አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 21/2004
በሐረር ክልል ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እንዲሁም ከሐረር ከተማ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ ዑለሞች የራሳቸውን የዑለሞች ምክር ቤት አቋቋሙ ካቋቋሙት ምክር ቤት በተጓዳኝ የፈትዋ ዳዕዋ ኮሚቴ አደራጅተዋል፡፡
አዲስ የተቋቋመው የሐረር ክልል ዑለሞች ምክር ቤት አባል ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት ምክር ቤቱን በክልል በዞንና በወዳ ደረጃ ማቋቋም ያስፈለገው የቀድሞው መጅሊስ አመራር አባላት በክልሉ ሕዝበ ሙስሊም እውቅና የተነፈጋቸው በመሆኑ ነው፡፡
ነባሩ መጅሊስ አመራር በክልሉ ህዝብ እውቅና የተነፈገው በመሆኑም ህብረተሰቡ ኢስላማዊ አገልግሎት የሚሰጥ የተደራጀ አካል በማስፈለጉ የዑለሞች ምክር ቤት ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስረፍተዋል፡፡
በዚህም መሰረት የምዕራብ ሀረርጌ ወረዳዎችን የሚወክሉ አባላት ያሉት ሐረርጌ ወረዳዎችና ከሐረር ከተማ የተውጣጡ 20 አባላት ያሉት የዑለሞች ምክር ቤት መቋቋማቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከሁለቱም ዞኖችና ዳዕዋ ኮሚቴዎች የዑለሞች ምክር ቤቶች ጋር በጥምረት የሚሰሩ የፈትዋና ዳዕዋ ኮሚቴዎች መደራጀታቸውንም የዑለሞች ምክር ቤቱ አባል አስረድተዋ፡፡
የዑለሞች ምክር ቡቱ ነበሩ መጅሊስ ያተወጣቸውን ኃላፊነቶች ለመወጣት የሚያሻሽሉት ዝርዝር የሥራ ኋላፊነት እንደሚኖር ተናግረዋል ፡፡
መድረሳ የማቋቋም ዳዕዋ የማካሄድ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት የማጠናከር ፣በሀገራዊ ጉዳቶች ተሳትፎ እንዲያደርግ የማበረታቻ ፣ፀረ ኢስላም አቋሞችንና አመለካከቶችን የመታገል ኃለፊነቶች እንደሚኖሩት አብራርተዋ፡፡
በተመሳሳይ የፈትዋና የዳዕዋ ኮሚቴው ማብራሪያ በሚፈለጉ ጉዳዮች ላይ ከሸሪኸው አንፃር ማብራሪያ የመስጠትና የዳዕዋና ኹጥባ ፕሮግራሞችን የማስተባበር ኃላፊነት እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡
የዑለሞች ምክር ቤቶች አባላት በህዝብ ሠፊ ተቀባይነት ያላቸው ዑለሞች ፣የመስጂድ ኢማሞች የአገር ሽማግሌዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የሁለቱ ዞን ዑለሞች ምክር ቤት በክልል ደረጃ ሃጂ ቀመር አብዱላሂ የፈትዋና የዳዕዋ ኮሚቴውን ደግሞ ሸህ ጀማል ሰኢድ በሊቀመንበርነት እንደሚመሩት ለማወቅ ተችሏል፡፡
Read more