Latest Articles

  • የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ባልጨረሱ ፖሊሶች ተደበደቡ

    የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ባልጨረሱ ፖሊሶች ተደበደቡ -በጥይትና በከባድ ድብደባ የተጎዱ ተማሪዎች ህክምና ላይ ናቸው -የከተማው ነዋሪም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል ትላንት ለተቃውሞ በወጡ የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ታጣቂዎችበጥይትና በዱላ ጉዳት ማድረሳቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ከትላንት በስቲያ እሁድሚያዝያ 28 እና ትላንት ሰኞ ሚያዝያ 29 በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ሊከሰትየቻለው ተማሪዎች ተጓደለ ያሉትን የምግብ ጥራት በመቃወማቸው እንደሆነምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ እሁድ ሚያዝያ 28 ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በተቀጣጠለው በዚህ ተቃውሞ አብዛኛው ተማሪቁጣውን የዩኒቨርስቲውን መስታወቶች በመሰባበር እንደገለፀ የሚናገሩት ምንጮቻችንምሽት ላይ በድንገት ወደ ግቢው የገቡት ታጣቂዎች ተማሪዎቹ ላይ ከመጠን ያለፈኃይል በመጠቀም ጉዳት እንዳደረሱ ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ በታጣቂዎች በተወሰደውእርምጃ ከ60 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸውና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ላይድብደባ እንደተካሄደ ታውቋል፡፡ በወቅቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከፍተኛ የተኩስእሩምታ የተሰማ ሲሆን ኢብራሂም መሀመድ የተባለ የ2ኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ በጥይት መመታቱ ታውቋል፡፡ ተማሪው በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳትበደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ በመከታተል ላይ እንደሚገኝ ፍኖተ ነፃነት ስፍራው ድረስ በመደወል አረጋግጣለች፡፡ ተማሪ ኢብራሂም መሃመድ በስልክ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፀው ከትላንት በስቲያ ምሽት ታጣቂዎቹ በቀጥታ በጥይት እግሩ ላይ መተውአቁስለውታል፡፡ ሌላው በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመበት የ2ኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ የሆነውና ከትግራይ ክልል የመጣው ገብረ ኪዳንብርሃኔ ትላንት ጠዋት በጀርባውና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ለዝግጅት ክፍሉ ተናግሯል፡፡ በትላንትናው እለት ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ‹‹የታሰሩ ተማሪዎች ይፈቱ›› የሚል ጥያቄን ይዞ የቀጠለው ተቃውሞ ቀስ በቀስ ከዩኒቨርሲቲው ውጪመስፋፋቱን ከከተማው ያገኘናቸው መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ ተቃውሞው በደብረ ማርቆስ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በቀጠለበት ወቅት በርካታ የከተማውነዋሪዎችም ትዕይንቱን ተቀላቅለው ጥያቄው ፖለቲካዊ ይዘት ተላብሶ ገዢውን ፓርቲ በማውገዝ እና ለኑሮ ውድነቱ ገዢውን ፓርቲ መኮነናቸውንምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ታጣቂቆች ቶክስ በመክፈታቸው ተቃውሞው ተበትኗል ሲሉ ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ በሁኔታውየተደናገጡት ተማሪዎች ወደ ተለያየ አቅጣጫ ሲበታተኑ ታጣቂዎችና ፖሊሶች አብዛኞቹን እያፈሱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዳጓጓዟቸው የከተማው ነዋሪዎችለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ወደ ህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ አፈሳው እንደቀጠለ ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም በድብደባዉከተጎዱ ተማሪዎች መካከል አይናቸዉ ተመትቶ ኡፕራሲዮን የተደረጉ እንደሚገኙበት አስረድተዋል፡፡ ከስፍራው የደረስን መረጃ እንደሚያመለክተውበተማሪዎቹ ላይ እርምጃ የተወሰደው ስልጠናቸውን ባልጨረሱ ፖሊሶች ጭምር መሆኑን ያመለክታል፡፡ ማምሻውን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተውአሁንም በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ዩኒቨርሲቲውና ወደ ደብረማርቆስ ሆስፒታል ደውለን ምላሽወደ ህትመት እስከገባንበት ሰአት ድረስ ምላሽ ማግኘትአልቻልንም፡ Read more
  • ye mejlis mercha ke gelobal wede mazegaja

    የመጂሊስ ምርጫ፡ ከ’ግሎባል’ ወደ ‘ማዘጋጃ’ በ 2001 ፤ የቀድሞ መጂሊስ ሹማምንት የእነ አቶ ኤሊያስን ቡድን እንዝላልነት ለማረምና ሙሰኞችን ለፍርድ ለማቅረብ በሚል ህቡዕ ሰበብ በግሎባል ሆቴል በተሰየሙ ጉባዔተኞች አድስ ፤ታማኝና የአህባሽ ጥምቆች (ቅምጦችም ይሆናል- የፖለቲካ)፤ አረንጓዴ ጠምጣሚዎች አቶ አህመድን ጨሎን ራስ አድርገው፡ ሌሎች ደግሞ በተዋረድ ተሹመው (ተመርጠው አላልኩም) በጓሮ በር ወንበሩን ያዙ፡፡ እኛም ከዛሬ ነገ አቶ ኤሊያስ በ50 ሚሊዮን ብር ሙስና ተከሶ ፍርድ ቤት ሲቆም (ወይም ሲቀመጥ) ለማየት በጉጉት ስንጠብቅ፡ ስንጠብቅ …. (የዋሆች!) ተረስቶ ቀረ- ወይ አለማወቅ! ለካስ ለመሾም ሙስና ዋነኛ መስፈርት ሆኖ ኖሯል! እነ ጨሎም ቢሮውንና ሙስናውን ከተላመዱ በኋላ ከመንግስት ’አህባሽ’ን የማጥመቅ ዘመቻ እንደ ዋና የቤት(ቢሮ)ስራ ተሰጥቷቸው ተረከቡ፤ ከዚያም ቅደመ-ማፅዳት ስራ ጀመሩ-‘IIRO’ን ማስባረር፡ አወሊያን መረከብ፡ ለመንግስት መረጃ ማቀበል፤ የሙስሊሙን የልብ ትርታ መለካት ወዘተ…. ስንቱ ጥፋት ይዘረዘራል.. በመጨረሻም ከሊባኖስ 200 የአህባሽ ዓሊሞችን በማስመጣት በሃምሌ 2003 በሐረር ማጥመቁን በይፋ ጀመሩ ቀጥሎ በሌሎችም ቦታዎች አፋፋሙት፡፡ ህዝበ-ሙስሊሙም ነገሩን በሹክሹታ፤ በፊት-መፅሃፍ(facebook)ጫካ፤ በጋዜጣና መፅሄቶች መቃወሙን ተያያዘው፡፡ ተቃውሞው በውጭ ሃገራት አይሎ ነበርና በ November 21, 2011 በአሜሪካ የተቃውሞው ሰልፍ ፈነዳ፡፡ በሀገር ውስጥ ግን ፍርሃት እንደነገሰ ነው ሆኖም በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ የአወሊያ ኮሌጅ መዘጋትና መምህራንና ኢማም መባረርን ተከትሎ በጀግኖች የአወሊያ ተማሪዎች አገር ውስጥም የተቃውሞ ሰልፍ ፈንዳ፡ አድሳባዎችም አጎራባቾችም ሆኑ ክፍለ-ሀገሮች ከቤታችው፤ የፊት-መጽኃፍ ታጋዮችም ከጫካው በመውጣት የተቃውሞ ትግሉን ተቀላቀሉ፡ የቅሬታ ፊርማም ተጧጧፈ፤ ጥያቄውም ከአወሊያ ጉዳይ ወዴ መጂሊስ ይውረድ አደገ፤ መጂሊሶችም ጨነቃቸው፡ ተቃውሞውም ጠነከረ፡ በኮሚቴ ተዋቀረ፡ ወደ ክፍለ-ሀገርም ተሰራጨ ሀገራዊም ሆነ፤ እስካሁን የተዋጣለት አካሄድ መሄድ ችሏል፤ ከመቼውም በላይ አንድነት ጠንክሯል፤ ድጋሜ ላይላላም ተማምለዋል፤ አንዋር መስጅድ ላይ ከትሟል፤ መንግስትንም አወዛግቧል፤ ዓለምንም አስተጋብቷል፡፡ በጀት ለ2004 መጂሊስም በጥር ወር ላይ የ2004 አመታዊ በጀቱን ይፋ አደረገ፡ 636 ሚሊዮን ብር (“ከየት መጣ?” ብሎ መጠየቅ ያስቀስፋል) ለአወሊያም 6 ሚሊዮን ብር ስለተመደበለት ሰልፉን ትታችሁ ወደ ቤታችሁ ግቡ ተባለ (አይ መደለያ!!) ጋዜጣም ተገዛ(“አል-ቁድስ”)፡ በቅርቡም የሀገር ውስጥ ዊኪሊክሰ ይፋ አንዳደረገው ከበጀቱ ውስጥ 203ሚሊዮን ብር የሚሆነው በአቶ ጨሎ ልጅ የግል ቁጠባ ሂሳብ መግባቱን ፤ ለ”አል-ቁድስ” ጋዜጣ በየወሩ 88ሺህ ብር መሰጠቱን፤ አብዛኛው ገንዘብ ለአህባሽ ስልጠናና ለጫት ወጭ እንደሚውል መታቀዱን ሰማን- ጆሮን አትስማ አይሉት፡፡ የጉልቻ ለውጥ ዜና አሁንም እንዴ ሀገር ውስጥ ዊኪሊክሰ መረጃዎች መሰረት ባለፈው ሀሙስ ሚያዚያ 19 ቀን እጅ….ግ መራር ዱብዳ ከአቶ መለስ በፀጥታ አማካሪያቸውና የቀድሞ የትግራይ ክልል ብረትዘንድአንት(ትርጉሙ-መሳሪያ በእጅህ ያለ) አቶ ፀጋዬ በርኸ እና በፌደራል ገዳዮች ሚ/ር ‘ሙፍቲ’ ሽፈራው ተ/ማሪያም በኩል መጂሊሶች ከስልጣናቸው በእንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲወርዱ ተነገራቸው፤ መቼም ከስልጣንና ከጫት መነሳት ይከብዳል ይላሉ (የሚያውቁት) እናም የኦሮሚያና የአዲሳባ መጂሊሶች አለቃቀሱ አሉ፤ ምርጫም በሰኔ ወር እንደሚካሄድ ተነገራቸው (ለነገሩ ከአሁን በኋላ ምን ሊያደርግላቸው-እኛ ከወረድን ሰርዶ አይብቀል ነውና ነገሩ!)-በፌደራል ገዳዮች ሚ/ር በጀትና መሪነት ብሎም በዑለማዎች ም/ቤት(በመጅሊሱ የተቋቋመ) ሽፋንነት- ልጅ አባቱን ሲመርጥ!! ይህን ዜና ተከተሎ ትላንት ግንቦት 1 ቀን በአድሳባ ማዝጋጃ ቤት አዳራሽ የ”ነባሩ” እስልምና ተከታዮች (ለአህባሽ በአቶ መለስ የተሰጠ አዲሱ ለምድ) ብቻ ለጉባዔ ታደሙ፤ መከሩም፤ ዘከሩም በመጨረሻ ላይ የእነ ጨሎ ልጅን ጅማሮ አጠናክሮ የሚቀጥል፤ ድክመታችውን የሚያርም፤ “ጊዜያዊ” የመጂሊስ ፕሬዜዳንት ለመሾም ጠንካራ ታጋይ ማፈላለጉን ተያያዙት፤ ከብዙ ቁፈሮ በኋላ አንድ ጀግና ብቅ አሉ-ከትግራይ(ዘረኛ እንዳትሏቸው-ዘረኝነት በኢስላም ቦታ የለውምና!) ሸህ ከድር ማህሙድ ይባላሉ፡፡ ሸህ ከድር የትግራይ ክልል መጅሊስ ፕሬዜዳንት የነበሩ ሲሆን ከወር በፊት ሚያዚያ 1 ቀን ስልጣናቸውን አስረከበው በታላቅ ሽኝት ለዕድገት ወደ አድሳባ መጥተው የዑለማዎች ም/ቤት ፕሬዜዳንት አማካሪ በመሆን ተሸመው ለአንድ ወር ያህል ካገለገሉ በኋላ ነው-ትላንት ለ”ጊዜያዊ” የፌዴራል መጅሊሰ ፕሬዜዳንትነት የታጩት(ጊዜያዊ በመጅሊስ ዘመን አቆጣጠር ገደብ የለውም)፡፡ ከአንድ ወር በኋላም ስልጣናቸውን ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል-ምናልባት ህዝበ-ሙስሊሙ ቁሞ ከጠበቃቸው! ይድረስ ለክቡር አቶ መለስ ከሁሉም በፊት አስቀድሜ በጨሎ ልጅ ቁጠባ ሂሳብ ውስጥ ያለውን 203 ሚሊዮን ብር እንዳይረሱት ለማስተወስ ነው-ስራ ስለሚበዛብዎት፤ ለነገሩ ምን አላትና እንደውም “አፍወቱል-አህባሽ” በሉት፤ ወይም ለተሰናባቾቹ እኩል ያካፍሏቸው፡፡ ክቡርነትዎ ሦስቶቹ መሰረታዊ ጥያቄዎቻችንን ቢያንገሸግሽዎትም እደገማቸዋለሁ.. 1. የመጅሊሳችንን መሪዎች እኛው፤ ከእኛው፤ ለእኛው፡ በነፃነት፤ በግልፅ፤ ያለማንም ጣልቃ-ገብነት በመሳጅዳችን እ…..ንምረጥ!!! ስለዚህ ‘ጥቁሩን አውርደው ነጩን አህባሽ(“ነባሩ” እስልምና አማኝ በራስዎ ቋንቋ እንዲገባዎት)ተኩልን’ በፍ…..ፁም ኧረ በፍ……ፁም አልንም፡፡ ምክንያቱም ጉልቻ ቢቀያይር ወጥ አያጣፍጥምና! ለነገሩ በቤተ-መንግስት ጉልቻ ስሌለለ ላይገባዎት ይችላል!!….ሰምተዋል!? መጅሊሱ በስንት አባቶቻችን ደም እንደተመሰረተ በአይንዎ አይተዋል! ደም፤ ህይወት፤ ገንዘብ፤ ጊዜና ጉልበት ተከፍሎበታል-ዛሬ ካዴሬዎች ቢፈነጩበትም! ስለዚህ በቃዎት፤ ጥላቻም ልክ አለው! በቃ……..! 2. አወሊያም ሆነ ሌሎች የሙስሊሙ ተቋሞችም እንደመጅሊሱ በብዙ መስዋዕትና ትግል የቆሙ ናቸው፤ ስለዚህ ለዚህ ለእርስዎ አድሱ(ውይ! ይቅርታ ተሳሳትኩ “ነባሩ”ማለቴ ነው) ሃይማኖት ማጥመቂያም ሆነ ለፖለቲካዎ ስራ መጠቀም አይቻልም፡፡ ሙስሊሙ እነደሰራቸው የራሱ ንብረት ሆነው በራሱ ሰዎች ይተዳደሩ!!! 3. አህባሽ ኢትዮጲያ ውስጥ ከ1994/5 ጀምሮ በ’NGO’ነት በራሱ ማዕከላት እንደሰበከው ዛሬም መስበክ ይችላል፤ ነገር ግን በእርስዎ ሰራዊቶች ተገደን፤ ተስፈራርተን በኢትዮጲያ ህዝብ ተቋማት ውስጥ ያለ አግባብ ሊጫንብን አይገባም፤ ነውርም ነው፤ ኢ-ሰብዓዊም ነው፤ ኢ-ህገ-መንግስታዊም ነው፤ ስለነባርነቱ ባይሰብኩን ይሻላል-ከፈለጉ እራስዎ ያምልኩት! የእኛን የእምነት ምርጫ ለእኛው ይተውልን!! ጥያቄዎቹ አለቁ፤ በቃ አራት ነጥብ(፡፡) አይጨመ(ም)ሩ፤ አይቀነ(ን)ሱ..(‘ጨ’ ና ‘ቀ’ ይጠብቃሉ!)- አራት ወራትን አሳለፉ!!! ስለዚህ ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ጥፋት አይስሩ! ጥቁር ታሪክ አይስሩ! ይድረስ ለሙስሊም ብሎም ለመላ ኢትዮጲያውያን ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ፤ እናትና አባቶቼ ይህ ሃይማኖታዊ የመብት ጥያቄ ትግላችን ከፍተኛው ጡዘት ላይ ደርሷል-በአላህ ፈቃድ! በዚህም ሁለት ጥቁር ነጥቦች መቼም አይረሱንም-የካቲት 26 ፌዴራል ገዳዮች የተፋበት ቀን እና ሚያዚያ 19-የአሳሳ ንፁሃን ሙስሊም ወንድሞቻችን በፖሊሶች ጭፍጨፋ በግፍ ህይወታቸው ያለፈችበት(አላህ ጀነትን ያጎናፅፋቸው!) ቀን! ስለዚህ፤ 1. አሁንም ቢሆን አንድም ጥያቄያችን በአግባቡ አለመመለሱን በማወቅ ለሌሎችም በአግባቡ ማስረዳትና ሴራውን ማጋለጥ ብሎም ግንዛቤ በሰፊው መስጠት…. 2. አንድነታችንን በማጠንከርና ፍፁም ሰላማዊ በሆነና ከየመሳጅዳችን ቅጥር ግቢዎች ሳንወጣ የተቃውሞ ሰልፋችንን በበለጠ በማጠናክር ማካሄድ፤ (አደራ ስሜታዊ እናስወግድ) 3. የመንግስት ማስፈራሪያዎችንና ዛቻዎችን ከመጤፍ ሳንቆጥርና ቅንጣት ታክል ሳንፈራ በጥንቃቅ በመከታተል ራሳችን ለራሳችን የደህንነት ኃይል ሆነን በንቃትና በትጋት መጠበቅ፤ ለትልቁ ዓላማችን ወሳኝ ነውና፤ 4. ወደድንም ጠላንም ይህ ተቃውሞ ላይመለስ 11ኛው ሰዓት ላይ ደርሷል! ይህ ጥያቄ ከተቀለበሰ ትልቅ አደጋ አለው፤ ትልቅም ታሪካዊ ጠባሳ ጥሎ ማለፍም ብቻ ሳይሆን ምናልባት ላንዴዬና ለመጨረሻ ጊዜ ድጋሜ ላይነሳ ተቀብሮ ሊቀር ይችላል፤ ስለዚህ እንደ ቀላል ነገር ማየቱ እስልምናን በኢትዮጲያ ላይ አጣብቂኝ ውስጥ ከማስገባቱም ሌላ ለዚህም ተጠያቂዎቹ እኛው ነን!! 5. መረጃ ኃይል ነውና መረጃን በጊዜው፤ በዕውነተኝነት፤ በአስቸኳይ ለሌሎች ማቀበል፤ በትኩሱ መቀበልና ለክርስቲያን ወገኖቻችን ስለጉዳዩ ማስረዳት፤ ትዕይንቶችን በድምፅና በምስል በመቅረፅ ወደ ኢንተርኔት መረጃ ቋቶች መስቀል፤ ትዕይንቱንም በፅሁፍና በምስል መለጠፍና ለዜና አውታሮችም ማቀበል…ወዘተርፈ……….. በመጨረሻም ሁሉም ኢትዮጲያውያን ይህ ጉዳይ ከዘርፈ-ብዙዎቹ የኢህአዴግ የ”ከፋፍለህ ግዛ” አካል አንዱ ነውና ሴራውን ተረድተን ለመንግስት ፕሮፓጋንዳ ጀርባችንን ሰጥተን ሁላችንም ለወደፊቷ ኢትዮጲያ በአንድነት እንድንቆም፤ አንዱ አንዱን እንድጠብቅ (እንደ ግብፆቹ)፤ ከእያንዳድንዱ ሃይማኖታዊ ጥፋቶች ጀርባ የመንግስት ህቡዕ እጆች እንዳሉብት በማጤንና በመረዳት “በቃህ፤ ኧረ በቃ…..ህ” ልንለው ይገባል፤ ኧረ ህዝቦች- ኢትዮጲያ ጠፈች፤ በሀሰት ላይ ቆመች፤ ትውልዷ ከሸፈ፤ በጨካኞች ተሾፈረች፤ ስንቱ ….…… አንድ እንበላት!! ለዛሬ እኔ እዚህ ላይ ይብቃኝ፤ ትግሉ ግን ይቀጥላል!! ድል ለኢስላም ነው!! አሏሁ አክበር!! አሏሁ አክበር!! By Bin Moh Read more
  • ከኮሚቴ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

    ግንቦት 2፣ 2004 ለሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መፍትሄ ለማፈላለግ ከተቋቋመው ኮሚቴ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ላለፉት አራት ወራት እጅግ ሰላማዊና ህገ መንግስታዊ በሆነ አግባብ አቤቱታችንን ለመንግስት ስናቀርብ ቆይተናል፡፡ ጥያቄዎቻችን የሃይማኖት፣ የግለሰብና የማህበረሰብ ነጻነቶችን በተመለከተ በሕገ መንግስታችን የተቀመጡትን አቢይ መነሻዎች፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሁም መብቶችና ነጻነቶችን መሰረት ያደረጉ ህጋዊ የህዝበ ሙስሊሙ ብሶቶች ናቸው፡፡ ጥያቄያችንን ያቀረብነው በህገ መንግስቱ መግቢያ ላይ እንደሰፈረው “ባህሎችና ሃይማኖቶች ካለ አንዳች ልዩነት እንዲራመዱ የማድረ...ጉ አስፈላጊነት ጽኑ እምነታችን” በመሆኑ ነው፡፡ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. መንግስትም ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት የማረም ህገ መንግስታዊ ሀላፊነት እንዳለበት ተስፋ በማድረጋችን ነው፡፡ ጥያቄያችን ሕገ መንግስቱ ይከበር፣ ሃይማኖት በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱሕገ ወጥ እንደመሆኑ ሁሉ መንግስትም በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ስልጣንስሌለለው በዚህ ረገድ ባለስልጣናቱንና መዋቅሩን ይቆጣጠር የሚል መንፈስ ያስተጋቡ ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ሕገ-መንግስቱን የሚያከብርና የሚያስከብር የራሱንም መተዳደሪያ ደንብ የሚያከብር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትቢዋቀር ኖሮ እኛም ህዝባዊ ጥያቄ በመያዝ የመንግስት ቢሮዎችን ማንኳኳት ባላስፈለገን ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እነዳለ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የህዝባዊ ንቅናቄውን ቀና መነሻና ጥያቄ ለሀገርም ለህዝብም በማይፈይድ መንፈስና ገለጻ ማቅረቡ አሳዝኖናል፡፡ እንደሚታወቀው የካቲት 26፣ 2004 የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሰጠው ምላሽ ውስን የመርህም ሆነ የአፈጻጸም ግልጽነት ያልተስተዋለበት ከመሆኑ ባሻገር መጅሊሱ ሆን ብሎ ሲሰጣቸው የነበሩ መግለጫዎች ህዝባዊ ቁጣበማስከተላቸው የጥያቄያችን ይሰማ ትግላችንን ለመቀጠል መገደዳችን ይታወሳል፡፡ ይሁንና በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ምንም እንኳ ጥያቄአችንን በቀጥታ መልሰውልናል የሚል እምነት ባይኖረንም መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ እንደማይገባ ዳግም አረጋግጠውልናል፡፡ ተግባራዊነቱን በሂደት የምንታዘበው ጉዳይ ነው፡፡ ወትሮውንም የአፈጻጸም ስህተት እንጂ የመርህ ብዥታ እንደሌለ እውን ነው፡፡ በተጨማሪም የሃይማኖታችንን ኢትዮጵያዊ ሚናና ሕልውና የሚመለከቱ አንኳር ገጽታዎች እንዳሉ ብናምንም በህዝብ ለተወከልንበት ጥያቄዎች ከመርህ አኳያ ምላሽ የተሰጠበትክስተትና ተግባራዊ ፍንጭም በመስተዋሉ፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያልተመረጠ አመራርም ሲጥሰው የቆየውን መተዳደሪያ ደንቡን መርምሮ ራሱን ከሀላፊነት ለማግለል በመወሰኑ ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳው ጥያቄ ምላሽ የማግኘት ሂደት ላይ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ የስልጣን ሽግግሩ ህዝባዊነት በሌለውና የመጅሊሱ መዋቅር አካልና አጋር ለሆነው እንዲሁም መዋቅራዊአቅም ለሌለው የኡለማዎች ምክር ቤት መሰጠቱ አግባብ እንዳልሆነም ይሰማናል፡፡ ቢሆንም ሕዝበ ሙስሊሙ በቅርቡ ለሚደረገው የመጅሊስ ምርጫ ይሆኑኛል የሚላቸውን ተወካዮች ለመምረጥ ብርቱ ዝግጅት ከማድረግ በተጨማሪ ከኮሚቴው ጎን በመሆን አፈጻጸሙ ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ግልጽና ፍትሃዊ መሆኑን በንቃትእንዲከታተልም ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በመላ ሀገሪቱ ያለው ህዝባዊ ጥያቄ ተመሳሳይ በመሆኑ መንግስት ካነሳነው ጥያቄ ጋር በተያያዘ ምክንያት ለእስር የተዳረጉ እንዲፈቱ፤ ማስፈራራቶችና የኃይል እርምጃዎች እንዲቆሙ ያደርግ ዘንድ አቤቱታችንን እናቀርባለን፡፡ ዴሞክራሲና እውነተኛ ሰላም ከማንም በላይለህዝበ ሙስሊሙ ብቸኛ የድል መስመሮች መሆናቸውን ድምጻችንን ለተጋሩ ሁሉ በድጋሚ እያሳሰብን ወደ ብጥብጥ ሊያስገቡየሚችሉ ድርጊቶች በመስጊዶችም ሆነ በማንኛውም ቦታ እንዳይከሰቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ በአላህ ስም እንጠይቃለን፡፡ Read more
  • Announcement!!!World-wide mass protest on May 31st 2012 against Ethiopian government for the massacre of peaceful, innocent Muslims

    Announcement: World-wide mass protest is planned on May 31st 2012 against Ethiopian government for the massacre of peaceful, innocent Muslims demonstrators in Arsi-Asasa, and its persistence in interfering in our religious affairs and the ongoing subjugation of our fellows at home. Thus, you are cordially invited to join the protest nearest to you. Detail Info & list of Countries will be given on Sunday May 13, 2012. In Ethiopian Muslims Interfaith Dialog for justice Room. The Global Organizing Adhoc-Committee. Read more
  • የማንችስተር ሲቲ ተጫዋች የሆነው ያህያ ቱሬ የኮከብ ተጫዋች ሽልማት ሀይማኖቴ አይፈቅድልኝም በ ማለት ሽልማት አልቀበልም አለ!!

    በእንግሊዝ ፕሪሚየም ሊግ ለማንችስተር ሲቲ ቡድንና ለኮትዲቭዋር ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነው ያህያ ቱሬ ቡድኑ ከኒውካስትል ጋር አድርጎት በነበረው ጫወታ ጥሩ እንቅስቃሴ በማሳየቱ ኮከብ ተጫዋች ተደረጎ ቢመረጥም የቀረበለትን ሽልማት አልቀበልም ብሏል።ስካይ ስፖርትስ የተባለው ቻናል ከጫወታው በኌላ ኮከብ አድርጎ እንደመረጠው አሳውቆት ሽልማቱን እንዲቀበል ጠርቶት የነበረ ሲሆን ሽልማቱ አስካሪ መጠጥ የነበረ በመሆኑ እኔ ሙስሊም ነኝ ሀይማኖቴ አይፈቅድልኝም በ ማለት ሽልማቱን የማይቀበል መሆኑን ገልጾላቸዋል። አላህ ይጨምርለት !!! አሚን !!! Read more
  • መልካም ጥርጣሬ !!

    መልካም ጥርጣሬ by Ibrahim Abdulaziz ሰውዬው እጅግ ታታሪ የሆነ የታክሲ ሹፌር ነው ፡፡ደከመኝ ሰለችኝ ሳይል ሌት ተቀን ይሰራል፡፡ታዲያ አንድ ቀን ሚስቱ “ውዴ ሆይ ለምን ይህን ያህል ትደክማለህ፡ያለንን እያብቃቃን ብንኖር ይሻለናል፡እኔም ቢሆን ካንተ ጋር ሰፊ ጊዜ ማሳለፍ እፈልጋለሁ አለችው፡፡” “ማሬ እኔም እኮ የምለፋው እንደምንም ብዬ የራሳችን ታክሲ ለመግዛት እና ከዛም እርፍ ብለን በርካታ ጊዜያትን አብረን እንድናሳልፍ ነው፡፡”ሰውዬው መለስ፡፡ሚስትም ታዲያ “ብቻህን አትችለውም በዛ ላይ ገቢውን ታውቀዋለህ በዚ መልኩ ሰርተህ ደግሞ ታክሲ ለመግዛት ረጅም ጊዜ ይፈጅብሀል፡ስለዚህ እኔን አረብ አገር ላከኝና ጠንክሬ ስርቼ ለምን ከዛ አልክልህም ቢበዛ ሁለት አመት ቢፈጅብኝ ነው፡፡”አለችው ፡፡ሰውዬውም ከሚስቱ መለየት ቢከብደውም ነገን የተሻለ ህይወት ለመኖር አማራጭ የለምና በሀሳቧ ተስማምቶ ሌት ተቀን ለፍቶ አልበላም አልጠጣም ብሎ ያጠራቀመውን ገንዘብ አውጥቶ ላካት ታዲያ በመጨረሻ ስንብታቸው ወቅት፡ሆዴ ቃል እገባልሀለው በሁለት አመት ውስጥ ታክሲ ገዝቼ እልክልሀለው፡እስከዛው ግን በጣም ትናፍቀኛለህ ብላው ተላቅሰው ተሰነባበቱ፡፡ታዲያ ቀን ቀንን እየወለደ በዋዛ ፈዛዛ አንድ አመት አለፋ ግን በሰላም ደርሻለሁ ከሚለው የመጀመሪያ መልዕክቷ ውጭ ድምጽዋ ጠፋ ፡፡ታዲያ ይህ ሰው ቢጨንቀው አንድ አሊም ነው ብሎ የሚያሰበው ሰው ጋር ሄዶ ”ባለቤቴ ውጭ ላከኝና ስርቼ ታክሲ ልላክልህ ብላኝ ነበር ግን ይሀው አንድ አመት ሞላት በሰላም ደርሻለው ከማለት ውጪ ደውላ አታውቅም፡ምን አሰባ ይሆን ሲል ጠየቀው” ፡፡ አሊም ተብዬም “ወዳጄ እስኪ ሁሰነ ዘን(መልካም ጥርጣሬ) ይኑርህ ምንአልባት አልተመቻት ይሆናል” ሲል መለሰለት ፡፡ሰውዬውም መልሱን ተቀብሎ አዎ በሚስቴ ላይማ መልካም ጥርጣሬ ሊኖረኝ ይገባል፡ሳይመቻት ቀርቶ ነው ብሎ ተመለስ፡፡ቀናት መቼም ማቆሚያ የላቸውምና አሁን ድምጽዋ ሳይሰማ ሁለተኛው አመት ደረስ፡ታዲያ ባል ቃል የተገባለት ጊዜ ቢያልፍበት አሊም ተብዮው ጋር ዳግም መፍትሄ ፍለጋ አቀና፡አሁንም አሊም ተብዬው “ወዳጄ ሁስነ ዘን (መልካም ጥርጣሬ) ይኑርህ ምን አልባት የሰራቸው ገንዘብ ታክሲ ለመግዛት በቂ ስላልሆነ ይሆናል”;; አሉት ታዲያ ባልም ዳግም የመልካም ጥርጣሬን ሀሳብ አጽድቆ ተመለሰ፡፡ሀይ ባይ የሌለው ቀን አሁንም ነጎደና ሶስተኛው አመት ደረስ፡፡ታዲያ ባልም የመልካም ጥርጣሬ እሳቤው ላይ ጥርጣሬ ቢያድርበት ተመልሶ የእሱ አሊም ጋር ሄደ ፡ታዲያ አሊሙም “ተረጋጋ እንጂ ወዳጄ መልካም ጥርጣሬ ይኑርህ ፡ምናልባት የተሻለ ታክሲ ልትገዛልህ አስባ ይሆናል አለው”፡፡ሰውዬውም አምኖ ተመለስ፡፡ታዲያ እንደ ጅረት የሚፈሱት ቀናት አራተኛ አመት ሊሞላቸው ሲቃረብ ፡ሚስት ለባል እንዲህ ሰትል ደወለች “ሆዴ እስከዛሬ ድረስ የጠፋሁት ልንገርህ ፈርቼ ነው፡፡አሁን ግን አማራጭ የለኝም ፡እዚህ ከሌላ ሰው ልጅ ወልጃለሁ ልጁን ይዤ መስራት ስላልቻልኩ ነገ በሚመጣው አየር ልኬዋለሁ ተቀብለህ እንደልጅህ እንደምታሳድግልኝ ተስፋ አደርጋለሁ “ብላው የሱ ድምጽ ሳይሰማ ስልኩ ተዘጋ፡፡ታዲያ ሰውዬው በብስጭት አሊም ተብዬው ጋር ይሄድና ጉዳዩን ያወጋዋል፡፡አሊም ተብዬውም “ተረጋጋ ወዳጄ ሁስነ ዘን (መልካም ጥርጣሬ) ይኑርህ ምን አልባት ከታክሲው ቀድማ ረዳቱን(ወያላውን)ልካልህ ይሆናል” አለው፡፡አሁን ግን ሰውዬው መልካም ጥርጣሬ የሚይዝበት አንጀት ራቀው፡፡እኛ ሙስሊሞች ባለፉት መሪዋቻችን የጭቆና ቀንበር ተጭኖብን አጎንብስን ኖረናል፡፡በበደል ሸክም ጀርባችን ጎብጧል፡፡ታዲያ እነዛ አምባገነኖች በህዝብ ትግል ከተወገዱ በኃላ በዘመነ ኢ.ህ.አዲ.ግ. ጭቆናው መልኩን መቀየሩን እንጂ አለመወገዱን ልብ ያላልን ኢህአዲግን በበጎ የምንጠረጥር የዋሆች ቁጥራችን ቀላል አይደለም፡፡ሌላው ይቅርና የሠሞኑ እንቆቅልሽ የታሪክ ጥራዞችን የሚሞላ ሆኖ ሳለ ፡ኢ.ህ.አ.ዲ.ግ.ን በበጎ በመጠርጠር የመጀመሪያ እጃችንን የጠቆምነው ወደ መጅሊስ ነበር፡፡አሁንም ኢህአዲግ ችግራችንን ይፈታልናል በሚል በጎ ጥርጣሬ ደጃቸውን ጠንተን ፡በቀጠሮዋቸው ተመላልስን የተሰጠንንም መልስ አሁንም በበጎ በመጠርጠር የግለሰቦችና የአንድ ሚኒሰቴር መ/ቤት አቋም ነው ብለን ሳንጨርስ ፡ከጠ/ሚኒስተሩ መልሱ ቃል በቃል ተደገመልን፡፡ ለአላማው ማስፈጸሚያ ያሰቀመጣቸውን የመጅሊስ አመራሮች አስወገደልን ይህ ትልቅ ድል ነው በሚል በጎ ጥርጣሬያችን አሁንም እንደቀጠለ ነው ፡፡ለኔ ግን ኢ.ህ.አዲግ አቅጣጫውን ቀይሮ እኛን የሚበታትንበት አዲስ መንገድ አምጥቷል፡ምን አልባትም መጂሊስ ይሀው ተወገደላችሁ ከዚህ በኃላ ተቃውሞ አልቀበልም ሊል ይችላል :: እኛንም ጉዳዩ ለሁለት እንዳይከፍለን እፈራለሁ ምክኒያቱም የመጅሊስ መባረር ብቻ በቂ አድረግን አስበን ፡መጂለስ መባረሩ ብቻ በቂ አይደለም ሙስሊሙ በሚፈልጋቸው አመራሮች መተካት አለበት ከሚለው ሀሳብ ጋር እንዳንጣረስ ፍርሀቴ ነው፡፡በዛ ላይ ጉዳዩን ከተለያዩ ሚዲያዎች ሽፋን ለማሳጣትና ሙሰሊሙን ጸብ አጫሪ ለማስመስልም ይሆናል፡፡የሆነ ሆኖ በጎ ጥርጣሬያችንን አቁመን ከሚተጣጠፈው የኢህአዲግ ዕቅድ ጋር የሚተጣጠፍ ዕቅድ ከሌለን የመጨረሻው ውጤት እንደ ሰውየው ለመቀበል የከፋ መርዶ ነው የሚሆነው፡፡ Read more
  • Allahu Akber!! Yemejis ameraroch mulu lemulu kesltanachew endinesu tewesene

    አላሁ አክበር!አላሁ አክበር! የመጅሊስ አመራሮች ሙሉ ለሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲነሱ ተወሰነ:: የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ወይም የመጅሊስ አመራሮች ሙሉ ለሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲወርዱ ዉሳኔ መተላለፍ ተሰማ:: ይህ ዉሳኔ የተላለፈዉ ባሳለፍነዉ ሀሙስ ሲሆንለመጅሊስ አመራሮች ይህ መራር ዜና በአቶ ፀጋዬ በርሄና በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተርዶ/ር ሽፈራዉ አማካኝነት ይፉ ተደርጎል:: በዉሳኔዉም መሠረት አሁን በስልጣን ላይ የነበሩት አመራሮች በሙሉ ከስልጣናቸዉ እንዲነሱና ስልጣናቸዉን እንዲያስረክቡ መወሰኑ ተገልፆል:: ከመጅሊስ አመራሮች በኩል እንዴት እንዲህ ይወሰንብናል በማለት ቅሬታቸዉን ቢያሰሙም ከላይ የመጣዉሳኔ መሆኑ ተገልፆላቸዎል:: የመጅሊስ አመራሮች ምርጫም ከሰኔ ወር ጀምሮ ሀምሌ ላይ እንደሚጠናቀቅ ታዉቇል:: የምርጫዉን ሙሉ ሂደት በተመለከተ የፌደራል ጉዳዮች ደንብ ያዘጋጀ ሲሆን ሙሉ የምርጫ ወጪዉም በፌደራል ጉዳዮች እንደሚሸፈን ምንጮች ገልፀዎል:: ምርጫዉን የኡለማዎች ም/ቤት እንዲያካሂደዉ የተወሰነ ሲሆን በምርጫዉ ላይ መወዳደርም ሆነ ታዛቢ መሆን የሚችለዉ የነባሩ እስልምና ተከታይ ብቻ መሆን እንዳለበት ተወስኗል:: ምርጫዉም በምንም አይነት መልኩ መስጂድ ዉስጥ እንደማይካሄድእና በየቀበሌዉ እንደሚካሄድም ወስነዎል:: የመጅሊስ አመራሮች ምርጫዉ በዚህ ጊዜ መካሄዱ የማይፈለጉ ሰዎች ሊቆጣጠሩት አይችሉም ወይ በማለት ስጋታቸዉን የገለፁ ሲሆን የፌደራል ጉዳዮች ለዚህ በቂ ዝግጅት ማድረጉን እና ስለዚህ ጉዳይ የመጅሊስ አመራሮች እንደማይመለከታቸዉ ተነግሮአቸዎል:: የአህባሽ ስልጠናም ነባሩየኢትዮጲያ እምነት በመሆኑ በአዲሱ መጅሊስም በተጠናከረና በአዲስ መልክ ተቀጣጥሎ እንደሚቀጥል ተወስኗል:: አወልያን በተመለከተ በአዲሱ መጅሊስ ሰርእንደሚተዳደርም ወስነዎል:: ይህንን በመጅሊስ አመራሮች ላይ የተወሰነዉን ዉሳኔ ቅዳሜ እለት ዎና ዎና አመራሮችን ጠርተዉ እንዲያሳዉቁ በፌደራል ጉዳዮች ስለታዘዙ ዉሳኔዉን ቅዳሜ እለት አሳዉቀዎል:: በዚህ ዉሳኔ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ አመራሮች ከፍተኛ ተቃዉሞ አሰምተዎል:: ይህን ሁላ ትግል እያደረግን እንዴት እንዲህ ይወሰንብናል ያሉ ሲሆን ይህ ዉሳኔ ከበላይ የመጣ በመሆኑ ዎጥ አድርጉና መራራዉን አጣጥሙ ተብለዎል:: በቅርቡ ተሹመዉ የነበሩት የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት እና የኡለማዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አማካሪዎች ግን ካሉበት ስልጣን ፍንክች እንደማይሉና ባሉበት እንደሚቀጥሉ መወሰኑ ታዉቆል:: በዛሬዉ እለትም የሁሉምክልል መጅሊሶች እና ጠቅላላ ጉባኤዉ ተሰብስቦ የተወሰነባቸዉን የስንብት ዉሳኔ ወይም መርዷተቀብለዎል Source: ድምፃችን ይሰማ page Read more
  • በአሰሳ በእስር ከሚገኙት መካከል 100 የሚሆኑት ወዳልታወቀ ስፍራ መዛወራቸው ተነገረ

    በአሰሳ በእስር ከሚገኙት መካከል 100 የሚሆኑት ወዳልታወቀ ስፍራ መዛወራቸው ተነገረ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 27/2004 ከሳምንት በፊት በአሰሳ የተፈጠረውን ግርግር ተከትሎ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው 185 የሚሆኑ ሰዎች መካከል የተመረጡ 100 ወጣቶች ወደ ማይታወቅ ስፍራ መዛወራቸውን የአካባቢው ምንጮች አመለከቱ ፡፡ ምንጮቻችን እንዳመለከቱት ከሆነ የተመረጡት ወጣቶች ከአራት ቀናት በፊት ከአሰሳ ማረሚያ ቤት ጨለማን ተገን በማድረግ ወዳልታወቀ ስፍራ በመኪና ተጭነው ተወስደዋል፡፡ ከተወሰዱት ወጣቶች መካከል አንደኛው የሌላ እምነት ተከታይ ስለመሆኑ መታወቂያውን በማሳየት በሰጠው ማረጋገጫ ከተለቀቀ በኋላ ለማወቅ መቻላቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ወጣቱ ባደረሳቸው መረጃ መሰረትም ከአሰሳ ማረሚያ ቤት ተመርጠው የተወሰዱት ወጣቶች የሚገኙበት ስፍራ በግምት ከከተማዋ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ካለ ልዩ ማቆያ ቦታ ሳይሆን እንዳልቀረ አብራርተዋል፡፡ Read more
  • AlJazeera English report about Ethiopian Muslim 05/05/2012

    In Ethiopia, continue protest movement for Muslims in the mosques of the Ethiopian capital Addis Ababa and other states. Muslims are protesting what they say is government interference in the affairs of religion. demanding bodies and Islamic figures Ethiopian government to address the situation, and not to impose ideas on the band Abyssinian Muslims, fearing source Al-jazeera youtube Read more

Latest Articles

Most Popular