BILAL TUBE NEWS AMHARIC

  • ke bezu weyeyet buhala shmgelenawu endemanqebel ena tegelu endemiqetel tenegere

    ሰሞኑን ጅምር ላይ ስላለው ሽምግልናና ለሽምግልናው ሂደት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ተቃውሟችንን ለአንድ ጁሙዓ ብናራዝም የሚሉ ሃሳቦች ላይ በሰፊው ውይይት እየተደረገ መሆኑንና የውይይቱን ውጤትም ይዘን እንደምንቀርብ ቃል ገብተን እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በርካታ ወንድሞችና እህቶች በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይቶች ካደረጉ በኋላ በአላህ ፍቃድ ሁሉም የጋራ አቋም ላይ መድረስ የቻሉ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ህብረተሰባችን ጉዳዩ እጅግ አሳስቦት በአካልም በፌስቡክም ሃሳቦችን ለመስጠት የነበረው ርብርብ ሊደነቅ የሚገባውና የደረሰበትንም የብስለት ደረጃ የሚያሳይ መሆኑን ሳናበስር አናልፍም፡፡ 
    የተቃውሟችንን ቀጣይነት አስመልክቶ 
    • የሽምግልናው ሂደት ከመነሻው ጀምሮ ከሚዛናዊነት ይልቅ ኮሚቴዎቻችንና ሰላማዊ እንቅስቃሴያችንን በመወንጀል የተጀመረ በመሆኑ፤ 
    • ከመንግስት ጋር እንዲደራደሩ የመረጥናቸው ኮሚቴዎች አላግባብ ታስረው ያሉ በመሆኑ፤
    • መንግስት በአንድ በኩል ሽምግልና እያለ በሌላ በኩል ያለፈውን ጁሙዓ ጨምሮ እስካሁንም በርካታ ወንድሞችና እህቶችን ለእስርና ድብደባ እየዳረገ በመሆኑ፤
    • በጥቅሉ ከመንግስት በኩል ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት በጎ ተነሳሽነት ያልታየ በመሆኑ
    የጁሙዓ ተቃዉሟችን ከበፊቱ በተጠናከረ ሁኔታ አዳዲስ ስልቶችን አካቶ መቀጠል እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ የሽምግልናው ሂደት ተቀባይነት እንዲያገኝ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስመልክቶ የተደረሰባቸውን ውሳኔዎች በቀጣይነት የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ አላሁ አክበር!
    Read more
  • Gud Gud!!! ye mejlis presidant ato ahmedin chelo ye ebdet besheta melekfachewun menchoch astawequ

    የህዝብ ዉክልና የሌለዉ የህገ ወጡ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የነበሩት አቶ አህመዲን አብዱላሂ ጨሎ በእብደት በሽታ መለከፉቸዉን ምንጮቻችን አረጋገጡ:: የጨሎ የልጅ ልጅ የሆኑት አህመዲን አብዱላሂ በገጠማቸዉ የእብደት በሽታ ከአ.አ በድብቅ ወደ ትዉልድ ቦታቸዉ ሀረር ኮምቦልቻ መወሰዳቸዉን ለማወቅ ተችሏል:: በአሁኑም ሰአት ሀረር ኮምቦልቻ በሚገኘዉ የአቶ አህመዲን አብዱላሂ ሼህ በሆኑት ሼህ መሀመድ ሷሊህ ሀድራ ላይ ለህክምና እንደሚገኙ የቤተሰብ ምንጮች አስታዉቀዎል:: ሼህ መሀመድ ሷሊህ ታዋቂ የአህባሽ ሼህ ሲሆኑ የተለያዩ ባህላዊ መድሀኒቶችን እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል:: አቶ አህመዲን አብዱላሂ እራሳቸዉን በመርሳታቸዉ እጅና እግራቸዉ በሰንሰለት ታስሮ እንደሚገኝ የአይን ምስክሮችና የቅርብ ቤተሰባቸዉ ለምንጮቻችን ገልፀዎል:: ወደ ሼህ መሀመድ ሷሊህ ሀድራ ቦታ ለመግባት ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን ወደ ሀድራዉም ለዚያራ የሚገቡ ሰዎች አቶ አህመዲን ወዳሉበት ክፍል መግባት የማይፈቀድላቸዉ ሲሆን ማንኛዉም ሰዉ ፎቶግራፍ እና የሞባይል ስልክ ይዞ መግባት እንደማይፈቀድ በቦታዉ የተገኙ ምንጮቻችን ገልፀዎል:: የሀድራዉ ቦታም ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል:: የአቶ አህመዲን አብዱላሂ በእብደት በሽታ መለከፉቸዉን እና በሰንሰለት እጅና እግራቸዉ መታሰሩን ለመደበቅ ቢሞከርም የሀረር ሙስሊም እየሰማባቸዉ በመሆኑ ሌላ ቦታ ለመዉሰድ ማሰባቸዉን የቤተሰብ ምንጮች አመልክተዎል:: ይህ ዜና በሁሉም ጆሮ መድረሱ ያስደነገጣቸዉ የአቶ አህመዲን አብዱላሂ ደጋፊ ቤተሰቦች አንድ ወንድሙና የአጎቱ ልጅ"አቶ አህመዲን አብዱላሂ ሀረር ኮምቦልቻ የመጡት ለረመዷን ፆም ነዉ" በማለት ማስተባበያ በመስጠት ለመደበቅ እየሞከሩ እንደሚገኙ የቤተሰብ ምንጮች ተቁመዎል Read more
  • asdengach yeteqawumo self gonder

    አስደንጋጮቹ የፀረ ተቃውሞ ሰልፎች
    አስደንጋጮቹ የፀረ ተቃውሞ ሰልፎች
    ዕለት ከጎንደር ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው የአምባጊዮርጊስ ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ፡፡ ይህ ሰልፍ ከሌሎች ሰልፎች ለየት ያለ ነበር ብሎናል ዘጋቢያችን ከቦታው….
    ባለፈው በጎንደር ከተማ “ የታሰሩት ሙስሊም ወንድሞቻችን አሸባሪዎች፣ፅንፈኞች፣አክራሪዎች ናቸው”ብላችሁ ውጡ ተብሎ በተካሄደው ሰልፍ በጎንደር ከተማ አለ ተብሎ ከሚገመተው 158000 ህዝበ ሙስሊም በሰልፉ የተገኘው ቁጥር ከ1000 የማይበልጥ ሲሆን ሁሉም ማለት
    ይቻላል ሽማግሌዎች፣ሴቶችና ጥቂት የአህባሽ አቀንቃኝ የሆኑ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸው ሰልፉ ያልተሳካ የነበረና ሁሉንም የጎንደርን ሙስሊም ህብረተሰብ ያሳዘነ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ሰልፍ ላይ የተለያዩ መፈክሮች ሲባሉ የነበሩ ሲሆን ጥቂቶቹ
    - ውበብያ አሸባሪ ነው
    - ሙስሊም ህጻናትን የሚያስተምሩ ት/ት ቤቶች ይዘጉ(ከአህባሾች ት/ት ቤት በስተቀር)
    - የታሰሩት አሸባሪዎች ለፍርድ ይቅረቡ………. ሌሎችም ለጀሮ የሚቀፉ መፈክሮች በጎንደር የማስታወቂያ ሥራ በሚሰራው ዘውዱ ምሳሌ በተባለ ግለሰብ (ሙስሊም ያልሆነ ግለሰብ ) መፈክሮቹ እየተባሉ በአህባሽ አቀንቃኞች ድጋፍ እየተቸረው አደባባዩ ሲረበሽ ውሏል፡፡
    ይህ ትዕይንት የከተማውን ሙስሊም ነዋሪ ሳይሆን ክርስቲያን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችን ያሳዘነና ያስገረመ ነበር፡፡ “የጎንደር ሙስሊም ቁጥር ይህ ነው እንዴ” በማለትም ግርምትን ጭሯል፡፡ በኢቲቪ እንዳየነውም ሜጋፎን ይዞ በሴቶችታጅቦ መፈክር የሚያሰማው ግለሰብ በጫት መሸጥ ስራ የተሰማራውና ከአህባሽ ደጎስ ያለ ገንዘብ ተሰጥቶት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው እራሱን “ ሸህ” ብሎ የሚጠራው ሀሚድ በቀበሌ 18 በመገኘት ህዝበ ሙስሊሙን ሲቀሰቅስ ነበረ ሲሆን በሌሎች መስጊዶችም ሙስጦፋ አሚኑን፣ኑርሁሴን ዳውድን ጨምሮ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን ከመቀስቀሻ ነጥቦችም
    - በሰልፉ የተገኘ ጀነትን ያገኛል፣
    - ሰልፍያ ልተገነኘ ከጀምዕያ ይሰረዛል፣ቀብርም ሊከለከል ይችላል
    - የውሀብያ ደጋፊ ነው………. ሌሎችም ነበሩ
    በቦታው የነበረው ዘጋቢያችን በተለይ በቀኝ ቤት መስጊድ 7 ሰዎች ብቻ በምዝገባመገኘታቸው ጎንደርን አጅብ አሰንቷል፡፡የአህባሽ አቀንቃኝና ከአሁንበፊት ቃዲ ኖሮ በሙስና የተባረረው እራሱን “ሀጅ” ብሎ የሚጠራው ኡስማን አብድረህማን በመስጊዱ ከሚሰግደው ከ1500 በላይ ጀምዓ 7 ሰው መገነቱ ያበሳጨው በመሆኑ በስፍራው የሚገኙ ወጣቶችን እያሸማቀቀ ይገኛል፡፡ ለመንግስትም ሰላማዊ ወጣቶችን የታሰሩት አባላት ናቸው እያለ በመጠቆም የሙስሊሞችጠላት መሆኑን በማስመስከር ላይ ይገኛል በማለት ዘጋቢያችን ከጎንደር ገልፆልናል፡፡የጎንደር ሙስሊም ወጣቶችምበሁኔታው መናደዳቸውንና ጎንደር የአሸባሪዎች መፍለቂያ ሳትሆን የታላላቅ ዑለማዎችና የነ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን፣የነኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣የነ ኡስታዝ ሀሰን ታጁና የሌሎች ዳዒዎች መፍለቂያ መሆኗን ለማሳወቅ በሰልፉ ባለመገኘት አስመስክሯል ተብሏል፡፡ በቴሌቪዢን እንዳየነው ሀሚድና ሚስቱ ቢፎክሩ፣ቢስፎክሩ የጎንደርን ወጣት ሊያሰልፉ አልቻሉም፡፡ ይባስ ወጣቱ በኢማኑ በመጎልበት ዲኑን እንዲያጠነክር አደረገ እንጅ ነበር ያሉት ወጣቶቹ፡፡ በሰልፉ ላይ ተገኝተው የነበሩ አዛውቶችምወደ ሰልፍ ስንወጣ የተነገረን ሌላ አሁን ደግሞ ሌላ በማለት ከተቆጩ በኋላ ወንድሞቻችንን ፈረድንባቸው በማለት አፉ ይበሉን ተጭበርብረን በፈፀምነው ወንጀል ተጸጽተናል በማለት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
    ወደዋናው ርዕሴ ልመለስ ይላል ዘጋቢያችንወደ አምባጊዮርጊስ
    በጎንደሩ የተቃውሞ ሰልፍ ተብየው ሲገርመን በአምባጊርጊስ አዲስ ክስተት መፈጠሩ አገር ጉድ አሰኘ፡፡ዘጋቢያችን እንደሚከተለው ዘገበልን››………..
    እንደሌላው ሁሉ የአምባጊዮርጊስ ሙስሊም ህብረተሰብ የታሰሩት ወንድሞቻችን በአሸባሪነትና በአክራሪነት ተወንጅለው እንዲፈረድባቸው ሰልፍ ውጡ ይባላሉ፡፡እነርሱም ሀሳቡን ይቀበሉና ለሰልፉ ቀጠሮ ይይዛሉ፡፡ህዝበ ሙስሊሙ በተባለው ቀን በነቂስ ይወጣል፡፡ ሰልፉ ተጀመረ፡፡”አላሁ አክበር” ሰልፉ ቀጠለ፡፡ ነገሩ እንደታሰበው ሳይሆን ቀረ፡፡ “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” መፈክሮቹ ሌላ ሁኑ፡፡
    - የመስጊዳቺን ቦታ ይከበር
    - የታሰሩ ወንድሞቻችን ይፈቱ
    - የሙስሊሞች መብት ይከበር…… ሌሎችም መፈክሮች ቀጠሉ
    የመንግስት አካላትም በጉዳዩ ተደናግጠው ሰልፉ እንዲቆም ቢሞክሩም ሳይሳካ ቀጥሎ ዋለ…….. አላሁ አክበር!
    አሁንም የምናስተላልፈው መልዕክት ቢኖር መንግስት የታሰሩትን ወንድሞቻችንን ፈትቶ ጥያቄዎቹ ተመልሰው በሰላም ወደ ልማታችን እንግባ ነው በማለት በመረረ ቃል አሳስበዋል ሰልፈኞቹ፡፡ በጎንደርና አካባቢዋ የምንገኝ ሙስሊሞች ወንድሞቻችን እንዲፈቱ እየጠየቅን ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ጎን መሆናችንን ልንገልጽ እንወዳለን፡፡
    ኢስላም ሰላም ነው!!
    ኢስላም ሰላም ነው!!
    Read more

Latest Articles

Most Popular