BILAL TUBE NEWS AMHARIC

  • Be Gonder universit Qur'an'n le shent bet yeteqemewu ye islam telat ke eser benetsa tefeta

    Be Gonder universit Qur'an'n le shint bet sitekem ej ke finj yeteyazaw wonjelegna ke esir telekeke.Minm enkuan be video ena be kal yetedegefe merja bikerbibetm sewyew be netsa be universitew ena be akababiw sinkesakes taytual! Ye gondar university muslim temariwoch keftegna wutret lay nen.bemalet yegonder universti temariwoch geltswal ye ethiopia mengest ke qereb gize wedi be ethiopian muslim lay eyaderege yalewu bedel be sefiwu eyeqetele mehonu yetaweqal Read more
  • በጎንደር ሃያ ሙስሊሞች መታሰራቸው ተገለፀ

    ጎንደር ሃያ ሙስሊሞች መታሰራቸው ተገለፀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 5/2004 በጎንደር ፎገራ ወረዳ አርማጮ ከተማ ለመስጂድ በተሰጠ ቦታ ላይ ሆቴል እንዲሰራ ያለአግባብ በመፈቀዱ የአካባቢው ሙስሊሞች ተቃውሞ በማሰማታቸው ሃያ ሰዎች ከመስጂድ ተወስደው መታሰራቸው ተገለፀ፡፡ የመስጂዱ ግንባታ እየተፋጠነ ባለበት ሁኔታ በኢንቨስትመንት ሽፋን ሆቴል በመስጂዱ ደጃፍ ላይ እንዲሰራ በመፍቀዱ የአካባቢው ሙስሊሞችና የመስጂዱ ኮሚቴዎች ለመንግስት አካላት አቤት ቢሉም እስከ አሁን ፈጣን ምላሽ አለማግኘታቸው ታውቋል፡፡ እንደ አካባቢው የሬዲዮ ቢላል ምንጭ መስጂዱ አዛን እንደማይባልበትና ሰላት እንዳይሰገድበት በከተማው የፀጥታ ዘርፍ አላፊ ታሽጓል ፡፡ የታሰሩት 20 ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ጉዳዩን ለመመርመር የ5 ቀን ቀጠሮ ጠይቆ እንዲቆዩ ቢያደርግም ነገር ግን በትላንትናው ዕለት እንዲፈቱ በፖሊስ ትህዝ ተላልፎላቸው ነበር ሰዎቹ ግን ያለአግባብ እንደታሰሩና ፍትህ ሳያገኙ ከእስር ቤቱ እንደማይወጡ መግለፃቸውን ከምንጫችን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመስጂዱ ኮሚቴዎች ጉዳያቸውን ለዞን እና ለክልል የመንግስት አካላት በማቅረብ ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ የአካባቢው ሙስሊም ህብረተሰብ በድርጊቱ እንደተቆጣና በሽማግሌዎችና በኮሚቴው አካላት አማካኝነት እንዲረጋጉ መደረጉንና ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ እንደሆነ ከአካባቢው ምንጭ ለመረዳት ተችሏል፡፡ Read more
  • ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም በ አክራሪዎች ላይ እጄን አጣጥፌ አልቀመጥም አለ

    በየመስጊዱ ሕዝበ ሙስሊሙ የዓርብ ፀሎትን በሰላም እንዳይፀልይ በማወክ በግልጽና በህቡዕ የሚንቀሳቀሱ አካላት በሃይማኖት ሽፋን ሰላም ከማደፍረስ የማይቆጠቡ ከሆነ፣ እጁን አጣጥፎ እንደማይመለከት መንግሥት አስገነዘበ፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም የመሥርያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ትናንት ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፣ በግልጽና በህቡዕ በመንቀሳቀስ የአገሪቱን ሰላምና ልማት የሚያውኩትን ፀረ ሰላም ኃይሎች መታገስ ሰላም ወዳዱን ሕዝብ ለአደጋ ማጋለጥ ነው፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ሕዝበ ሙስሊሙ እነዚህን አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች እንዲመክራቸው፣ እንዲገስጻቸውና ለይቶ በማጋለጥ የተለመደ ትብብር እንዲያደርግ እያሳሰብን፣ እነዚህ አካላት በሃይማኖት ሽፋን ሰላማችን ከማደፍረስ የማይቆጠቡ ከሆነ መንግሥት እጁን አጣጥፎ እንደማይቀመጥ ማስገንዘብ ይፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ጥቂት አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች ሕዝበ ሙስሊሙን በማደናገር፣ በመደለልና በማስፋራራት የአክራሪነት እንቅስቃሴያቸውን በይፋ ማራመድ መጀመራቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ እነዚህ ኃይሎች በተለይም አዲስ አበባን እንደ ማዕከል በመጠቀም በኦሮሚያና ሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች የአክራሪነት ፍላጐታቸውን በግድ ለመጫን እየተንቀሳቀሱ መሆኑን፣ ባይሳካላቸውም ሕዝበ ሙስሊሙንና መንግሥትን ለማጋጨት አልመው ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችንና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የተለያዩ ማደናገሪያ አጀንዳዎችን በማስተጋባት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ለሕዝበ ሙስሊሙ ባለው ጥልቅ እምነትና ከበሬታ፣ እንዲሁም የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ባለው ዝግጁነት በአወሊያና በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጉዳይ ጥያቄ አለን ብለው መንቀሳቀስ የጀመሩ ግለሰቦችን ሲያወያይ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ሽፈራው፣ የእነዚህ ወገኖች ጥያቄ ማጠንጠኛ የነበረውን የሕዝበ ሙስሊሙን ተቋም የሆነውን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተያዘለት የድርጊት መርሐ ግብር መሠረት ሕዝበ ሙስሊሙን በሰፊው በሚያሳትፍ መንገድ እንዲፈጸም ድጋፍ እንደሚያደርግ መንግሥት ቢገልጽም፣ ጥያቄ አለን በሚሉ ግለሰቦች ውስጥ የተሸሸጉና ከእነሱም በስተጀርባ ድብቅ የትርምስ አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ግለሰቦች ሕዝበ ሙስሊሙን በማደናገር ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ እርሳቸው እንዳሉት፣ በመንግሥት በኩል እነዚህ ጥቂት አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ሰላማዊና ሕገ መንግሥታዊ መንገድ ተከትለው እንዲጓዙ ያልተቋረጠና ያልተቆጠበ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የዜጐቹን ሰላም ወዳድነት በመተማመንና የአክራሪ ፀረ ሰላም ኃይሎቹ ማንነትና ድብቅ ፍላጐት በሕዝቡ ውስጥ በግልጽ እስከሚታወቅ ድረስ በትዕግስት ጠብቋል ብለዋል፡፡ Read more
  • በአሰሳ በቤት ለቤት አሰሳ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑ ተጠቆመ

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 4/2004 በአርሲ ዞን አሰሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊም የሕብረተሰብ ክፍሎች ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ለሬዲዮ ቢላል ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከተማዋ ቀበሌ 02 ኑር መስጂድ ሚያዚያ 19/2004 የተከሰተውን ሁከትና ግርግር ተከትሎ የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች ከሚያዚያ 23 ቀን ጀምሮ የአካባቢውን ሙስሊም ነዋሪዎች ቤት ለቤት በመፈተሸ የቤት እመቤቶችንና አባወራዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ስማችን እንዳይጠቀስና ድምጻችን እንዳይቀረጽ ያሉ የአሳሳ ነዋሪዎች እንዳመለከቱት የፀጥታ ኃይሎች የቤት ለቤት አሰሳውና እስር እያካሄዱ ያሉት ከአልቃኢዳና አሸባሪ ቡድኖች ጋር የግንኙነት መረብ አላቸው በሚል ነው፡፡ከዚህ ባለፈ ግነ መረጃ ለመስጠት ስጋትና ፍርሀት እንዳለባቸው ነው የገለጹት፡፡ ባለፈው አንድ ሳምንት በካሄዱት አሰሳም ከ90 በላይ የሚሆኑ አባወራ ዑለሞች ኡስታዞችና ወጣቶችን ጨምሮ የቤት እመቤቶች በመኪና ተጭነው መወሰዳቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ወደ ሻሸመኔ መስመር ሳይወሰዱ እንዳልቀረ ነው ምንጮች ግምታቸውን የሰጡት፡፡ በሻሸመኔ ከአራት ቀናት በፊት 44 ሴቶችና 50 ወንዶች ከአሳሳ በጸጥታ ሀይሎች ተይዘው መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡እነዚሁ 94 አስረኞች በአሁኑ ወቅት በሻሸመኔ ከተማ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ Read more
  • የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ባልጨረሱ ፖሊሶች ተደበደቡ

    የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠና ባልጨረሱ ፖሊሶች ተደበደቡ -በጥይትና በከባድ ድብደባ የተጎዱ ተማሪዎች ህክምና ላይ ናቸው -የከተማው ነዋሪም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል ትላንት ለተቃውሞ በወጡ የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ታጣቂዎችበጥይትና በዱላ ጉዳት ማድረሳቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ከትላንት በስቲያ እሁድሚያዝያ 28 እና ትላንት ሰኞ ሚያዝያ 29 በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ሊከሰትየቻለው ተማሪዎች ተጓደለ ያሉትን የምግብ ጥራት በመቃወማቸው እንደሆነምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ እሁድ ሚያዝያ 28 ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በተቀጣጠለው በዚህ ተቃውሞ አብዛኛው ተማሪቁጣውን የዩኒቨርስቲውን መስታወቶች በመሰባበር እንደገለፀ የሚናገሩት ምንጮቻችንምሽት ላይ በድንገት ወደ ግቢው የገቡት ታጣቂዎች ተማሪዎቹ ላይ ከመጠን ያለፈኃይል በመጠቀም ጉዳት እንዳደረሱ ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ በታጣቂዎች በተወሰደውእርምጃ ከ60 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸውና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ላይድብደባ እንደተካሄደ ታውቋል፡፡ በወቅቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከፍተኛ የተኩስእሩምታ የተሰማ ሲሆን ኢብራሂም መሀመድ የተባለ የ2ኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ በጥይት መመታቱ ታውቋል፡፡ ተማሪው በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳትበደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ በመከታተል ላይ እንደሚገኝ ፍኖተ ነፃነት ስፍራው ድረስ በመደወል አረጋግጣለች፡፡ ተማሪ ኢብራሂም መሃመድ በስልክ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፀው ከትላንት በስቲያ ምሽት ታጣቂዎቹ በቀጥታ በጥይት እግሩ ላይ መተውአቁስለውታል፡፡ ሌላው በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመበት የ2ኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ የሆነውና ከትግራይ ክልል የመጣው ገብረ ኪዳንብርሃኔ ትላንት ጠዋት በጀርባውና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ለዝግጅት ክፍሉ ተናግሯል፡፡ በትላንትናው እለት ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ‹‹የታሰሩ ተማሪዎች ይፈቱ›› የሚል ጥያቄን ይዞ የቀጠለው ተቃውሞ ቀስ በቀስ ከዩኒቨርሲቲው ውጪመስፋፋቱን ከከተማው ያገኘናቸው መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ ተቃውሞው በደብረ ማርቆስ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በቀጠለበት ወቅት በርካታ የከተማውነዋሪዎችም ትዕይንቱን ተቀላቅለው ጥያቄው ፖለቲካዊ ይዘት ተላብሶ ገዢውን ፓርቲ በማውገዝ እና ለኑሮ ውድነቱ ገዢውን ፓርቲ መኮነናቸውንምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ታጣቂቆች ቶክስ በመክፈታቸው ተቃውሞው ተበትኗል ሲሉ ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ በሁኔታውየተደናገጡት ተማሪዎች ወደ ተለያየ አቅጣጫ ሲበታተኑ ታጣቂዎችና ፖሊሶች አብዛኞቹን እያፈሱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዳጓጓዟቸው የከተማው ነዋሪዎችለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ወደ ህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ አፈሳው እንደቀጠለ ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም በድብደባዉከተጎዱ ተማሪዎች መካከል አይናቸዉ ተመትቶ ኡፕራሲዮን የተደረጉ እንደሚገኙበት አስረድተዋል፡፡ ከስፍራው የደረስን መረጃ እንደሚያመለክተውበተማሪዎቹ ላይ እርምጃ የተወሰደው ስልጠናቸውን ባልጨረሱ ፖሊሶች ጭምር መሆኑን ያመለክታል፡፡ ማምሻውን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተውአሁንም በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ዩኒቨርሲቲውና ወደ ደብረማርቆስ ሆስፒታል ደውለን ምላሽወደ ህትመት እስከገባንበት ሰአት ድረስ ምላሽ ማግኘትአልቻልንም፡ Read more
  • በአሰሳ በእስር ከሚገኙት መካከል 100 የሚሆኑት ወዳልታወቀ ስፍራ መዛወራቸው ተነገረ

    በአሰሳ በእስር ከሚገኙት መካከል 100 የሚሆኑት ወዳልታወቀ ስፍራ መዛወራቸው ተነገረ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 27/2004 ከሳምንት በፊት በአሰሳ የተፈጠረውን ግርግር ተከትሎ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው 185 የሚሆኑ ሰዎች መካከል የተመረጡ 100 ወጣቶች ወደ ማይታወቅ ስፍራ መዛወራቸውን የአካባቢው ምንጮች አመለከቱ ፡፡ ምንጮቻችን እንዳመለከቱት ከሆነ የተመረጡት ወጣቶች ከአራት ቀናት በፊት ከአሰሳ ማረሚያ ቤት ጨለማን ተገን በማድረግ ወዳልታወቀ ስፍራ በመኪና ተጭነው ተወስደዋል፡፡ ከተወሰዱት ወጣቶች መካከል አንደኛው የሌላ እምነት ተከታይ ስለመሆኑ መታወቂያውን በማሳየት በሰጠው ማረጋገጫ ከተለቀቀ በኋላ ለማወቅ መቻላቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ወጣቱ ባደረሳቸው መረጃ መሰረትም ከአሰሳ ማረሚያ ቤት ተመርጠው የተወሰዱት ወጣቶች የሚገኙበት ስፍራ በግምት ከከተማዋ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ካለ ልዩ ማቆያ ቦታ ሳይሆን እንዳልቀረ አብራርተዋል፡፡ Read more
  • Breaking News Zare Arsi Asesa Mengest Bezu Muslimochn Cherese (gedele)

    Zare Arsi Asesa Mengest Bezu Muslimochn Cherese ;( Breaking News(B asasa 4 sewoch motu! Andet?)Zare k jum'a selat buha b asasa ketama yalu muslimoch tesebsebew b da'awa lay iyalu b fedral police baltaweke huneta tekebebu mnw sibalu sw falegen bemalat saweyewun liwasdut silu yaw yemi wasdubat mekneyat hulachenem and menakew nw b botaw yeneberew umma ayhonem b melat qretawun siyasama police emmedietily wede toks nw yagabut b toks arat(4) sewoch simotu wede 10 mitagut demo qoslowal. "Bemeketel demo manena yet hagar hedo nw migalut?"Insha Allah Zerzerun Radio Bilal eskemizegbew dress Le Muslimu DUaa Adregu Allah Ke weyane Gedayochna Ke Ahbashoch Tenkol Yitebken, Read more
  • የ”አልቁድስ” ጋዜጣ ከመጅሊስ የበጀት ድጋፍ እንደሚደረግለት ተገለፀ

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 13/2004 የመጅሊስ አመራር በህዝበ ሙስሊሙ ላይ አስከትሏቸዋል በተባሉት ችግሮች ዙሪያ በአወሊያ ተቃውሞውን እያሰማ በሚገኘው ህዝበ ሙስሊም ህዝበ መሀል ይፋ የሆነው መረጃ ነው-የአልቁዱስ ጋዜጣ ከመጅሊስ የበጀት ደጋፈ እንደ ሚያገኝ ያጋለጠው፡፡ የጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ከቅርብ ወራት ወዲህ በተደጋጋሚ የሚያወጧቸው ዘገባዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ውዥብር መፍጠራቸውን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡በዚህ ሁኔታ ላይ ተመሳሳይ ችግሮች ያሉባቸውን ዘገባዎች ዛሬም ይዞ መምጣቱን የቀጠለበት የአልቅዱስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ትላንት በአወሊያ ለ12ኛ ጊዜ በተካሄደው ሰላማዊ የመብት ማስከበር ሕዝባዊ ንነቅናቄ ላይ ከመጅሊሱ ለአንድ የጁምዐ ህትመት እስከ 22ሺብር የሚደርስ የበጀት ድጋፍ እንደተደረገለት ይፋ ሆኗል ፡፡ ለአንድ ወር 88 ሺ ብር ከመጅሊስ እንደተሰጠውም ተናግሯል፡፡ ለዚህም በማስረጃነት ቀረበው የመጅሊሱ ማህተም ያረፈበት ደብዳቤ ነው፡፡ መረጃውን ይፋ ያደረገው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው አባልና የታሪክ ፀሀፊው አህመዲን ጀበል ነበር፡፡ የአልቁድስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የመጅሊስን ድክመት በማጋለጥ ትታወቅ የነበረ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ግን ሙሉ በሙሉ የመጅሊስን አቋም የሚያንፀባርቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ Read more
  • teqlay minsiter Melses zenawi sele ahbash be parlam tenagere

    መለስ ዜናዊ ብቻውን በሚያስተዳድረው ፓርላማ የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ በራሳቸው መንገድ ተርጉሞታል በንግግሩ ውስጥ በተደጋጋሚ ሲያነሳው የነበረው አንዱን ሱፊያ አንዱን ሰለፍያ እያለ መከፋፈል ነው የማከረው በተጨማሪ ምንም በማይገናኝ መልኩ የኛን ጥያቄ በአሁን ጊዜ እንደ ግብፅ የመን ቱኒዚያ ሊቢያ ከመሳሰሉት ሀገሮች ጋር በማገናኘት እስላማዊ አስተዳደር ይፈልጋሉ ብሎ ተናግሮአል we will post the video soon Read more
  • የኢህአዴግ አመራሮችና አባላት ለሚከተሉት እምነት እላፊ ድጋፍ የሚሰጡበት ሁኔታ መኖሩ ተገለፀ

    አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 8/2004 የኢህአዴግ አመራሮችና አባላት በሚከተሉት እምነት በመንግስት በህዝብ በተሰጣቸው ኃላፊነት መካከል የሚወራውን ድንበር በማለፍ እላፊ ድጋፍ የሚሰጡበት ሁኔታ መኖሩን አንድ ሰነድ አመለከተ፡፡ በሰላምና በህገ መንግስቱ ዙሪያ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር የዜጎችና የመንግስት መብትን ግዴታም ነው በሚል ርዕስ በቅርቡ በኢህዴግ ፅ/ቤት የወጣው ሰነድ እንዳመለከተው የድርጅቱ አመራሮችና አባላት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ለሚከተሉት እምነት እላፊ ድጋፍ ሲሰጡ የሚታዩበት ሁኔታ በርካታ ነው፡፡ እንደ ማሳያም በአንዳንድ አዓላት ሀገሪቱን የኃይማኖቶች መቻቻልና መከባበር ሳይሆን የፉክክርና የፍጥጫ ማዕከል እንደሆነች በሚያስመስል መልኩ ድጋፍ ሲሰጡ ይታያል ነው ያለው ሰነዱ፡፡ የጋራ የሆኑ የመንግስት አደባባዮች፣ቢሮዎች፣የሌላ ኃይማኖት ተከታይ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችና አጥሮች ጭምር በአንድነት ምልክቶችና የሌላውን እምነት በሚነካኩ እንዲሁም ህገመንግስቱና የሰንደቅ ዓላማ በሚፃረር መልኩ ሲንፀባረቁ የሚተባበሩበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቅሰዋል፡፡ ሰነዱ በእነዚህ ድርጊቶች ተባባሪ ከሆኑና በመጠኑ የተሸሉት ብሎ የጠቀሳቸው ደግሞ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን ሳያስተካክሉ አጥር ጥግ ቆመው የሚመለከቱትን አመራሮችና አባላትን ነው፡፡ እናም አብሮ ማጥፋትና ሌላው ሲያጠፋ እያዩ እንዳላዩ ማለፍ ስህተት ነው ያለው ይኼው ከኢህአዴግ ጽ/ቤት የወጣው ሰነድ በሁለቱም መንገድ ጥፋቶቹ ከመፈፀም የሚገቱበት ሁኔታ አንደማይኖርም አመልክቷል፡፡ ሙስሊምና ክርስቲየን የሆኑ የኢህዴግ አባላትና አመራሮች ይህን ተከተሉ ያን አትከተሉ የሚባሉበት ሁኔታ እንደሌለም ገልፀዋል፡፡ በዚህ ረገድ ችግሩ የሚስተዋለው ከሚከተሉት እምነት ወይም የእምነት ቡድን (ሴክት) ውስጥ መቻቻልን ህገመንግስቱን የሚሸረሽሩ አዝማሚያዎች ሲንፀባረቁ ከድርጅቱ መርህና ከሀገሪቱ ህገመንግስት መንፈስ አንፃር በጥብቅ ዲሲፕሊን የማይታገሉ መሆናቸው እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ የኢህአዴግ አባል የእምነት ነፃነት አለው ሲባል ፀረ ህገመንግስት አቋሞችን የሚያራምድ ድርጅት ወይም በኃይማኖት ሽፋን በሚያስኬድ እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ አለበት ማለት አለመሆኑን አስረድቷል፡፡ በመሆኑም በኢህዴግ አባላትና አመራሮች አቋማቸውን ሳያስተነትኑ ከሚከተሉት እምነት መሰረታዊ አስተምህሮት ፈንጠር ያሉና ፀረ ህገመንግስታዊ መግለጫ ያላቸው አቋሞችን ተላብሰው ይታያሉ ነው ያለው ሰነዱ፡፡ በዚህም መሰረት አንዳንድ የኢህዴግ አባላትና አመራሮች ኢህዴግነትንም ፀረ-ኢህአዴጋዊ አቋሞች የያዙ ቡድኖችንም የሚያንቀሳቅሱበት ሁኔታ በገሃድ እንደሚታይ ነው ሰነዱ ይፋ ያደረገው፡፡ ስለሆነም ከዚህ አንፃር የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ግልፅነት በመፍጠር የአባላቱንና አመራሮቹን አሰላለፍ ማስተካከል እንደሚገባ ለማስተካከል የሚቸገር ደግሞ ከድርጅቱ መፅዳት እንዳለበት ነው ያመለከተው፡፡ ህገ መንግስቱ በኃይማኖት ዙሪያ ካስቀመጣቸው መርሆሆች በመነሳት በአባሉና አመራሩ ዘንድ የጋራ ግንዛቤ መፍጠርና ትግሉም ይህንኑ መሰረት ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቅሷል፡፡ ህገ መንግስቱ ለግለሰብና ለቡድን መብቶች አስተማማኝ ጥበቃ የሰጠውን ያህል መብቶችን ለመተግበር የሚደረጉ እንቅስቃሰሴዎች መከተል የሚገቡ መርሆዎችና ዳር ድንበሮች በዝርዝር እንዳስቀመጠም ጠቅሷል ከኢህአዴግ ፅ/ቤት ለድርጅቱ አመራሮችና አባላት መወያያነት በቅርቡ የወጣው ይህው ሠነድ፡፡ Read more

Latest Articles

Most Popular