BILAL TUBE NEWS AMHARIC

  • Remedan 15 great scilent symbolic protest by shwing white flag at the grand mesjid of Anwar.

    Remedan 15 great scilent symbolic protest by shwing white flag at the grand mesjid of Anwar.
    የአንዋር መስጊዱ የጁምኣ ተቃውሞ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል፡፡ ነጭ ወረቀት ተውለበለበ ye ethiopia muslim selamwinetun eyasaye newu
    menem comitewochachen bitaserum muslimu begirefm bidebedebem selamawi yehone tegelachen eskemechershawu yeqetetale mengest wededem tela teyaqechenen memels yenorebetal allahu akber ledinachen enmotaln

    Read more
  • ነገ August 1/2012 በ 33 የ አራብ ቻናሎች LIVE የሚተላለፍ ታላቅ የቴሌቭዥን ውይይት ፕሮግራም ሊተላለፍ ነው

    ታላቅ የቴሌቭዥን ውይይት ፕሮግራም 
    በ 33 የ አራብ ቻናሎች የሚተላለፍ የቀጥታ ስርጭት (live) የውይይት
    ፕሮግራም ነገ August 1/2012 በሳውዲ ወይም በኢትዩፕያ ሰዓት አቆታተር ከምሽቱ 5 ሰዓት ይተላለፋል። በፕሮግራሙ ላይ በርካታ ተዋቂ ሙስሊም አንግዶች ከ ኢትዮጵያ፣ ከ ሳአዑድ ዓረብያ ፣ ከ አሜሪካ፣ ከ ፈረንሳይ፣ ከ ጣልያን፣ ከ ዋሺንግተን ከ ኒውዮርክ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የ መብት ጥያቄ ትግልን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፋ ያለ አለም አቀፍ ውይይት የሚካሄድበት ፕሮግራም ሲሆን ፕሮግራሙም የሚተላለፍው በቢላል ኮሚኒኬሽን አና በ አረብ ቻናል በጋራ የተዘጋጀ ነው። አንዳያመልጣችሁ ተከታተሉት ታዋቂ የ ሙስሊም ምሁራኖችን ያሳተፈ ልዩ ፕሮግራም ነው ። Read more
  • የኮሚቴዎቻችን ቤት ሲፈተሸ ከተከሰቱ አስደናቂ ነገሮች መሀል በጨረፍታ

    የኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ቤት ሲፈተሽ ፖሊሶቹ አከራዮቹን ‹‹ለዐረብ እንዴት ታከራያለሽ?!›› አሏቸው፡፡ ‹‹አረ የሀበሻ ልጅ፡፡ ያውም ጠንቅቄ የማውቀው የጓደኛዬ ልጅ ነው!›› ብለው መለሱ፤ ባልቴቲቱ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ረዥም ክርክር ካደረጉ በኋላ የኡስታዝ አህመድ ፎቶ ተፈልጎ ኢትዮጲያዊ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ የሚያሳዝኑት ግን አከራይቱ ናቸው፡፡ ኡስታዙን (ዐረቡን) ስላከራዩት ይሁን እኛንጃ የሰባ አመቷ አዛውንት በውድቅት ለሊት ውጪ (ያውም በእንቅላል ፋብሪካ ብርድ እየተሰቃዩ) እንዲያድሩ ተደረጉ፡፡ (ጉድ ነው!) ኢትዮጲያዊ ሙስሊም መብት አይጠይቅም ነው ነገሩ ወይስ መብት መጠየቅ ዜግነት ያስነጥቃል?! 

    ሌላ አጋጣሚ እንጨምር

    ይህኛው የኮሚቴ አባል ባይሆንም ለመብቱ መከበር የሚታትር ኢትጲያዊ ነው፡፡ እርሱን ቤቱ ሄደው ሲፈልጉት አጡት፡፡ ከዚያም ‹‹ፖሊስ ሰንዝሮ አይመለስም!›› ብለው ይሁን እናቱን እና አባቱን ወሰዱ፡፡ እውነትም ፖሊስ ሰንዝሮ አይመለስም! Read more
  • አላሁ አክበር ትላንት በመካ ለ ኢቶዮጵያን ሙስሊም ዱኣ ተደረገ

    ትላንት በ 11 ኛዉ ተራዊ በ ታላቁ የ መካ ኢማም ሱዴሲ ከ ሥስት ሚሊዮን ከ ዓለም የመጡ ሙስሊሞች በተገኙበት እና ከ መቶ ሚሊዮን በላይ በቲቪ በሚያየዉ  ለ ኢትዮጵያ ሙስሊም ዱኣ ተደረገ ዱዓዉም (አላሁ መንሱር ኢትዮጵያን ሙስሊም ይል ነበር አሚን)አልሃምዱሊላ ጉዳያችን አለም አቀፍ እውቅና እያገኘ ነዉ ኢንሻአላህ ቪዶዮ እንደደረሰን እናስተላለፋለን Read more
  • አስደሳች ዜና Ethiopian Muslim be Washington DC yesedeqa ena ye andenet program akahedu

    አስደሳች ዜና
    በዋሽንግተን ዲሲ ና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጽያዊያን ሙስሊሞች ታላቅ የዓንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም አካሄዱ። በዚህ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ በዋሽንግተን ዲሲ ና አካባቢው የሚኖሩ ሙስሊሞች የተሳተፉበት ፕሮግራም በሃገር ቤት መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚያደርሰውን በደልና ግፍ ከማውገዝ በተጨማሪ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም ገልጾል። ዛሬ ቅዳሜ ጁላይ 28 በተካሄደው በዚሁ ፕሮግራም ላይ በእስር ላይ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች አላህ ከጨቆኞች እስር ነጻ እንዲያወጣቸው እንዲሁም በፖሊስ ድብደባና ጭስ ለተጎዱ ወገኖች አላህ አፊያቸውን እንዲመልስላቸው ዱአ ተደርጎል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ የሚገኙት በድር ኢትዮጽያ፣ ፈርስት ሂጅራ፣ ነጃሽ የፍትህ ካውንስል እና ሰላም ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት የኢትዮጽያ ሙስሊም ቅንጅት መስርተዋል። ቅንጅቱም የመጀመሪያ የጋራ ስራ ያደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ሀሙስ ኦገስት 2 ያካሂዳል። ኢንሻአላህ በቀጣይም ቅንጅቱ የታሰሩ እንዲፈቱና የሙስሊሙ መሰረታዊ መብት እንዲከበር ከፍተኛ የሆነ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል። Read more
  • ‎**** ግልጽ ደብዳቤ ለሳሞራ ዩኑስ ****

    ይድረስ ለኢትዮጵያ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ ዩኑስ በመጀመሪያ የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኩኝ ለጤናዎ አንደምን አሉ እላለሁኝ። በመቀጠልም እርሶ እና የትግል ጓዶ ጫካ በመግባት የታገላችሁለት አንዱ አላማ የእምነት ነጻነት ለማረጋገጥ ነበር። ይህንን የእምነት ነጻነት ለማስከበር እነ ቀሽ ገብሬን የመሳሰሉ ከ60,000 በላይ ሰራዊት መስዕዋት ሆነዋል። ዳሩ ግን አሁን እየፈጸማችሁት የለው ነገር ከታገላችሁለት አላማ ውጪ ነው እንዲያውም በተቃራኒው ነው።
    ወደ ዋናው ቁም ነገር ስገባ እርሶ በከባድ ሃላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ ሙስሊም የጦር አዛዥ ኖት ፤ በተለይም በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባልተረጋጋበት ሁኔታ ላይ ከባድ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ ባለስልጣን ኖት። እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰዐት እኛ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መብታችን ተገፎ ብሎም በእስር እየተሰቃየን እና እየተገደልን እንደምንገኝ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በተለይም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚተማመኒባቸው ኡለሞች፣ ዱአቶች፣ ባለሃብቶች እና ሙህሮች በእስር ክፉኛ እየማቀቁ ይገኛሉ።
    በጣም የሚያሳዝነኝ እርሶ የህን ኢስላምን ከኢትዮጵያ የማጥፋት ዘመቻን ዝም ብለው ማየቶ ነው። እንዴት ሙስሊም ሙስሊም ላይ ይጨክናል፤ በኢትዮጵያ ሙስሊም ታሪክ ውስጥ ታሪክ ሲወቅሶ የሚኖር ጥቁር ነጥብ አያሳረፉ መሆኖትን አይዘንጉት። ሳስቦት እርሶ አሁን በዕድሜዮት መባቻ ላይ ነው የሚገኙት፤ ታድያ እንዴት ሰው ከአላህ መጋናኛው በቀረበ ሰዐት ለአላህ ዲን(ኢስላም) ጠላት ይሆናል ነገ አላህ ፊት ለኢስላም ምን ሰራሁ ሊሉ ነው? 
    እኔ ግን አሁን አንድ ነገር ልምከርዎ ፤ እስከ ዛሬ ለኢስላም አንድ የሚታይ ነገር አንዳልሰሩ ግልጽ ነው። ነገር ግን አሁን ሙስሊሙ ኡማ በተቸገረበት ቀውጢ ሰዐት ታሪክ በኩራት ሲዘክሮ የሚኖር ነገር መስራት ይችላሉ ይኸውም እየተደረገብን ያለውን ግፍ በመቃወም እንዲቆም የበኩሎን ጥረት ማድረግ ይችላሉ። አለበለዚያ ግን ነገ ማንም ሰው በማይበደልበት የቂያም ቀን 40 ሚልዮን ህዝብ ይፋረዶታል። በመጨረሻ አላህ ቅኑን ጎዳና እንዲመሮት አለምነዋለሁኝ። 
    ከሰላምታ ጋር
    መህዲ ማይልስ
    Read more
  • የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ቢታሰሩም ተቃዉሞዉ አልተቋረጠም <

    ለጁመዓ ጸሎት በአዲስ አበባዉ የአንዋር መስጊድና በአካባቢው የተሰባሰቡ በብዙ ሽህዎች የሚገመቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዛሬም ተቃዉሞአቸዉን አካሄደዋል

    አስራ ሰባቱም ሙስልም ማህበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና በርካታ የእምነነቱ ተከታዮች ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ መተሰራቸዉ ይታወቃል። ለጁመዓ ጸሎት   በአዲስ አበባዉ የአንዋር መስጊድና በአካባቢው የተሰባሰቡ በብዙ ሽህዎች የሚገመቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዛሬም ተቃዉሞአቸዉን አካሄደዋል። አፋቸዉ እንደተሸበበ በማመልከትና እጆቻቸዉን የፊጢኝ ወደሁዋላ በማሰር መልክና ሌሎች ምልክቶች ጭምር ተቃዉሞአቸዉን እንደገለጹ ተመልክቶአል።

     

    የፌድራል ፖሊስ ኮምሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ወርቅነህ ገበየሁ ሰሞኑን ለመንግስት የመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በቁጥጥር ሥር በዋሉት የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ተጀመረ ያሉትን እንቅስቃሴ ከአክራሪነት ጋር የተያያዘ ብለውታል።

    Read more
  • በአሜሪካ ታላቅ የአንድነት የሰደቃና የዱዓ ፕሮግራም ሊያከናውኑ መሆኑ ታውቀ ,ፕሮግራምን ለመዘገብ አልጀዚራ ቢቢሲ ሲኤንኤን ቪኦኤ ዶቼ ዌሌ ይገኛሉ

    በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች መጪው ቅዳሜ ጁላይ 28 በዋሺንግተን ታላቅ የአንድነት የሰደቃና የዱዓ ፕሮግራም ሊያከናውኑ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይኸው በአሜሪካ የሚገኙ በርካታ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ማህበራት በጋራ ያዘጋጁት ፕሮግራምን ለመዘገብ አልጀዚራ ቢቢሲ ሲኤንኤን ቪኦኤ ዶቼ ዌሌና ሌሎችም ዐለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን ግፍና በደል ለዐለም ህብረተሰብ የማሳወቅ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ኮሚቴዎቻችንንና ሌሎችም በርካታ ንጹሐን ዜጎችን ለእስር መዳረጉን በማውገዝ በመጪው ሳምንት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ውሳኔ ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይም ቀኑ በትክክል መቼ እንደሚሆን 
    ይወሰናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አላሁ አክበር!
    Read more
  • ትኩስ መረጃ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከታሰሩበት ማዕከላዊ ተለቀቁ

    ድምፃችን ይሰማ ትኩስ መረጃ የዛሬው ውሎ
    በመላዉ አለም የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያዉያን ሙስሊሞች በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ የወከሉት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከታሰሩበት ማዕከላዊ ተለቀቁ:: ከጠዎቱ 3 ሰአት ላይ ኡስታዝ አቡበከር እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል አብረዉ በመኪና እየተጏዙ በነበረበት ወቅት አንድ መኪና በከፍተኛ ፍጥነት ወደነሱ መኪና በመምጣት መንገድ ዘግቶባቸዉ ይቆማል:: ወድያዉኑ አራት ሰዎች በፍጥነት ከመኪናዉ በመዉረድ ወደነ ኡስታዝ አቡበከር በመምጣት ኑ ዉጡ በማለት ያንባርቁባቸዎል:: እነሱም መኪና ዉስጥ እንዳሉ ማንነታቹን ሳናዉቅ አንወርድም ሲሏቸዉ ከአራቱ ሰዎች አንዱ የኡስታዝ አቡበከርን መኪና በር በሀይል ለመበርገድ ሙከራ አደረገ:: ማንነታችሁን ከገለፃችሁልን ከመኪናዉ እንወርድላቹኃለን ሲሏቸዉ የፖሊስ መታወቂያቸዉን በማሳየት ከመኪናዉ አስወርደዉ በራሳቸዉ መኪና ጭነዎቸዉ ማዕከላዊ ጎን በሚገኘዉ አዲሱ የአ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ህንፃ ይወስዷቸዎል:: እዛ ከደረሱም ቡሀላ ሁለ ነገራቸዉን የተቀበሏቸዉ ሲሆን ቀበቷቸዉንም ሳይቀር አስወልቀዎቸዉ ነበር:: ሁለቱንም ለየብቻ የተለያየ ክፍል አስገብተዉ ያስቀመጡዎቸዉ ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ከዚህ ቡሀላ በኢትዮጲያ ዉስጥ ለሚፈጠረዉ ችግር በሙላ ተጠያቂዉ አንተ ነህ:: የፊታችን ሐምሌ 8 በአወልያ ይካሄዳል በተባለዉ ፕሮግራም ላይ ለሚፈጠረዉ ከባድ ችግር ሀላፊነቱን የምትወስደዉ አንተነህ በማለት ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተሰቷቸዎል:: ቀጥለዉም ሁለቱንም አንድ ክፍል በማስገባት ሁለት የፀጥታ ሀይሎች ዛቻና ማስፈራሪያቸዉን ተያያዙት:: እናንተ ሀገሪቱን ለማተራመስ እየተንቀሳቀሳቹ ትገኛላቹ:: ከኢትዮጲያ ፀረ ሰላም ሀይሎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቹ በተጨባጭ ደርሰንበታል:: ህገ ወጥ ናችሁ:: በሰደቃ ስም ሀገሪቱን እያመሳችሁት ገኛላችሁ:: ከዚህ ቡሀላ ማንኛዉም አይነት ሰደቃ የሚባል ፕሮግራም እንዳንሰማ:: ከዚህ ቡሀላ ኮሚቴ ነን የምትሉትን አማርኛ አቁሙ:: እናንተ ህገ ወጦች ናችሁ በማለት ማስፈራሪያቸዉን ለመቀጠል ሲሞክሩ ጀግኖቹ የኢስላም ልጆች እኛ ህገወጥ አይደለንም:!!! ህገ ወጥ እናንተናችሁ በማለት አይደለም ማስፈራሪያቸዉን ሊቀበሉ ይቅርና ያለአንዳች መደናገጥ ፅናታቸዉን አሳዩዎቸዉ:: አስፈራሪዎቹም ጩኸታቸዉን ቀጠሉ እጅግ በጣም ተቆጡ:: እኛ እኮ እዚህ ያመጣናችሁ ለስብሰባ አይደለም:: እናንተን አንድም ሙስሊም አልመረጣችሁም:: ህዝብ በድምፁ የመረጠዉ ኢህአዴግን ብቻ ነዉ:: ከዚህ ቡሀላ ኮሚቴ የሚባል ነገር መንግስት አይቀበለዉም:: መንግስት ዝም ሲላችሁ የፈራችሁ መስላችሁ ወይ?? ከዚህ በላይ መንግስት አይታገሳችሁም:: ሀገሪቱን ወደ አላስፈላጊ ነገር እየመራችኃት ስለሆነ በዝምታ አናያችሁም!! ከዚህ ቡሀላ የምናስራችሁ ወይም ፍርድ ቤት የምናቀርባችሁ እንዳይመስላችሁ:: መንግስት የራሱን እርምጃ እንደሚወስድባችሁ እወቁ በማለት ማስፈራሪያቸዉን አዥጎደጎዱት:: የሙስሊሙ ኮሚቴዎችም ያላአንዳች ፍርሀት አስደናቂ ምላሻቸዉን ሰጡ:: እባካችሁ ይህንን ማስፈራሪያችሁን ተዉ!! እኛ የምንፈራችሁ መስሏቹ ከሆነ አትሳሳቱ:: አንድም እናንተን የምንፈራበት ምክንያት የለም:: ለምን አስካሁን እርምጃ አትወስዱብንም ነበር:: ይኸዉ አሁን አጠገባችሁ ስለሆንን ቀጠሮ ለምን ትሰጣላችሁ!! እዚዉ የፈለጋችሁትን እርምጃ ዉሰዱ::እኛ ሞትንም ሆነ እስራትን የምንፈራ አይደለንም:: በማለት ኢስላም ምን ያህል ፅናት እንደሰጣቸዉ አሳይተዎቸዎል:: ይህንን ማስፈራሪያቸዉን ባዶ ካስቀሩባቸዉ ቡሀላ ኡስታዝ አቡበከር አህመድን በቅድሚያ የለቀቁት ሲሆን ከቆይታ ቡሀላም ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን አዘግይተዉ ለቀዉታል:: ኢስላም ሂወታችንን አሳልፈን የምንሰጥለት ሀይማኖት መሆኑን ዘነጉት እንዴ??? አላሁ አክበር!!!! Read more
  • ኡስታዝ አቡበከር አህመድና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የመጨረሻ የሂወት ማስጠንቀቂያ ከመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ተሰጣቸዉ

    ኡስታዝ አቡበከር አህመድና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የመጨረሻ የሂወት ማስጠንቀቂያ ከመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ተሰጣቸዉ
    ለአሚሮቻችን የተሰጠዉ ማሰጠንቀቂያ እኛንም ይመለከታል አሚሮቻችን ማለት እኛዉ ህዝበ ሙስሊም ነን እነሱ ተነኩ ማለት እኛንም እንደሚያካትት{ ይታወቅልን} ይኽ ዛቻም እኛንም ይመለከታል በነገራችን ላይ ኡስታዝ አብበከር በባለፈዉ የያዙትጊዜ ከተለቀቀ በኃላ ያላት ነገር ትዝ አለችኝ
    እኛ የኮሚቴዉ አባላት ህጋዊዉን ጥያቄ ከዳር ለማድረስ ማንኛዉም ዓይነት መስዋአትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን
    እኛስ ያ'ጀመዓ አሚሮቻችን ነኩ ማለት እኛን ህዝበ ሙስሊም ነኩን ማለት ነዉ
    እኛ ሙስሊሞች ከዱኒያ ዲናችንን እንደምናስቀድም አያዉቁም እንዴ
    እቺ ከአሁን በኃላ የመጨረሻ ሂወታቹ ናት የምትሉት ሰዉ ሰራሽ ዛቻ ትቁምልን ትዕዛዙ ከላይ ነዉ በእንደዚህ አይነቱ ዛቻ ሀይል ይጨምርልናል እንጂ ከትግላችን ንቅንቅ አንልም!!! Read more

Latest Articles

Most Popular