Latest Articles

  • World’s tallest mega-mosque being built in Algeria

    A big religious feeling deserves a big house of worship. Algeria is set to get its own mega-mosque with the tallest minaret in the world. Almost as tall as the Eiffel Tower, the $1.3-billion mosque will stand on 20 hectares of land and will be capable of hosting 120,000 worshippers within its prayer room. Its minaret will soar 270 meters high. Algerian President Abdelaziz Bouteflika said he wanted to “leave his mark" and enter history with this epic building. The construction is currently underway in the city of Algiers, as the foundations began to be laid on Sunday. The building is due to be completed in 2015. China State Construction Engineering Corporation will build the mega-mosque, Al Arabiya reports. It will also feature a library containing one million books and manuscripts, a museum and a research center. The new mosque will be one of the world’s largest. Only those in Saudi Arabia’s Mecca and Medina, one in Iran’s Mashhad and one in Bhopal, India are capable of welcoming more worshippers. One of Europe’s biggest mosques is situated in Grozny, Russia’s Chechen Republic. The world’s highest mosque resides on the 158th floor of the tallest manmade structure – the 830-meter Burj Khalifa in Dubai. The world’s tallest mosque is currently the Hassan II Mosque in Casablanca, Morocco. Its minaret is 210 meters tall. The Prophet's Mosque in the city of Medina is 105 meters high. Read more
  • ትኩስ መረጃ leak from government about mejlis mercha

    ወንድሞችና እዚህ የሚገለጹ መረጃዎች ዝም ብለው እንዲነበቡ ብቻ ሳይሆን ከተነበቡ በሁዋላ ሁሉም በተቻለው አቅም መረጃውን በማዳረስም ሆነ የጸረ ሙስሊሞችን ሴራ ለማኮላሸት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ሀላፊነታችንን እንድንወጣ ጭምር ነው፡፡ ትኩስ መረጃ 1. የፌዴራል ጉዳዮች የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ ከሰኔ 13 እስከ 15 እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል፡፡ ምርጫውን በድንገት ህዝቡ ሳያስበው ለማካሄድና ቶሎ ለማጠናቀቅ ጥድፊያ ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ምርጫውን በቀበሌ በኩል ለማድረግና ህዝቡን ከረመዳን በፊት ለመሸወድ ስላሰቡ በገጠርም በከተማም የምንገኝ ሁሉ በየቀበሌያችን ያሉ እንቅስቃሴዎችን በጥብቅ መከታተል አለብን፡፡ በየወረዳችንና ዞናችን የሚገኙ የመጅሊስ ተወካዮችንም እንቅስቃሴ በደንብ እንቃኝ፡፡ ምክንያቱም የሽወዳ ስራ ለመስራት እንዳሰቡ ታውቆባቸዋል፡፡ ትኩስ መረጃ 2. ምርጫን በተመለከተ ጨምሮ የደረሰን መረጃ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ በድጋሚ ለምርጫ መወዳደር መወሰኑንና ለምርጫ ቅስቀሳም ከሰሞኑ ሀረር ኮምቦልቻ ለሳምንት ያህል ከርሞ መመለሱ ተሰምቷል፡፡ ብር ለአካባቢው ህዝብ ሁሉ ሲበትንም እንደነበር ይነገራል፡፡ ፌዴራል ጉዳዮች ከኦሮሚያ ከሚመረጡ 50 የኦሮሚያ ተወካዮች 30 ሰዎችን መርጦ የጨረሰ ሲሆን 20ዎቹ ግን በህዝብ ይመረጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ሆኖም ከእነዚህ ህዝብ ከሚመርጣቸው 20 ተወካዮች መካከልም ፌዴራል ጉዳዮች የራሱን ሰዎች ለማስረግ ጥረት ያደርጋል፡፡ የመጅሊስ አመራሮችም በሙሉ ከሰሞን ለቅስቀሳ ወደየክልላቸው ይጓዛሉ፡፡ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ ሰሞንን ለመጅሊስ ሰራተኞች እኛ ሰልጣን ብንለቅ እንኳ ተመርጠው የሚመጡ ሰዎች እኛ ካስቀመጥነው መንገድ ውጪ የመሄድ አማራጭም መብትም የላቸውም ብሎ ተናግሯል፡፡ አስመራጮችን በተመለከተ ፌዴራል ጉዳዮች ከኦሮሚያ ለሚመጡ 190 የአህባሽ ስልጠና የወሰዱ አስመራጮች ከዚህ ሰምንት ጀምሮ የ9ቀን ስልጠና ይሰጣል፡፡ ትኩስ መረጃ 3. በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ አባዲ ዘሙ መንግስት የአህባሽን ስልጠና እንዲያካሂድ ከአሜሪካ መንግስት 250 ሚሊዮን ዶላር መቀበሉንና ስልጠናውንም ሊያቆም እንደማይችል ሱዳን ኤምባሲ ውስጥ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን አብዱላሂ ጨሎም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሊባኖስ ቤሩት ከሚገኘው የአህባሾች ግሎባል ዩኒቨርሲቲ ጋር የአህባሽን ስልጠና በዘላቂነት ለመስጠት ፍርርምና ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከሰሞኑ ሀረር ውስጥ ገልጧል፡፡ አወሊያንም ትናንሽ ስልጠናዎች ሰጪ በማድረግ በሂደት ግን የአህባሽ ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ መታሰቡም የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት አህመዲን ተናግሯል፡፡ ትኩስ መረጃ 4. የመጅሊስ አመራሮች በአሁኑ ሰአት የብር ፈሰስ የሌላቸው መሆኑ የታወቀ ሲሆን ሳኡዲ ለሐጅ በሄዱበት ወቅት ዘርፈው በኢትዮጵያ ቆንስላ በአደራ ያስቀመጡትን 8 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ አልቁድስ ጋዜጣም በብር እጥረት ምክንያት ክፍያው ቆሞበታል፡፡ ለዚህም ነው ከባለፈው ሳምንት ወዲህ ወሃቢያ እያለ ማላዘኑን ያቆመው፡፡ ትኩስ መረጃ 5. የመንግስት ሚዲያዎች በተለይም አዲስ ዘመን ሙስሊሞችን ማሻማቀቁን ቀጥሎበታል፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ ዘመን ወሀቢያ እና ሱፊያ እያለ የሂላፍ አጅንዳዎችን በተከታታይ ለማተምና የተገኘውን አንድነት ለመናድ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ ትኩስ መረጃ 6. የአዲስ አበባ መጅሊስን አስመልክቶ ፕሬዚዳንቱ ሰይድ ግዛውና ዋና ጸሐፈው ሁሴን ኑረዲን ከፍተኛ ጸብ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ የፀባቸው መንስኤ ብር ሲሆን ሁሴን ኑረዲን በግሎ መልምሎ ባስቀጠረው ምክትል ፕሬዚዳንት በኩል የፈለገውን ደብዳቤ እያስፈረመ ፕሬዚዳንቱን ድጋፍ አልባ ያደረገው ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ሰይድ ግዛውም ሁሴን ኑረዲን በመርዝ ይገድለኛል ብሎ በመስጋት አዲስ አበባ መጅሊስ ውስጥ ማኪያቶ እና ቡና እንኳ መጠጣት ማቆሙ ተሰምቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁሴን ኑረዲን ምርጫ እንዳይወዳደርና በምትኩም ሌላ ስራ እንደሚሰጠው በመንግስት ቃል ተገብቶለታል፡፡ የአዲስ አበባ መጅሊሱ ሁሴን ኑረዲን በየቦታው ቲሸርት የለበሱና ተክቢራ ያሉ ሰዎች ላይ በማስመስከር ለእያንዳንዱ መስካሪ 1300 ብር እየከፈለ ይገኛል፡፡ መስካሪዎቹ ፍርድ ቤት ሄደው ከመመስከራቸው በፊት ምን ብለው መመስከር እንዳለባቸው የአዲስ አበባ መጅሊሱ ሁሴን ኑረዲን እና አቶ ሰይድ ኢብራሂም የተባለ ለምስክርነት በመጅሊሱ የተቀጠረ ሰው ገለጻ እንደሚሰጧቸው ታውቋል፡፡ ትኩስ መረጃ 7. የአዲስ አበባ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስብሰባ ጠርቶ የነበረ ቢሆንም በብዙዎቹ ቦታዎች 500 ሰው ተጠርቶ የተገኘው 30 እና 40 ስው ብቻ በመሆኑ በብዙዎቹ ቦታዎች ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ስብሰባዎቹ በተካሄዱባቸው ቦታዎች በየመስጊዱ ተክቢራ የሚሉና የሚያስብሉ ሰዎችን አሳልፋችሁ ስጡን ብለው ጠይቀዋል፡፡ ግን ስብሰባዎች ብዙም ሳይሳካላቸው ቀርተዋል፡፡ Read more
  • የጎንደር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ከሚያዚያ 08/2004 ጀምሮ የምግብ ማቆም አድማ እንደሚያደረጉ ተገለጸ

    የጎንደር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ከሚያዚያ 08/2004 ጀምሮ የምግብ ማቆም አድማ እንደሚያደረጉ ተገለጸ፡፡ምክንያቱንም ሲናገሩ መጋቢት 19/2004 ዓ.ም በጂሲ ካምፓስ በቁርዓን ሽንት ቤት ተጠቅሞ ሲጸዳዳ እጅ ከፍንጅ የተያዘው የዩኒቨርሲቲው ባለደረባ ከእስር መለቀቅን ተከትሎ የሚደረግ ነው ማለታቸውን የዜና ምንጫችን ከጎንደር አስታውቋል፡፡የምግብ ማቆም አድማው እስከመቸ እንደሚቆይ የታወቀ ነገር የለም፡፡ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ኡኡ የመንግስት ያለህ…… ኡኡ የፍትህ ያለህ….. የጎንደር የአራቱ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊምተማሪዎች ድምጽ ይሰማ…… ኡኡ የፍትህ ያለህ…..ኡኡኡ ለዜናየ መነሻ እንዲሆነኝ አንድ ነገር ልጥቀስ፡፡በአውሮፓዊቷ ሀገር ዴንማርክ አንድ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ነብዩ ሙሀመድን(ሰ.ዓ.ወ)በካር ቶን ስዕል በመሳሉ በተነሳው ችግር ሀገሪቱ በየወሩ 7.3 ቢሊዮን ዩሮ ኪሳራ ይደርስባት እንደነበርና ሰውየው ለፍርድ ቀርቦ የቅጣት ውሳኔ ካገኘ በኋላ እንደድሮው ባይሆንም ለአመታት ገቢዋ እንደቀነሰ የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ሁሉም ሙስሊም ሀገራት ከዴንማርክ የሚገዙትን ሸቀጣሸቀጥ በማቆማቸው ነበር ይህ ሁሉ ኪሳራ የደረሰባት፡፡ወደ ርዕሴ ልመለስ፡፡ አርብ የካቲት 22/2004 በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጂሲ ግቢ ሽንት ቤት ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች የቁርዓን ቅዳጅ በአይነ ምድር ተለውሶ ወይም ሰገራ ታብሶበት ያገኛሉ፡፡በሁኔታው ግራ የተጋቡት እነኚህ ተማሪዎች ጉዳዩን በሚስጥር ይይዙትና ክትትላቸውን ይቀጥላሉ፡፡ድርጊቱ በድጋሜ ፈጸማል፡፡ በጉዳዩየተበሳጩት እነዚህ ጥቂት ሙስሊም ተማሪዎች የራሳቸውን ዘዴ መቀጠስ ጀመሩ፡፡ነገሩን ለሁሊም ሙስሊም ተማሪዎች ቢናገሩ የሚመጣውን አደገኛ ችግር ለመፍታት ዘዴ ቀየሱ፡፡ 1. ጉዳዩን ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቢያሳውቁ እንንተ ናችሁ ይህንን ያደረጋችሁ ሊባሉና ችግሩ ወደራሳቸው እንደሚመጣ ግምት ውስጥ በማስገባት ጉዳዩን በሚሥጥር በመያዝ ድርጊቱን የሚፈጽመውን ግለሰብ እጅ ከፍንጅ መያዝ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስቀመጡ 2. ጉዳዩ ከተወሰኑ ሙስሊም ተማሪዎች በስተቀር ሌሎች እንዳይሰሙ በሚስጥር እንዲያዝ ወሰኑ፡፡ 3. ሰውየው እጅ ከፍንጅ እስኪዝ ድረስ ሰዓታቶች ተከፋፍለው ተማሪዎቹ ዋርድያ እንዲወጡ ተወሰነ፡፡ጥበቃውም በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠንከር ያለ ውሳና አስተላለፉ፡፡ 4. ሰውየው ምን አልባት ቢገኝ ምን እርምጃ ይወሰድበት በሚለው ዙሪያም ከፍተኛ ውይይት ካደረጉ በኋላ ለህግ ማቅረብብቻ እንደሚገባ ወሰኑ፡፡ 5. የሰውየውን ማንነት መለየት፤ተማሪ፣የከተማ ነዋሪ ወይም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ እንደሆነ መጀመሪ ማረጋገጥና እጅ ከፍንጅ በመያዝ ድርጊቱን ሲፈጽም በፎቶግራፍና በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ መያዝ እንደሚኖርባቸው ውሳኔ አሳለፉ፡፡ እንደተባለው ጥበቃው እንደ ነገሩ ክብደት እየከበደና እየረቀቀ መጣ፡፡የነዚህ ተማሪዎች ተስፋ በከንቱ አልቀረም፡፡ሁለተኛውን ድርጊት ከፈጸመ ከጥቂት ቀናት በኋላሌሊት የተለመደውን ተግባር ለመፈጸም አንድ ግለሰብ ወደ ሽንት ቤቱ አመራ፡፡ዘብ ነበሩት ተማሪዎች ሰውየውን ሲከታተሉት ወዘ ልውጥ የነርሱ ግቢ ሰው አለመሆኑን አረጋገጡ፡፡እንግዳ ፊት፡፡ሽንት ቤት ተጠቅሞ ሲወጣ ተከታትለው ሲገቡ የቁርዓን ቅዳጁ አይነ ምድር ተለውሶ ያገኛሉ፡፡ጠባቂዎቹ በነገሩ ቢበሳጩም በትግዕስት ሰውየውን ተከትለው ቤቱ ሲገባ ያዩታል፡፡እዚያው አካባቢ ቁጭ ብለው በማንጋት ማንነቱን ለዩ፡፡የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ሞግዚትና የደህንነት ሰራተኛ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ አሁን ነበር ትልቁ ፈተና የመጣው፡፡ተረኛ ሆነው ያደሩት ዘብ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ካምፓሳቸው ተመልሰው ጉዳዩን ለሚያውቁት ሙሉ መረጃውን ይነግሯቸዋል፡፡በነዚህ ብልህ ተማሪዎች መካከል አለመግባባት ተፈጠረ፡፡በጉዳዩ የተበሳጩትእርምጃ መውሰድን ቢመርጡም ከብዙ ውይይት በኋላ መስማማት ላይ ተደረሰ፡፡ሰውየው እንደለመደው ሊጠቀምበት ሲመጣ እንደሚይዙት እርግጠና ነበሩ፡፡ጥበቃው ሽንት ቤት ውስጥ ሆነ፡፡ጉዳዩን የሚፈጽመው ግለሰብ የሚያድረው ከዘቦች ቤት እንደሆነ ተረጋገጠ፡፡ግን ለምን ቤት እያለው ያለሥራ ቦታው ያውም ጥበቃ ሰራተኞች ቤት እንዲተኛ ተደረገ፤ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል፡፡ ስለ ሰውየው መያዝ፡- ሙስሊም ተማሪዎቹ 27 ቀናት ያለመታከት ሌሊት ሽንት ቤት ውስጥ እየተፈራረቁ ከጠበቁ በኋላ መጋቢት 19/2004 ግለሰቡ እንደለመደው ከጥበቃ ሰራተኞች ቤት ወጥቶ ሽንት ቤትከተጠቀመ በኋላ በጁ ይዞት በነበረው የቁርዓን ቅዳጅ ሊጠቀምሲል “አላህን ፍራ የያዝከው የጌታ(የአላህ) ቃል ስለሆነ አትጠቀምበት በማለት በፎቶና በቪዲ ይቀርጹት ጀመር፡፡የያዘው የቁርዓን ቅዳጅ አጨማትሮ “ምን ታመጣላችሁ”በማለት ከሱሪው የመቀመጫ ኪስ ከቶ ለመማታትና ለማምለጥ ቢሞክርም አልቻለም፡፡የቁርዓኑን ቅዳጅ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁትም አሻከፈረኝ አለ፡፡ግብረ አበሮቹ በመምጣት ምንአደረጋችሁ በማለት ለማስለቀቅና ለማስመለጥ ሞከሩ፡፡አልተሳካም፡፡ ከዚያም ግርግር በመነሳቱ ሰውየው ከነግብረ አባሮቹ ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡ የሙስሊም ተማሪዎች መስማትና መሰባሰብ፡- ጉዳዩ 27 ቀናት ሽንት ቤት ውስጥ በጥበቃ መከራቸውን ሲያዩለነበሩት ጥቂት ተማሪዎች አላህ አስደሰታቸው፡፡የ4ቱ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎችም በደቂቃዎች የጎንደር ዩኒቨርሲቲህክምና ሳይንስ ኮሌጅን ቅጥር ግቢ አጥለቀለቁት፡፡ውጥረት ነገሰ፡፡ግን ሙስሊም “ሰላም” ነውና በርጋታ ጉዳዩን መጠየቅና መስማት ጀመሩ፡፡አዎ ውጥረት ነገሰ፡፡የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕረዚደንት፣የተማሪዎች ዲን፣የጥበቃ ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለሥልጣናት ሙስሊም ተማሪዎችን ተቀላቀሉ፡፡ሁሉም ተማሪዎችም ሆኑ የዩኒቨርሲቲውባለሥልጣናት የአንድ ቀን ውጤት መስሏቸው ነበር፡፡ግን አይደለም፡፡ነገር ግን ውይይቱ ተጀምሮ ጉዳዩን ይከታተሉት ከነበሩት ውስጥ አንዱ 27 ቀናት በሽንት ቤት ውስጥ ስላሳለፉት ችግርና ይህንንም ያደረጉት ከሌሎች ሙስሊም ካልሆኑ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር የነበራቸው ሰላም እንዳይደፈርስና የዩኒቨርሲቲውን ሥም ለማስጠበቅ እንደነበርሲያስረዳ ወንዶች ከመድረክ ፊትለፊት ሴቶች ደግሞ ከበስተጀርባ የተሰማቸውን ሀዘን በእንባ እየተራጩ መግለጽ ቀጠሉ፡፡የማይረሳ ቀን ነበር፡፡የተማሪዎች ዲንም ምንም እንኳ ሙስሊም ባይሆንም በሁኔታው በማዘን በእንባ ሲታጠብ ውሏል፡፡በዙሪያቸው የነበሩ ፖሊሶች እንኳ በተማሪዎች ምርጥሥራ ተገርመው ያዳምጡ ነበር፡፡ ሙስሊም ተማሪዎችም የሰውየውን ሁኔታ ማወቅ እንፈልጋለን በማለት ጥያቄያቸውን ማቅረብ ጀመሩ፡፡የውይይቱ ድባብ ተቀየረ፡፡በተለይ የሰውየው ሁኔታ ሲታወቅ ተማሪዎቹ እጅግ ተበሳጩ፡፡አንድ ውሳኔ እስኪሰሙም እንደማይንቀሳቀሱ አሳወቁ፡፡የዩኒቨርሲቲው ም/ፕረዚደንትም ጉዳዩን ከያዙት ወንድሞች ጋር በመሆን ውሳኔያችንን እንሳውቃችኋለን ጠብቁ ብለው ተሰናበቱ፡፡ሁሉም ምሳውን እዚያው ተመገቡ፡፡ሁሉም እህሉ እንደመረራቸው ያስታውቃል፡፡ከአስር ሰላት በኋላ ም/ፕረዚደንቱና ተማሪዎች ተመልሰው መጡ፡፡ተማሪዎች ምላሹንለመስማት ጓጉተዋል፡፡ሁሉም ነገር ጸጥ አለ፡፡የዩኒቨርሲቲውአስተዳደር የወሰነው ውሳኔ ቀረበ፡፡ 1. ዩኒቨርሲቲው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታግለሰቡን ከሥራ ማባረሩን አሳወቀ፡፡ 2. ዩኒቨርሲቲው ግለሰቡ ይህንን ተግባር ሊፈጽም የቻለበት ዓላማና ተልዕኮ ምን እንደሆነ እንደሚመረምርና ጉዳዩን በራሱ የህግ ባለሙያዎች ተከታትሎ ውሳኔ እንደሚያሰጥ ቃል ገባ፡፡ 3. ጉዳዩንም ሁሉም ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መከታተልእንደሚችሉ አስታወቀ፡፡ 4. ጉዳዩም በፍርድ ቤት እንደሚታይና ለዐቃቤ ሕግ እንደተሰጠ በማስረዳት ሙስሊም ተማሪዎች 27 ቀናት በትግዕስት ተሞልተው የተማሪዎችን ሰላም በማስጠበቅ ወንጀለኛውን በመያዛቸው አመስግነው ወንጀለኛውን እንደሚያስቀጡት ድስኩር አሰሙ፡፡ 5. በዚህ የ12 ሰዓት ቆይታ ሙስሊም ተማሪዎች ሙስሊም ባልሆኑ አንዳንድ ግለሰቦች የተፈጸመባቸውን፣የሚፈጸም ባቸውንና ሊፈጸምባቸው የታቀዱትን ጉዳዮች በማንሳት እየደረሰባቸው ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣እየደረሰባቸው ያለው ግፍና በደል እንዲቆምላቸው የሚጠይቅ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል፡፡ውይይቱም በሰላም ተጠናቀቀ……………. የወንጀለኛው መለቀቅ፡- ይህ ከባድ ወንጀለኛ የተከሰሰው በጎንደር ወረዳ ፍርድ ቤት ነበር፡፡ሆኖም ወንጀሉ ክባድ በመሆኑ እኛ የማየት ሥልጣን የለንም በማለት ወደ ሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይገፋዋል፡፡የሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤትም እኔን አይመለከተኝም በማለት ወደ አማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይልከዋል፡፡ይህም ፍርድ ቤት ወደ ፌደራል ይልከዋል፡፡ነገሩክብደት ተሰጥቶታል፤ በሚል ፍትህ ልናገኝ ነው እያሉ ሲጠብቅለነበሩት የአራቱ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች፣የጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብ፣ጉዳዩን ለሰሙት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን አንጀታችንን የሚሳርር ውሳኔ ተሰጠ፡፡ሰውየው ቀኑን በውል ባላውቀውም (ሚያዚያ 1 ወይም 2)/2004 በ15000.00(አስራ አምስት ሽህ ብር)ዋስተለቀቀ፡፡እርግጠኛ ሁኑ፡፡በዓይናችን በብረቱ ስላየነው፡፡ሁላችንም ግራ ተጋባን፡፡ዕውን ፍትህ አለ ለማለት ተገደናል፡፡ለዚህ ነው ኡኡኡኡኡአ የፍት ያለህ…… የመንግስት ለህ ያልነው፡፡ ጥያቄ፡ 1. ጉዳዩ በመጀመሪያ እንደተፈጸመ ለሁሉም ሙስሊም ተማሪዎችቢነገራቸው ምን ይከሰት ነበር 2. ተማሪዎቹ 27 ቀን ሽንት ቤት እያደሩ በብርድ እየተንሰፈሰፉ የያዙትን “በዘመኑ ቋንቋ” ትልቅ አሸባሪ እንደያዙት ቢገድሉትስ ኖሮ 3. ተማሪዎቹ እንደሰሙ እረብሻ ቢያነሱ ኖሮ በሁሉም አካባቢዎች(ዩኒቭረሲቲዎች ) ምን ሊከሰት እንደነበር ገምተዋል 4. አንድ ሙስሊም (አያደርገውም እንጅ)መጽሀፍ ቅዱስን ለሽንት ቤት መጠቀሚያ ቢደርግ እውን በዋስትና ይወጣ ይሆን ይህንን ልተወው፡፡ ግለሰቡ ይባስ ብሎ ከተፈታ በኋላ በተማሪዎች የመኝታ ክፍል ዙሪያ፣በካፌዎችና በዙሪያው እየተንጎራደደ ድሮ ሽፍታ ከዚያም ወታደር ከዚያ ደህንነት ነኝ እያለ እነዚያን ለሰላም የተዋደቁ ምስኪን ሙስሊም ተማሪዎች ማሰፍራራት መጀመሩ ለምን ይሆን፡፡ለነገሩ”ጌታዋንየተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች”ይባል የለ፡፡ምን ይደረግ! ለነርሱ አላህ አላቸው፡፡ ማጠቃለያ፡- 1. ይህ ግለሰብ ሙስሊሞችንና የሌላ ዕምነት ተከታይ ተማሪዎችን በማፋጀት የዩኒቨርሲቲውን ሰላም፣የሀገራችንን ሰላምለማደፍረስና ሀገራችን ከሌሎች ሙስሊም ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንገኙነት በማሻከር ካለብን ድህነት ላይ ሌላ ድህነት ለመጨመር ዓላማው አድርጎ የተነሳን ግለሰብ በዋስ መልቀቅ ምን ይሉታል ፍትሀዊ ነው ይገርማል፡፡ለነገሩ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” ይባላልእኮ….. 2. ዩኒቨርሲቲው ለሙስሊም ተማሪዎች የገባውን ቃል ለምን አልጠበቀም ለነገሩ ከማን የተማረውን 3. ዩኒቨርሲቲው ምናልባት ምንም አያመጡም ብሎ አስቦ ከሆነ ችግረ አለ ችግርም ይኖራል፡፡ወንጀለኛውም እነዚህን ምስኪንተማሪዎች ከማስፍራራት የማይቆጠብ ከሆነ…… ሰውየው ሌላ ተልዕኮ አለው ማለት ነው 4. መንግስት በዚህ ግለሰብ ላይ አፋጣኝ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ሁሉም ሙስሊሞች ጉዳዩን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች በማሳወቅ የሙስሊሙን ችግር ማሳወቅ ኖርብናል፡፡ስለዚህ ሁላችንም ለዚህ ዝግጁ እንሁን፡፡ Read more
  • ጠላታችን ኢሃዲግ ወይስ መጅሊስ?

    ጠላታችን ኢሃዲግ ወይስ መጅሊስ? ~~~~~~~~~~~~~~~~ “እኛ ድል ያደረግነው ለጥያቄያችን መልስ በማግነታችን ሳይሆን ማን ጠላታችን እንደሆነ ማወቃችን ነው”። ብዙዎቻቹህ ይህንን ርዕስ ስትናቡ ልተካፉ ወይም ሌላ ነገር ታስቡ ይሆናል።ያም ሆነ ይህ “እውንትን ትናግሮ የመሸበት ማደር “ እንዲሉ የሚከፋ ሰው በኖርም የመከፋት መብቱን እያከበርኩ እኔ ግን ለቀጥል:-- ወደ ርዕሴ ስገባ :-ባለፈው አንድ ክርስቲያን ወዳጄ እንዲህ አለኝ “እናንተ ሙስሊሞች! ለምንድን ነው መንግስት አህባሽን በናንተ ላይ መጫኑን እያወቃቹህ መንግስትን በመቃዎም ፋናታ ለምን መጅሊስን ትቃወማላቹህ? አሃያውን ፈርቶ ዳውላን አይሆንም ? የመጅሊስ አመራሮችን የሾመው መንግስት መሆኑን አያወቃቹህ እነዚህን አመራሮች የሾመውን መንግስትን ከመተቸት ይልቅ ለምን የመጅሊስ አመራሮችን ትትቻላቹህ ?“ ብሎ ጠየቀኝ! ይህ ጥያቄ የ አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ ሰውች ብቻ ሳይሆን የኔም በመሆኑ ለናንተ ለማቅረብ ወደድኩ። እንደሚታወቀው ዶክተር ሰሚር በጊዎን በተደረገው ስበሰባ ላይ በመንግስት(በ ኢሃዲግ) ተጋብዘው በመምጣታቸው ለመንግስት ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረባቸው ይታወሳል።ሰለዚህ “አህባሽን መጅሊስ ነው ያመጣው “ የሚለው አባባል ተረት ያደርገዋል። እንዲሁም በተደጋጋሚ ሙስሊሞን የመከፋፈል እና የሙስሊምን ስም የማጥፋት ዘመቻ ሲሰራብን የነበረው የመንግስት ሚዲያዎች እንጂ የመጅሊስ ሚዲያዎች አልነበሩም።ሙስሊምን ለመከፋል የሚሞክሩ አካላት የኛ ጠላት ከሆኑ ታዲያ ጠላታችን ማን ነው?ይህ ብቻም አይደለም ሙስሊምን ለሁለት በመክፈል ከፊልን “ሱፊ” ከፊልን “ውህቢያ” ብለው ሲያበቁ “ዋህቢያ” ያሉትን ክፍል ከመድረ ገጽ እናጠፋለን ብለው በተደጋጋሚ የፎከሮት እነ ዶክተር ሺፈርውን የያዘው የ ኢሃዲግ መንግስት ነው። ሙስሊም ይህንን ሁሉ እያወቀ ሰላም ወዳድ ከመሆኑ የተነሳ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ሲል ።መንግስት መበደሉን እያወቀ “አይ! እኛን የበደለን መጅሊስ እንጂ መንግስት አይደለም”እያለ ።አንድ ዲንጋይ ሳይወረውር የማንንም መበት ሳይገፋ ፤በኢትዮዲያ ታሪክ ውስጥ ማንም ያላደረገውን ከ አራት ወር በላይ የፈጀ ታላቅ ሰላማዊ ታቃውሞ አድርጓል።ይህንን ፍጹም የሆነ ተቃውሞ ለማደናቀፍ መንግስት የተለያዩ ደህንነቶች በመላክ ለማደናቀፍ የልፈነቀለው ድንጋይ የለም።በ አላህ እርዳት ሊከሽፍ ችሏል !!አላሁ አክበር!! መንግስት ይህንን ታላቅ ፤ለረጅም ጊዜ የፈጀ ተቃውሞ ፍጹም ሰላማዊ መሆኑን እያወቅ “በሃያማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ጸረ ህገመንግስት ፤ጸረ ሰላም ናቸው” ሲል አድምጠነዋል!ለመሆኑ ጸረ ህገመንግስት ማለት ምን ማለት ነው? ህግን አክብሮ በሃጋዊ መንገድ ሂዶ ህገመንግሳታዊ መብቴ የከበር ማለት እንዴት ሆኑ ነው ህገወጥነት የሚባለው? እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ህገወጥነት ማለት ህግ ይከበር ያለ ሳይሆን ህግን በመጣስ በሃያማኖታችን ውስጥ “ሸህ ነኝ” እያለ ልክ እነደዓሊም ፈትዋ እየሰጠ ያለው እንደነ ዶክተር ሸፈርው አይነቱን የሰበሰበው የኢሃዲግ መንግስት ነው።አላህ ሂዳያ ይስጣቸው ከማለት ውጪ ምን አንላቸው።እኛ እንደነሱ አይደለንምና ። በሰተመጨረሻም እኛ ሙስሊሞች ባደረግነው እልክ አስጨራሽ ትግል ትልቅ ድል አግኝተናል ከድሎች ሁሉ ድል የጠላቶቻችንን ሴራ ማክሸፋችን ነው።እነሱ አህባሽን ያመጡልን አንድነታችንን ለመናድ፤የሙስሊሙን ንቃተ ሂሊና ለመግደል፤ባለፈው ጠቃላይ ሚኒስቴሩ እንደገለጹን ታቦት ሸኚ መስሊም ለማድረግ ነበር።በ አላህ እርዳታ ግን ይህ ሁሉ ሊከሽፍ ችሏል።አላሁ አክበር!! ሙስሊም በ አሁን ሰአት ከየትኛውም ጊዜ በላይ እንደነቱን ጠብቃል፤ነቃተ ህሊናውም በጣም ከፍ ብሏል ።አላህምዱሊላህ ። يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ የ አላህን ብርሃን በ አፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ አላህም ከሐዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑ ገላጭ ነው። (ቁርኣን ሱረቱ አል -ሶፍ 8) አላሁ አክበር!!አላሁ አክበር!!!አላሁ አክበር!! Read more
  • Be Gonder universit Qur'an'n le shent bet yeteqemewu ye islam telat ke eser benetsa tefeta

    Be Gonder universit Qur'an'n le shint bet sitekem ej ke finj yeteyazaw wonjelegna ke esir telekeke.Minm enkuan be video ena be kal yetedegefe merja bikerbibetm sewyew be netsa be universitew ena be akababiw sinkesakes taytual! Ye gondar university muslim temariwoch keftegna wutret lay nen.bemalet yegonder universti temariwoch geltswal ye ethiopia mengest ke qereb gize wedi be ethiopian muslim lay eyaderege yalewu bedel be sefiwu eyeqetele mehonu yetaweqal Read more
  • በጎንደር ሃያ ሙስሊሞች መታሰራቸው ተገለፀ

    ጎንደር ሃያ ሙስሊሞች መታሰራቸው ተገለፀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 5/2004 በጎንደር ፎገራ ወረዳ አርማጮ ከተማ ለመስጂድ በተሰጠ ቦታ ላይ ሆቴል እንዲሰራ ያለአግባብ በመፈቀዱ የአካባቢው ሙስሊሞች ተቃውሞ በማሰማታቸው ሃያ ሰዎች ከመስጂድ ተወስደው መታሰራቸው ተገለፀ፡፡ የመስጂዱ ግንባታ እየተፋጠነ ባለበት ሁኔታ በኢንቨስትመንት ሽፋን ሆቴል በመስጂዱ ደጃፍ ላይ እንዲሰራ በመፍቀዱ የአካባቢው ሙስሊሞችና የመስጂዱ ኮሚቴዎች ለመንግስት አካላት አቤት ቢሉም እስከ አሁን ፈጣን ምላሽ አለማግኘታቸው ታውቋል፡፡ እንደ አካባቢው የሬዲዮ ቢላል ምንጭ መስጂዱ አዛን እንደማይባልበትና ሰላት እንዳይሰገድበት በከተማው የፀጥታ ዘርፍ አላፊ ታሽጓል ፡፡ የታሰሩት 20 ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ጉዳዩን ለመመርመር የ5 ቀን ቀጠሮ ጠይቆ እንዲቆዩ ቢያደርግም ነገር ግን በትላንትናው ዕለት እንዲፈቱ በፖሊስ ትህዝ ተላልፎላቸው ነበር ሰዎቹ ግን ያለአግባብ እንደታሰሩና ፍትህ ሳያገኙ ከእስር ቤቱ እንደማይወጡ መግለፃቸውን ከምንጫችን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመስጂዱ ኮሚቴዎች ጉዳያቸውን ለዞን እና ለክልል የመንግስት አካላት በማቅረብ ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ የአካባቢው ሙስሊም ህብረተሰብ በድርጊቱ እንደተቆጣና በሽማግሌዎችና በኮሚቴው አካላት አማካኝነት እንዲረጋጉ መደረጉንና ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ እንደሆነ ከአካባቢው ምንጭ ለመረዳት ተችሏል፡፡ Read more
  • ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም በ አክራሪዎች ላይ እጄን አጣጥፌ አልቀመጥም አለ

    በየመስጊዱ ሕዝበ ሙስሊሙ የዓርብ ፀሎትን በሰላም እንዳይፀልይ በማወክ በግልጽና በህቡዕ የሚንቀሳቀሱ አካላት በሃይማኖት ሽፋን ሰላም ከማደፍረስ የማይቆጠቡ ከሆነ፣ እጁን አጣጥፎ እንደማይመለከት መንግሥት አስገነዘበ፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም የመሥርያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ትናንት ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፣ በግልጽና በህቡዕ በመንቀሳቀስ የአገሪቱን ሰላምና ልማት የሚያውኩትን ፀረ ሰላም ኃይሎች መታገስ ሰላም ወዳዱን ሕዝብ ለአደጋ ማጋለጥ ነው፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ሕዝበ ሙስሊሙ እነዚህን አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች እንዲመክራቸው፣ እንዲገስጻቸውና ለይቶ በማጋለጥ የተለመደ ትብብር እንዲያደርግ እያሳሰብን፣ እነዚህ አካላት በሃይማኖት ሽፋን ሰላማችን ከማደፍረስ የማይቆጠቡ ከሆነ መንግሥት እጁን አጣጥፎ እንደማይቀመጥ ማስገንዘብ ይፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ጥቂት አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች ሕዝበ ሙስሊሙን በማደናገር፣ በመደለልና በማስፋራራት የአክራሪነት እንቅስቃሴያቸውን በይፋ ማራመድ መጀመራቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ እነዚህ ኃይሎች በተለይም አዲስ አበባን እንደ ማዕከል በመጠቀም በኦሮሚያና ሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች የአክራሪነት ፍላጐታቸውን በግድ ለመጫን እየተንቀሳቀሱ መሆኑን፣ ባይሳካላቸውም ሕዝበ ሙስሊሙንና መንግሥትን ለማጋጨት አልመው ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችንና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የተለያዩ ማደናገሪያ አጀንዳዎችን በማስተጋባት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ለሕዝበ ሙስሊሙ ባለው ጥልቅ እምነትና ከበሬታ፣ እንዲሁም የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ባለው ዝግጁነት በአወሊያና በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጉዳይ ጥያቄ አለን ብለው መንቀሳቀስ የጀመሩ ግለሰቦችን ሲያወያይ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ሽፈራው፣ የእነዚህ ወገኖች ጥያቄ ማጠንጠኛ የነበረውን የሕዝበ ሙስሊሙን ተቋም የሆነውን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተያዘለት የድርጊት መርሐ ግብር መሠረት ሕዝበ ሙስሊሙን በሰፊው በሚያሳትፍ መንገድ እንዲፈጸም ድጋፍ እንደሚያደርግ መንግሥት ቢገልጽም፣ ጥያቄ አለን በሚሉ ግለሰቦች ውስጥ የተሸሸጉና ከእነሱም በስተጀርባ ድብቅ የትርምስ አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ግለሰቦች ሕዝበ ሙስሊሙን በማደናገር ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ እርሳቸው እንዳሉት፣ በመንግሥት በኩል እነዚህ ጥቂት አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ሰላማዊና ሕገ መንግሥታዊ መንገድ ተከትለው እንዲጓዙ ያልተቋረጠና ያልተቆጠበ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የዜጐቹን ሰላም ወዳድነት በመተማመንና የአክራሪ ፀረ ሰላም ኃይሎቹ ማንነትና ድብቅ ፍላጐት በሕዝቡ ውስጥ በግልጽ እስከሚታወቅ ድረስ በትዕግስት ጠብቋል ብለዋል፡፡ Read more
  • በአሰሳ በቤት ለቤት አሰሳ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑ ተጠቆመ

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 4/2004 በአርሲ ዞን አሰሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊም የሕብረተሰብ ክፍሎች ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ለሬዲዮ ቢላል ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከተማዋ ቀበሌ 02 ኑር መስጂድ ሚያዚያ 19/2004 የተከሰተውን ሁከትና ግርግር ተከትሎ የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች ከሚያዚያ 23 ቀን ጀምሮ የአካባቢውን ሙስሊም ነዋሪዎች ቤት ለቤት በመፈተሸ የቤት እመቤቶችንና አባወራዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ስማችን እንዳይጠቀስና ድምጻችን እንዳይቀረጽ ያሉ የአሳሳ ነዋሪዎች እንዳመለከቱት የፀጥታ ኃይሎች የቤት ለቤት አሰሳውና እስር እያካሄዱ ያሉት ከአልቃኢዳና አሸባሪ ቡድኖች ጋር የግንኙነት መረብ አላቸው በሚል ነው፡፡ከዚህ ባለፈ ግነ መረጃ ለመስጠት ስጋትና ፍርሀት እንዳለባቸው ነው የገለጹት፡፡ ባለፈው አንድ ሳምንት በካሄዱት አሰሳም ከ90 በላይ የሚሆኑ አባወራ ዑለሞች ኡስታዞችና ወጣቶችን ጨምሮ የቤት እመቤቶች በመኪና ተጭነው መወሰዳቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ወደ ሻሸመኔ መስመር ሳይወሰዱ እንዳልቀረ ነው ምንጮች ግምታቸውን የሰጡት፡፡ በሻሸመኔ ከአራት ቀናት በፊት 44 ሴቶችና 50 ወንዶች ከአሳሳ በጸጥታ ሀይሎች ተይዘው መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡እነዚሁ 94 አስረኞች በአሁኑ ወቅት በሻሸመኔ ከተማ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ Read more
  • “Call me a terrorist but I will defend my religion!! < one of the popular website muslim.net report about ethiopian muslim

    ADDIS ABABA — Defying government threats, Ethiopian Muslim have vowed to continue their protests against the “Ahbashism Campaign” instigated by the government and “Majlis”. “Call me a terrorist but I will defend my religion,” a muezzin in a mosque at the outskirts of Addis Ababa said in his sermon, denouncing the Al Ahbash movement, Reuters reported. Over the past few weeks, Muslim protests have been causing concern in the predominantly Christian nation that takes pride in centuries of coexistence. Thousands of Muslims have protested against the government's oppression of their community, accusing it of spearheading a campaign in collaboration with the Majlis to indoctrinate Muslims with the ideology of a sect called "Ahbash". Protesters were further infuriated when Ethiopian police shot dead seven Muslims in Assasa town in Arsi province of Oromiya regional state two weeks ago. Witnesses say the Muslim victims fell when Ethiopian security forces surrounded a mosque to arrest Sheikh Su'ud Aman on accusations of prompting “terrorist” ideology. Scores of people were also reportedly injured in the incident. Observers said the brutal killing of innocent people in Assasa town has fueled tension between the government and the Muslim community. Muslims say the government is spearheading a campaign in collaboration with the Supreme Council of Islamic Affairs to indoctrinate their community with the ideology of a sect called "Ahbash". The government of Ethiopian Premier Meles Zenawi has put the Ahbash in charge of the religious affairs of Ethiopia's Muslims. Muslims say the government move is in violation of the constitution, which prevents the government interference in religious affairs. Muslims also accuse the Ahbash of launching an "indoctrination program" in predominantly Muslim areas, forcing people to attend "religious training" camps or risk police interrogation and possible arrest. Founded by Ethiopian-Lebanese scholar Sheikh Abdullah al-Harari, Ahbash is seen by the West as a "friendly alternative" to Wahabi ideology, which the West sees as extreme and militant. Muslims say Ahbash imams are being brought over from Lebanon to fill the Majlis and teach Ethiopians that “Wahabis” are non-Muslims. Interference Ethiopian Muslim activists confirmed that protesters reject any government interference or trial to impose Ahbashism ideology on their society. “It (Al Ahbash) has the right to exist in Ethiopia, but it is unacceptable that the Council tries to impose it on all members of the Muslim community,” Abubeker Ahmed, an Ethiopian Muslim activist and head of an independent Islamic arbitration committee, told Reuters. He said the government wanted to prevent a vote to elect a new council and replace the decade-old one. He added that the appointed leadership of Ethiopia's Islamic Affairs Supreme Council was not representative of the country's Muslim community. “They (the government) want to keep them because they agree to whatever orders,” he said. Rejecting the government claims that hardline Islam was taking root in the Horn of Africa country, some protesters say the government's strategy might backfire, sowing the seeds of the hardline Islam it seeks to keep at bay. “We are against any sort of extremism ourselves,” said Ahmed Mustafa, secretary of the independent arbitration panel. “We want to stop such thinking.” Ethiopia, Africa's second most populous country, is home to 60 percent Christian and about 34 percent Muslim, according to CIA factbook. Reproduced with permission from OnIslam.net Source: OnIslam Read more

Latest Articles

Most Popular