Fresh opportunity for illegals in Saudi Arabia to correct status
የዘንድሮው የሳውዲ የምህረት አዋጅ
==============================
* የምህረት አዋጁ ለ3 ወራት ወይም ለ90 ቀናት የጸና ይሆናል !
* ምህረት አዋጁ ህገ ወጥ የሆኑትን ብቻ ይመለከታል
* በላቅ " የተደረገና የተበላሸ መኖሪያ ፈቃድ ማስተካከል አይቻልም
* በምህረት አዋጁ ማንኛውም ህገ ወጥ ዜጋ ያለ መቀጮና እስር ወደ ሀገር መሄድ ይችላሉ
* የወጡት ዜጎች በህጋዊ የስራ ስምምነት ወደ ሳውዲ መመለስ ይቻላሉ
* መኖሪያ ፈቃድ ግን አልተፈቀደም
የምህረት አዋጁን ይፋ ያደረጉት የሳውዲ አልጋ ወራሽ ሲሆኑ ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ ትዕዛዝ መሆኑ ተጠቁሟል ። የምህረት አዋጁ በሳውዲ ተቀማጭ የሆኑ ህገ ወጥ የውጭ ሃገር ዜጎችን ይመለከታል ። በዘመቻው ከዚህ ቀደም እስርና ቅጣት የተጣለባቸው የውጭ ዜጎች መቀጮ ሳይከፍሉና እስር ቤት ሳይገቡ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ይረዳል ተብሏል ።
በተለይም በሃጅ በኡምራ፤ በጉብኝት የገቡ ህገ ወጥ ነዋሪዎች ወደ የትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት መሄድ አይጠበቅባቸውም ። በባህር ፤ በአየርና በየብስ ወደ ሀገራቸው መግባት ይችላሉ ። ከዚህ በተጨማሪ በኮንትራት መጥተው ከአሰሪያቸው የጠፉ ፤ ጠፉ ተብሎ የተከሰሱ ”በላቅ “ የተደረገባቸውና በመሳሰሉት መኖሪያ ፈቃዳቸው የተበላሸባቸውን ዜጎች ወደ ሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እየቀረቡ ጉዳያቸውን በመከወን ያለ መቀጮ በቀጥታ ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ የምህረት አዋጁ በዋናነት ይጠቅማል ተብሏል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሀ የምህረት አዋጅ በየትኛውም መንገድ የመኖሪያ ፈቃድ አልተፈቀደም ፤ " በላቅ " የተደረገና የተበላሸ መኖሪያ ፈቃድ ማስተካከል አይቻልም ። ያልሆነውን ይሆናል እያሉ ዘረፋ ከሚያደጉት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ።
በዚህ የምህረት አዋጅ የወጡ ከዚህ ቀደም የጣት አሻራ ሰጥተው እንዲዎጡ እንደተደረጉት የጣት አይወሰድባቸውም ። በዚህ የምህረት አዋጅ የወጡ የማንኛውም ሀገር ዜጎች በህጋዊ የስራ ስምምነት ወደ ሳውዲ መመለስ ይቻላሉ። በሃጅ ጸሎት ወቅት ፈቃድ ሳይኖራቸው ሀጅ በማድረጋቸው ህግን የተላለፉና የተያዙና አሻራ ያደረጉም በዚህ ምህረት አዋጅ ያለ ቅጣት ወደ ሀገር መሄድ እንደሚችሉ ከሳውዲ መንግስት የወጣ መረጃ ያስረዳል ።
ከምህረት አዋጁ ጋር የወጣው ሌላ መረጃ እንዳስታወቁት በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ሚሲዮኖች ፤ ኢንባሲዎችና ቆንስል መስሪያ ቤቶች ስለ ምህረት አዋጁ በሳውዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኩል ዝርዝር መረጃው እንደተላለፈላቸው ታውቋል ። በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ የገቡ የመጓጓዣ ሰነድ የሌላቸው ወደ ሃገራቸው ለመላክ ግዴታ ከሀገራቸው ተወካይ ኢንባሲና ቆንስሎች የመጓጓዣ ሰነድ መታዎቂያ መያዝ ይገባቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለሶስት ወር ወይም ለ90 ቀን የተሰጠው የምህረት አዋጅ ከያዝነው ወር መcጭረሻ እጎአ March 29 /2007 ጀምሮ ይጸናል ። እጎአ በ2013 ተመሳሳይ የምህረት አዋጅ ወጥቶ 2.5 ሚሊዮን የውጭ ዜጎች ሳውዲን ለቀው መውጣታቸው አይዘነጋም ።
በ2013 የምህረት አዋጁ ሲጠናቀቅ ሪያድ መንፉሃ ከፍተኛ ሁከት ተከትሎ የሞቱና የቆሰሉ ኢትዮጵያውያን ነበሩ ። በግርግር ሁከቱ የደረሰው እስካሁን በውል ባይገለጽም በወቅቱ ሳውዲን ለቀው ከወጡት መካከል መካከል 180 ሽህ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ሳውዲን ለቀዋል መውጣቸው ይታወሳል ።
የግል አስተያየቴ ...
===========
* የኢንባሲና ቆንስል ተወካዮች ዜጎችን ለማስተናገድ ከፍተኛ ትብብር ሊያደርጉ ይገባል
* የሰው ሃይል እጥረት ካለ “ጉዳዩ ያገባናል ” ያሉ ግለሰቦች ነጻ ግለጋሎት ልትቀበሉ ይገባል
* ከዚህ ቀደም የተስተዋለው የሰው ሃይል እጥረት ፤ ቅንጅትና የመረጃ ክፍተት ሊወገድ ግድ ይላል
* ዜጎች የተሰጠው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ከሁሉም ዜጎች ቀና ትብብር ይጠበቃል
* በዚህ የምህረት አዋጅ ተከትሎ የማይሆነውን ሆነ እያሉ ዜጎችን ከሚዘርፉ ደላሎች እንጠንቀቅ
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 12 ቀን 2007 ዓም
አንድ ነገር ልጠይቅ ነበር አሻራ አንስተው ከሀገር የወጡ ወደሳውዲ መመለስ ይችላሉ ሲባል ከምህረቱ ጋር ነው ወይስ ከምረቱ በፊት የወጡት ለስራ ቢመጡ አሻራው እንደት ነው መልሱን አሁኑኑ ላክልን ቻው