቂት የአመራር አካላት ናቸው።
    እነኝህ ግለሰቦች ከሀይማኖታዊ አባት በማይጠበቅ መልኩ በቡድንተኝነት ስሜት እርስ በራሳቸው ሲጠቃቀሙና ሌሎችን እያሳደዱ ሲያጠቁት ከርመዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለሀገራችን ሙስሊሞች ባዳ የሆነውና “አል-አሕባሽ” የሚባለው የእምነት አንጃ የሚያራምደውን ርዕዮት እንድንከተል ለማድረግ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። ህዝበ ሙስሊሙ በማያውቀው መድረክ በወሰኑት ውሳኔ የሀገራችንን መስጊዶችና መድረሳዎች በጠቅላላ በዚህ አንጃ ተከታዮች ቁጥጥር ስር ለማስገባት ሰፊ ዘመቻ እየተካሄደ ነው።። የነርሱን ህገ-ወጥ አካሄድ የማይቀበሉትን በሙሉ በጽንፈኝት በመፈረጅ የጥቃት በትራቸውን ያሳርፉበታል። ለዚህ እንዲያመቻቸው በማሰብም “ወሀቢያ” እና “ኸዋሪጃ” ለተሰኙ አደናጋሪ ቃላት ያሻቸውን ትርጉም እየሰጡ በጨዋነትና በመቻቻል ባህላቸው ዓይነተኛ ተጠቃሽ የሆኑትን የሀገራችንን ሙስሊሞች በአደባባይ በአክራሪነት ፈርጀዋል። በቅርበት ለሚያውቋቸው የመንግስት ባለስልጣናት የሀሰት መረጃዎችን በመስጠት በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲዎች በሚማሩ ሙስሊም ወጣቶች ላይ ልዩ ልዩ እቀባዎች እንዲጣሉ አድርገዋል። በዚህም ወጣቶቻችን አምልኮአቸውን በነጻነት እንዳያካሂዱ ከፍተኛ ችግር ተፈጥሯል።
    ክቡር ሆይ!
    የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራር አካላት የሚያካሄዱትንና አድማሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማስፋት ላይ ያለውን ይህንን ህገ-ወጥ ዘመቻ በጭምምታም ቢሆን ያውቃታል ብለን እንገምታለን። ሆኖም ከታች ካሉት የመንግስት መዋቅሮች ጋር በመወያየት ችግራችንን ልንፈታው እንችላለን በሚል ተስፋና እምነት ጉዳዩን ወደርስዎ ከማምጣት ተቆጥበን ቆይተናል። በተጨማሪም በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ የህዝበ ሙስሊሙን ሙሉ የእምነት መብት በይፋ በመቀበል ብቸኛ በሆነው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስትና በሙስሊም ዜጎቹ መካከል ጸንቶ ያለውን ወዳጅነት ለመሸርሸር የሚፈልጉ ሀይሎች ነገሩን እያራገቡ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሊነዙበት ይችላሉ በሚል ፍራቻ ወደርስዎ አላቀረብነውም። ይሁንና ከታች ያሉት የመንግስት አካላት እንደተመኘነው ችግራችንን ሊፈቱልን አልቻሉም። ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ደግሞ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት አመራሮች የአወሊያ እስላማዊ ኮሌጅን የመሳሰሉ የእምነት ተቋሞቻችንን እራሳቸው ባመጡት አዲስ አንጃ ስር ለማስገባት የሚያደርጉት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ህሊናችንን እረፍት ነስቶታል። ስለሆነም ለችግራችን አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠን ለመጠየቅ አቤቱታችንን ለርስዎ ማቅረቡ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኖ አግኝተነዋል። በዚሁ መሰረት ክቡርነትዎ ካለዎት ህገ-መንግስታዊ ሃላፊነት በመነሳት ጉዳዩን አይተው
    1. የም/ቤቱ አመራሮች ለ“አል-አሕባሽ” አንጃ በመወገን ሙስሊሙ በጠቅላላ የአንጃው ተከታይ እንዲሆን ለማድረግ በሚል የሚያካሄዱትን ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ እንዲያቆሙልን
    2. የም/ቤቱ አመራሮችና ተከታዮቻቸው በወሰዷቸው ህገ-ወጥ እርምጃዎች ከስራ ገበታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በአፋጣኝ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ፣
    3. በም/ቤቱ አመራሮች የተዘጉት የአወሊያ እስላማዊ ኮሌጅና ሌሎች እስላማዊ ተቋማት ተከፍተው መደበኛ ስራቸውን እንዲጀምሩ
    4. የም/ቤቱ አመራር አባላት ምርጫ የሁሉንም ሙስሊሞች ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ በአስቸኳይ እንዲካሄድ
    5. የም/ቤቱ አመራር አካላት በተለያዩ መድረኮች ሲሰጧቸው ለነበሩት የተሳሳቱ መግለጫዎች ሙስሊሙን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ
    የሚያዝ ቀጥተኛ አመራር እንዲሰጡልን፣ ይህንን ማድረጉ አስቸጋሪ ከሆነ ግን በህገ-መንግስቱ በተሰጠን መብት መሰረት ከ“አል- አሕባሽ” ጋር አንድ አይነት ርዕዮትና የእምነት ፍልስፍና የማንከተለው ብዙሀኑ ሙስሊሞች የምንሰባሰብበት አዲስ ምክር ቤት ለመመስረት እንድንችል ፈቃድ እንዲሰጠን በአክብሮት እንጠይቃለን።
    ከሰላምታ ጋር
    http://www.change.org/petitions/prime-minister-of-the-federal-democratic-republic-of-ethiopia-hear-the-voices-of-ethiopian-muslims


    Read more
  • Earliest Known Chinese Translation Of The Qur’an Discovered

    Earliest Known Chinese Translation of the QurMuslim culture researchers in China’s northwestern Gansu province said they have found the earliest Chinese version of the Qur’an, a handwritten copy completed in 1912.

    Before the 1912 version was found, experts believed the earliest complete Chinese version of the Qur’an was the one produced and published in Beijing in 1927.

    The newly discovered manuscript translation, found among old archives by researchers with the Muslim Culture Institute of Lanzhou University, is believed to have been translated into Chinese by Sha Zhong and Ma Fulu, two noted imams and Arabic calligraphers in Lanzhou, said Ding Shiren, head of the institute.

    Sha and Ma began translating the Qur’an in 1909 and completed their work in 1912, Ding said.

    Sha then copied out the Chinese text and made three handwritten books, which were widely used in Lanzhou.

    Ding said two other Chinese versions of the Koran were finished in Gansu in the 20th century.

    Ding and his colleagues are still making a comparative study of the three versions.

    He said the translation by Sha and Ma is faithful to the Arabic version, though parts of the Chinese text used Lanzhou dialect.

    Experts say Islam was introduced to China in the Tang Dynasty (618-907). But early Chinese Muslim scholars did not translate the Koran, out of fear they might misinterpret its text, Ding said

    Read more

Latest Articles

Most Popular