Latest Articles

  • በአዲስ አበባና በጅማ ከተማ በሚገኙ መስጂዶች ከፍተኛ የተክቢራ ስነ ስርዓት ማካሄዳቸው ተገለፀ

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 21/2004 ለተከታታይ 11 ሳምንታት በአወሊያ ተካሂዶ በነበረው የመጅሊስን ተቃውሞ እንቅስቃሴ ለሶስት ሳምንታት መቋረጡንና ህዝቡ የመስጂዱ ሰላማዊ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል በኮሚቴዎቹ መልዕክት መተላለፉ ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ዛሬ በአንዳንድ የአዲስ አበባ መስጂዶች እና በክልል መስጂዶች መጅሊስና የአህባሽ አስተምህሮት በመቃወም የተክቢራ ሰነ-ስርዓት መካሄዱ ተገለፀ፡፡ በባዩሽ በአንሱር፣በተባረክ ፣መስጂዶች የተካሄዱ እንቅስቃሴዎች ከአዲስ አበባ መስጂዶች ይጠቀሳሉ ይህ በእንዲህ እንዳለ በኑር መስጂድና በታላቁ አንዋር የተገኙ ዱዓና የድምፃችን ይሰማ የሚል ፅሁፍ በህብረተሰቡ መበተኑን በስፍራው ወነበሩ ሪፖርተሮቻችን ዘግበዋል በተመሳሳይ በጅማ ከተማ በሚገኙ ሁሉም መስጂዶች ዛሬ በተካሄደው የጁምዐ ሰላት ስነስርዓት መጠናቀቅ በኋላ ምዕመናኑ ተክቢራ ማሰማታቸውን ከምንጮቻችን ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡ Read more
  • በሐረሪ ክልል አዲሰ የዑለሞች ምክር ቤት ተቋቋመ የምክር ቤቱ ክንፍ ሆኖ የሚሰራ የፈትዋ ዳዕዋ ኮሚቴም ተደራጅቷል፡፡

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 21/2004 በሐረር ክልል ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እንዲሁም ከሐረር ከተማ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ ዑለሞች የራሳቸውን የዑለሞች ምክር ቤት አቋቋሙ ካቋቋሙት ምክር ቤት በተጓዳኝ የፈትዋ ዳዕዋ ኮሚቴ አደራጅተዋል፡፡ አዲስ የተቋቋመው የሐረር ክልል ዑለሞች ምክር ቤት አባል ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት ምክር ቤቱን በክልል በዞንና በወዳ ደረጃ ማቋቋም ያስፈለገው የቀድሞው መጅሊስ አመራር አባላት በክልሉ ሕዝበ ሙስሊም እውቅና የተነፈጋቸው በመሆኑ ነው፡፡ ነባሩ መጅሊስ አመራር በክልሉ ህዝብ እውቅና የተነፈገው በመሆኑም ህብረተሰቡ ኢስላማዊ አገልግሎት የሚሰጥ የተደራጀ አካል በማስፈለጉ የዑለሞች ምክር ቤት ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስረፍተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የምዕራብ ሀረርጌ ወረዳዎችን የሚወክሉ አባላት ያሉት ሐረርጌ ወረዳዎችና ከሐረር ከተማ የተውጣጡ 20 አባላት ያሉት የዑለሞች ምክር ቤት መቋቋማቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከሁለቱም ዞኖችና ዳዕዋ ኮሚቴዎች የዑለሞች ምክር ቤቶች ጋር በጥምረት የሚሰሩ የፈትዋና ዳዕዋ ኮሚቴዎች መደራጀታቸውንም የዑለሞች ምክር ቤቱ አባል አስረድተዋ፡፡ የዑለሞች ምክር ቡቱ ነበሩ መጅሊስ ያተወጣቸውን ኃላፊነቶች ለመወጣት የሚያሻሽሉት ዝርዝር የሥራ ኋላፊነት እንደሚኖር ተናግረዋል ፡፡ መድረሳ የማቋቋም ዳዕዋ የማካሄድ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት የማጠናከር ፣በሀገራዊ ጉዳቶች ተሳትፎ እንዲያደርግ የማበረታቻ ፣ፀረ ኢስላም አቋሞችንና አመለካከቶችን የመታገል ኃለፊነቶች እንደሚኖሩት አብራርተዋ፡፡ በተመሳሳይ የፈትዋና የዳዕዋ ኮሚቴው ማብራሪያ በሚፈለጉ ጉዳዮች ላይ ከሸሪኸው አንፃር ማብራሪያ የመስጠትና የዳዕዋና ኹጥባ ፕሮግራሞችን የማስተባበር ኃላፊነት እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ የዑለሞች ምክር ቤቶች አባላት በህዝብ ሠፊ ተቀባይነት ያላቸው ዑለሞች ፣የመስጂድ ኢማሞች የአገር ሽማግሌዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የሁለቱ ዞን ዑለሞች ምክር ቤት በክልል ደረጃ ሃጂ ቀመር አብዱላሂ የፈትዋና የዳዕዋ ኮሚቴውን ደግሞ ሸህ ጀማል ሰኢድ በሊቀመንበርነት እንደሚመሩት ለማወቅ ተችሏል፡፡ Read more
  • በዛሬዉ ጁምአ በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ መስጂዶች በተክቢራ ደምቀዉ ዉለዎል

    በዛሬዉ ጁምአ በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ መስጂዶች በተክቢራ ደምቀዉ ዉለዎል:: በቄራ ሰላም መስጂድ በመካኒሳ መስጂድ, በመገናኛ መስጂድ በቶፊቅ መስጂድ በአየር ጤና አንሷር መስጂድ, በባዩሽ መስጂድ በፈትህ መስጅድ , በሼህ ሆጀሌ መስጅድ እንዲሁም በሌላ በርካታ መስጂዶች ህዝበ ሙስሊሙ ተቃዉሞዉን በተክቢራ መግለፁን በየመስጂዱ የተገኙ ምንጮች ገልፀዎል:: በተመሳሳይም ሁኔታ ከአዲስ አበባ ዉጪ በጅማ ከተማ የሚገኙ መስጂዶችም በተቃዉሞ ተክቢራ ደምቀዉ መዎላቸዉን የአካባቢዉ ምንጮች አስታዉቀዎል::በሁሉም ክልሎች የሚገኘዉ ህዝበ ሙስሊም ይህንን ሰላማዊ ተቃዉሞ በየሳምንቱ ጁምአ በተክቢራ መግለፃቸዉን አጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ ተገልፆል:http://www.facebook.com/DimtsachinYisema?refid=46&m_sess=soCrvWs6-fekD_z6N Read more
  • የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ በአንዋር እና በኑር መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙን እንዳልጠራ አረጋገጠ

    የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ በአንዋር እና በኑር መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙን እንዳልጠራ አረጋገጠ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 20/2004 የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ነገ ጁምዓ አንዋር መስጂድና በኑር መስጂዶች ሙስሊሙን እንደጠራ ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ የተሳሳተ መሆኑ ተገለፀ፡፡ መሀል አዲስ አበባ ዛሬ በስፋት እየተወራ የሚገኘው ይህ መረጃ ከኮሚቴው አባላት እንዳልተላለፈ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለሬዲዮ ቢላል አስታውቀዋል፡፡ ይሁንና ነገ ጁምዐ ህብረተሰቡ በየአካባቢው ባሉመስጂዶች የሚያደርገው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ካለ ሂደቱ ሠላማዊ ሊሆን እንደሚገባው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ህብረተሰቡ ሰላሙን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ያሉት ዑስታዝ አቡበከር አህመድ በየአካባቢው የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሠላማዊ መሠረትና መስመራቸውን የጠበቁ እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡ Read more
  • በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቁርዓን ሽንት ቤት የተጠቀመው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

    አሰላምዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቁርዓን ሽንት ቤት የተጠቀመው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ ጉዳዩ እንዲህ ነው ከዛሬ 21 ቀናት በፊት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ አንባ ግቢ ጧት ሙስሊም ተማሪዎች ለሱብሂ ሰላት ሲንሱ ሽንት ቤት ውስጥ የቁረዓን ቅዳጆች በአይነምድር ተለውሰው ያገኛሉ፡፡ነግሩን በሚስጥር በመያዝ ጉዳዩን ለማጣራት ሥራቸውን ይጀምራሉ፡፡ክትትል ቢያደርጉም ምንም መረጃ አላገኙም፡፡ሁኔታውን በሚስጥር ቢይዙትም ከሶስት ቀን በኋላ ነገሩ ተደገመ፡፡አሁንም ግራ ተጋቡ፡፡አሁንም ከሶስት ቀን በኋላ ተደገመ፡፡ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ቢደርስም ተማሪዎቹ ስልት ቀየሱ፡፡ጉዳዩ የሚፈጸመው ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት በኋላ መሆኑን መረዳት በመቻላቸው ጥበቃቸውን አጠናክረው ቀጠሉ፡፡ ሰውየው ለአራተኛ ጊዜ ለመፈጸም እንደሚመጣ እርግጠኞች ስለነበሩ ሌሊቱን ዋርድያ ሆነው ማደር ጀመሩ፡፡ከአራት ቀናት ጥበቃ በኋላ በግምት 9፡45 አካባቢ አንድ አዲስ ፊት ከወደበር ብቅ አለ፡፡ሙስሊም ተማሪዎችም ጥግ ጥጋቸውን ይዘው ከታተሉት ጀመር፡፡ሰውየው ወደ ሽንት ቤቱ ቀጥ ብሎ ሲገባ ክትትሉን ቀጠሉ፡፡ከሽንት ቤት እስኪወጣ ድረስ በትግስት ከጠበቁት በኋላ ሰውየው ሲወጣ ተከታትለው ወደ ሽንት በቤት ሲገቡ የቁርዓን ቅዳጅ ያገኛሉ፡፡ተማሪዎችም የሰውየውን አድራሻ ለማወቅ ተከትለውት ነጎዱ፡፡ሰውየው ቀጥ ብሎ እዚያው አካባቢ ወዳለ አንድ ቤት ዘው ብሎ ይገባል፡፡ተማሪዎቹም የሰውየውን ማንነት ለማወቅ እዚያው አካባቢ ተቀምጠው አነጉ፡፡ሰውየው ሽንት የያዘ ፖፖ አውጥቶ ሲደፋ በማየታቸው የሰውየው ቤት መሆኑን ያረዳግጣሉ፡፡የሰውየውን ማንነት ለማወቅ ክትትላቸውን ቀጠሉ፡፡ሰውየው ልጁን ትምህርት ቤት ለማድረስ ሲሄድ ተከታተሉት፡፡ሰውየው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቴወድሮስ ካምፓስ ፕሮክተር መሆኑን አረጋገጡ፡፡ ተማሪዎቹ ውይይታቸውን ቀጠሉ፡፡ጉዳዩ ለዩኒቭረሲቲው ፕረዚደንት እንዲቀርብና እልባት እንዲገኝ ሀሳብ ቢቀርብም ሁኔታውን በትግስት መከታተልና ድርጊቱን የሚፈጽመውን ግለሰብ መያዝና ለፍርድ ማቅረብ እንደሚገባ ነገር ግን መጀመሪያ ሚስጥሩ ከወጣ ሰውየው ከድርጊቱ ሊቆጠብና ጉዳዩ ተደፋፍኖ ሊቀር ይችላል የሚለው ሀሳብ ገዢ ሆኖ የተገኘ በመሆኑ ጉዳዩን በትግስት መጠበቅ ጀመሩ፡፡ዱዓውም ቀጠለ፡፡ሚስጥሩ ጎንደር ከተማን ቀስ በቀስ ማዳረስ ጀመረ፡፡ሁሉም ዱዓውን ቀጠለ፡፡ታዲያ በ18 /07/04 ምሸት ላይ ሰውየው እንደለመደው ድርጊቱን ለመፈጸም እንደመጣ የጠረጠሩት ተማሪዎች ሰውየውን በቪዲዮ ለመቅረጽ ዝግጅታቸውን አጠናቀው መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ ድርጊት ፈጻሚው እንደለመደው ድርጊቱን ሲፈጽም ቀረጹት፡፡ለመውጣት ቢሞክርም እጅ ከፍንጅ እንዲያዝ ተደረገ፡፡ አላሁ አክበር! የዛሬውን ውሎ ነገ አቀርባለሁ ሙስሊም ወንድማችሁ ነኝ ከጎንደር Read more
  • warning !!! warning !!! ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!!

    ምጻችን ይሰማ ►►ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!! ሙስሊሞች ሆይንቁ!!►► ሰላማዊ የመብት ትግላችንን አሁንም የቀጠልን ብንሆንም ብዙ ስራ እንደሚጠበቅብን ግልፅ ሆኗል፡፡ መጅሊስና አጋሮቹ አሁንም አልተኙልንም፡፡ አሁን በሚገኙት የመጅሊስ አመራር አባላት ተስፋ የቆረጠው ፌዴራል ጉዳዮች ምርጫ አይቀሬ መሆኑን ተረድቶ ሁሉንም ሊያባርራቸው ወስኗል፡፡ ነገር ግን ምርጫውን አሁንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ!!! ምርጫውን የሚያስፈጽም ‹‹ገለልተኛ›› ሰው ስላስፈለጋቸው ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይህንንም ለማሳካት የአህባሽ ስልጠና እንደገና ሊሰጡ ሲሆን ኦሮሚያ፣ ደቡብ ክልል፣ አማራ ክልልና አሁን ደግሞ በወሰኑት መሠረት በአዲስ አበባ በአጠቃላይ 15 ሺህ ሰው ያህል ለማሰልጠን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ አዲስ አበባን ሳይጨምር በክልሎቹ ለሥልጠና የተመረጡት 16 ያህል ቦታዎች ናቸው፡፡ ስልጠናው ላይ አህባሽ ላይ ለቀረቡት ውንጀላዎች ‹‹ምላሽ›› የሚሰጡ ሲሆን ስልጠናውን የሚወስዱት የመስጊድ ኢማሞችና ዱአቶች ናቸው፡፡ የአህባሽ ደጋፊ እንዲሆኑና ምርጫውን እንዲቆጣጠሩለት፣ ‹‹ወሃቢያ›› እንዳይመረጥ እንዲከላከሉለት ፌዴራል ጉዳዮች ቋምጧል!!! (መብቴን ያለ ሁሉ ለነሱ ወሃቢያ ነው!!!) በጀቱ በሙሉ በፌደራል ጉዳዮች ነው የሚሸፈነው፡፡ ታይም ቴብሉንም ሁሉ አውጥቶ ለመጅሊስ የላከው ፌዴራል ጉዳዮች ነው!!! ስልጠናውንም ሊጀምሩ ያሰቡበትን ጊዜ በማራዘም ሚያዝያ 10 እና 11 ሊጀምሩት ወስነዋል፡፡ በምርጫው በ‹‹ሱፊ›› እና ‹‹ወሃቢያ›› መካከል ቡድን ለመፍጠርና ክፍፍል ለመፍጠር ፈልገዋል!!! አላህ ስንት ተንኮላቸውን አፈረሰባቸው??? መቼ ይሆን ልብ የሚገዙት??? በክልሎች መጅሊስ ጠቅላይ ጉባኤ እየተካሄደ ሲሆን ትናንት በባህርዳር መስጊድ አስመርቀው ከፍተው ዛሬ ሲወያዩ ውለዋል፡፡ ስትራቴጂያቸውን ሲነድፉም ቆይተዋል፡፡ ኢህአዴግ አባላቱን ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያየ ቦታ ሰብስቦ ሲያወያይ የቆየ ሲሆን በበርካታ ቦታዎች ከአባላቱ ተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲቀርብበት ነበር፡፡ ነገር ግን በማስፈራራት እና እንቅስቃሴው የወሃቢይ አክራሪያን እንደሆነ በመናገር አንዳንድ አባላቱን ለማሸማቀቅ ‹‹ከሁለት አንዱን ምረጡ!›› እያለ ሲያስፈራራ ነበር፡፡ ጥናት ተብዬ ወረቀትም አቅርበዋል!!! በተለያዩ ቦታዎች የመጠይቅ ወረቀት (ኩዌሽነር) የበተኑ ሲሆን መንግስት ጣልቃ ገብቷል ወይ በሚል ለቀረበው ጥያቄ 99 በመቶው ‹‹አዎ! ጣልቃ ገብቷል!›› የሚል መልስ እንደሰጣቸውም ታውቋል!!! ግን እነሱ እውነት መስማት አይፈልጉም!! በተጨማሪም ከየቀበሌው 15 ሰዎችን ለምርጫው መልምለው ጨርሰዋል፡፡ የነሱ ፍላጎት ምርጫውን በቀበሌ አድርገው የሚፈልጉትን ሰው በገፍ ሊያሰርጉ ነው!!! እኛ ደግሞ መንፈሳዊ ማእከላችን መስጊድ እንጂ ቀበሌ ስላልሆነ ይህንን በፍጹም መቀበል የለብንም!!! መልካም የአላህ ባሪያዎች እና ታማኝ ሰዎቻችን የሚገኙት በመስጊድ ነውና ምርጫ በቀበሌ ምልመላ እንዳይሆንና ይህን መሰሉን ሸፍጥ እና መንግስታዊ ጣልቃ ገብነት ካሁኑ ለመከላከል ቁርጠኝነት ያሻናል!!! ፌዴራል ጉዳዮች ይህንኑ የሸፍጥ ስራውን በመቀጠል ለአውሮፓ ህብረት እና ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት ያስገባ ሲሆን በሪፖርቱም አገራችን ውስጥ በእምነት ግጭት ምክንያት የተቃጠሉ ቤተ ክርስቲያናትን እና ሌሎች የተከሰቱ ግጭቶችን በመዘርዘር ‹‹ሁሉንም ያደረጉት እነዚሁ ወሃቢዮች ናቸው፡፡ አሁን ዋና መናኸሪያቸው አወሊያ ሲመታባቸው ነው መብታችን ተጣሰ እያሉ የሚረብሹት፡፡ አሁን ግን እርምጃ ልንወስድባቸው ስለሆነ ሰብአዊ መብት ጣስክ ብላችሁ እንዳትረብሹኝ›› ሲሉ አቅርበዋል!!! ተመልከቱ ምን ያህል ለእስልምና ያላቸው ጥላቻ አይን ያወጣ ውሸት ውስጥ እንደጨመራቸው!!! ሰላማዊ ዜጎቻቸውን ለማጥቃት እና ህገመንግስታዊ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ የጠየቁ ሰዎችን በአክራሪነትና በውሸት በመወንጀል የፈለጉትን ለማድረግ አረንጓዴ መብራት እንዲበራላቸው ውጭ ሃገር ይለማመጣሉ!!! ተመልከቱ ፌደራል ጉዳዮች እየሰራ ያለውን! አንድ ሺ አንድ ሴራቸውን እስካሁን የመለሰባቸው አላህ አሁንም ይመልስባቸዋል እንጂ እንደነሱ ቢሆንማ ሰማይ በታረሰ ነበር!!! አላሁ አክበር! አላህን የያዘ አይወድቅም!!! ወደአላህ እያለቀስን የቻልነውን ልፋት እና ስራ ሁሉ ማከናወን፣ ለዲናችን ዘብ መቆም አለብን!!! አላሁ አክበር!!! ከዚሁ ምርጫ ጋር በተያያዘ ፌደራል ጉዳዮች አራት ሰዎችን በፌደራል ደረጃ ታዛቢና ተቆጣጣሪ እንዲሆኑለት መርጧል፡፡ እነዚህም አራት ሰዎች የሀጂ ሳኒ ልጅ የሆኑት ሃጂ መሃመድ ኑር፣ ግራዝማች ሀዲስ ኑርሁሴን፣ ኢንጅነር ተማምና ሀጂ ፈድሉ ይባላሉ፡፡ (ግራዝማች ሃዲስ በ1987 ግርግር ዋነኛ ተዋናይ የነበሩና መጅሊስ የአወሊያውን ተቃውሞ እንዲያደበዝዙ የፈበረከው የሽማግሌ ቡድን አባል ናቸው!) ልብ እናድርግ ሙስሊሞች ሆይ! አስመራጭ ኮሚቴውን የሚመርጠው ፌደራል ጉዳዮችም ሆነ አሁን ያለው መጅሊስ አይደለም!!! የመምረጥ መብቱ የህዝበ ሙስሊሙ ነው! በመሆኑም እኛ ከምንመርጠው ውጪ የፈለገ ጥሩ የሚመስል ወይም የሆነ ሰው ቢመጣ በፍጹም አንቀበልም!!! ይህንን በፍጹም እንዳንረሳ!!!! ሰዎቹ ጥሩ ቢሆኑም እንኳ የምንመርጠው እኛ እንጂ መነግስት አይደለም፡፡ ስለዚህ ካሁኑ ለሌሎች በማሳወቅ ምርጫችንን ከጣልቃ ገብነት መከላከል አለብን!!! አላሁ አክበር!!! ከሐጅ ጋር በተያያዘ ሌላ ጉድ አለላችሁ! ፌደራል መጅሊሶች በሐጅ ጉዳይ ለመደራደርና ለመፈራረም ወደሳኡዲ ሊሄዱ ነው! ለጉዞው የሚሄዱት አራት ሰዎች ሲሆኑ አህመዲን አብዱላሂ፣ አዛም እና የሐጅ አስፈጻሚው አቶ አማን ሁሴን ይገኙበታል፡፡ እዚያ መሀመድኑር የሚባል ኢትዮጵያዊ ነው እስከዛሬ ሙስናውን፣ የቤት ኪራዩን ሁሉ ሲያመቻችላቸው የቆየው፡፡ ይህ ሰውዬ ለራሱም 6 አባዱላ ሚኒባስ ያለው ሀብታም ነው፡፡ የሃጅ ሙስና ዋና አመቻች እሱ ነው፡፡ ሳኡዲ ውስጥ ተቃውሞ ይገጥመናል ብለው ስለፈሩ ሙፍቲ ሃጂ ኡመርን ይዘው ሊሄዱ ነው ያሰቡት፡፡ እሳቸው ይስማሙ አይስማሙ ቁርጡን ያወቅኩት ነገር ባይኖርም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚገኘው የአራቱም ሰዎች ፓስፖርት ግን ባለፈው ጁሙኣ ቪዛ ተመቶበታል፡፡ (የሁሉም መጅሊስ አመራር አባላት ፓስፖርት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው የሚቀመጠው!) ጉዞውም አፕል ሶስት ነው፡፡ ያሳዝናል! ሊባረሩ ጥቂት ጊዜ ቀርቷቸውም እንኳን ከሌብነታቸው መቆጠብ አይፈልጉም!!! አላሁ አክበር! ምን አይነት የብር ፍቅር ነው የያዛቸው???!!! ሙስሊም ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ! እስቲ እናስተውል… እኛ አወሊያ ተሰብስበን መፈክር ስላሰማን ብቻ ብዙ የሰራን መስሎን እንረካለን፡፡ አልሀምዱሊላህ አላህ አጅራችንን ያበዛዋል፡፡ ሙስሊሞችን ጠምዶ የያዘው ዶክተር ሽፈራውና ድርጅቱ ግን በርካታ ስራ በሚሊዮን ብር በጀት እየሰራ ነው!!! እኛ በጥቂት ነገር ስንረካ እነሱ ግን ወስጥ ለውስጥ ብዙ ድንጋይ ይፈነቅላሉ፡፡ አላህ እንደ የእጁጅና መእጁጅ ቁፋሮ መና እያደረገባቸው እንጂ!!! አሁንም ቢሆን ብዙ ስራ ይጠበቅብናል፡፡ ገና አስቸጋሪውን ትግል እየጀመርነው ነው! ተስፋ በፍጹም አንቆርጥም!!! እስከመጨረሻው አላህ ያደርሰናል… እስካሁንስ እዚህ የደረስነው በአላህ ፕሮግራም እንጂ መች በእኛ ልፋት ሆነና!!! ከምንጊዜውም በበለጠ ምርጫውን ለመጠምዘዝ የሚካሄዱትን ሸፍጦች ለመቃወም እና ሁሌም በሰላማዊና በሰላማዊ መንገድ ብቻ መብታችንን ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆን አለብን!!! እኔ ይኸው ለእናንተ መረጃውን በማድረስ ሃላፊነቴን ተወጥቻለሁ! ሁላችሁም ይህን ፅሁፍ ታግ እና ሼር በማድረግ፣ ፕሪንት አድርጎ በፎቶኮፒ ለሰዎች በማዳረስ በትእግስት ሃላፊነታችሁን ተወጡ!!! ‹‹አላህ ከትእግስተኞች ጋር ነውና!›› ‹‹የአላህን ሃይማኖት ብትረዱ አላህም ይረዳችኋል፡፡›› ቅዱስ ቁርአን Read more
  • yemuslimu tegele beyemeskidu endeqetele tenegere Allahu akber

    በአወሊያ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊሙ ህብረተሰብ የመብት ጥያቄ በመስጂዶችም ቀጥሏል አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት17/2004 ለተከታታይ 11 ሳምንት በአወሊያ ሲካሄ የነበረው በአሁኑም ወቅት በከተማዋ ባ ሌሎች መስጂዶች መጀመሩን በየመስጂዱ የሚገኙ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ታቃውሞው እየተገለፀያለው በተክቢራ ሲሆን እንቅስቃሴው ከተጀመረባቸው መስጂዶች መካከል የአንዋር የቄራ እንደሚጠቀሱ ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ የመፍትሄ አፈላላጊው ኮሚቴው ባለፈው ጁምዓ ከአወሊያ ኢስላማዊ ማዕከል ለተገኘው ሕዝብ ሙስሊም በየአካባቢው በሚገኙ መስጂዶች ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን መቀጠል እንደሚችል ጠቅሶ ነበር፡፡ ኮሚቴው በቀጣይ ሶስት ሳምንታት ጅምር እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ በመቀጠል የደረሰበትን ለህዝበ ሙሊሙ እንደሚያሳውቅ ቃል መግባቱ አይዘነጋም ፡፡ የህን ተከትሎ ባፈው ጁምዓ ቅዳሜ በርካታ ምዕመናን በየአቅራቢያቸው በሚገኙ መስጂዶች የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጣቸው በተክቢራ ጠይቀዋል፡፡ Read more
  • be tegray Imamu yale mekniyat taseru

    በትግራይ ክልል መሆኒ ከተማ ኢማሙ ባልታወቀ ምክኒያት ታሠሩ ኢማሙ ትላንት የጁምዓ ሠላት ከተሰገደ በኃላ ነው ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸው፡፡ የሬዲዮ ቢላል ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት ከዛሬ 6 ዓመት በፊት በከተማዋ በሚገኘው ዋና መስጂድ መሰገድ በመከልከላችን ሣቢያ አንድ ባለሀብት ቤት ውስጥ ለ4 ዓመታት በመድረሳም በመስጂድም መልክ ስንጠቀምበት ብንቆይም በየግዜው የሚመነጡት ማስፈራሪያዎች ስጋት ጥሎብናል ብለዋል፡፡ ኃላም ይህ እየሰገዳቹ ያላችሁት ቤት እውቅና የለውም በሚል እንደወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ኢማሙ የታሰሩበትንም ምክኒያት ሲያስረዱ እናንተ አሸባሪዎችና ዋሃቢዮቸ ናችሁ በሚል ምክኒያት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ Read more
  • mjlish tegelun lemebeten gebre hayl eyaquwaqeme newu

    መጅሊስ ሠላማዊ ትግሉን ለመበተን ግብረኃይል እያቋቋም ነው አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 8/2004 የሚካሄደውን የሕዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል ለመበተን የሚያስችለውን ግብረ ኃይል እያደራጀ መሆኑ ተገለፀ፡፡ መጅሊሱ ዛሬ ጦርኃይሎች በሚገኘው ቅጥር ግቢው ከመዲናዋ የተለያዩ መስጂዶች ኢማሞች ጋር ባካሄደው ውይይት እንዳስታወቀው እየተጠናከረ የመጣውን የሕዝቡን ተቃውሞ ለመበተን የሚየስችል እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ባውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የተለያዩ ኢማሞችና ዱዓቶች ሥራ መሰራቱን ለሬዲዮ ቢላል አስታውቀዋል፡፡ ለደህንነታችን እንደሰጋለን ያሉ አስተያየት ሰጪዎቻችን እንዲገልፁት የመጅሊሱን እንቅስቃሴና የስብሰባ አጀንዳ ግልፀኝነት እንደሚጎድለው አመልክተዋል፡፡ ዛሬ ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ የሼህ አብደላ አልሃረሪ መፀገፎች መበተናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስብሰባው በርካታ ወጣት ዳዒዎች፣ዑስታዞች እንዳይሳተፉ ታግደዋል፡፡ተሳታፊዎቹ የተመረጡት በመጅሊሱ አመራሮች መሆኑንም ታማኝ ገልጸዋል፡፡ Read more
  • Two children injured by Israeli army fire near Ramallah

    Ramallah 24-03-2012 IMEMC & Agencies: A Palestinian child was wounded in the face by a rubber-coated metal bullet fired by Israeli soldiers who attacked nonviolent protesters against the Wall and Settlements in Nabi Saleh village, near the central West Bank city of Ramallah; a second child was shot and injured in the leg. Medical sources reported that Ez Ed-Deen Tamimi, 15, was treated by medics before he was moved to the Ramallah Medical Center suffering moderate injuries. A second child, identified as Osama Bilal Tamimi, 16, was shot by a rubber-coated metal bullet in his foot; his injury was described as mild. The army also fired dozens of gas bombs and concussion grenades at the nonviolent protesters, including Israeli and international peace activists, and also sprayed them with chemical-contaminated water. Dozens of protesters suffered the effects of teargas inhalation. It is worth mentioning that a team of the International Workers Union, including the head of the Union, participated in the protest to express solidarity with the Palestinian people facing ongoing aggression by the Israeli occupation, its soldiers and settlers. The Union’s head expressed solidarity with the Palestinian detainees, including female detainee Hana’ Ash-Shalabi who has been on hunger-strike since she was kidnapped by the army on February 16. He added that Nabi Saleh village is a symbol of steadfastness and nonviolence resistance against the illegal Israeli policies, including Israel’s Annexation Wall and Settlements in the West Bank. The protestors were also marking the first anniversary of the kidnapping of Basem Tamimi, a local figure and leader of the nonviolent resistance movement in the village who was kidnapped by the soldiers, and remains imprisoned by Israel through a process of endless “legal proceedings” that are only meant to keep him behind bars without charges. The army surrounded the village since early morning hours and installed a roadblock on its main entrance in an attempt to prevent journalists, activists and even medical teams from entering the village, local sources reported. Read more

Latest Articles

Most Popular