AHBASH
-
<< nalet mengest mels tekekelegna meles yesetal belen altebqenm ATO MULUGETA LE FANA 98.1 BESETUT KAL MESERET 1) mejlis hizbe muslimu yemifelgachewn sewoch fthawi behone melku yememret mebt alew yihinin lemadreg mengist asfelagiwn neger liyamuala ychlal gin techemari wuyiyit yasfelgewal 2 ahbash mejlis tru new blo yametaw neger slehone begid sayhon be flagot memar tchlalachu yalfelege metew ychilal 3 awelia timhrtu meketel yichlal gin be arebgna timhrt sebeb akrarinetn mastemar aychalm ye haymanot timhrit mesetet yemichalew betemezegebu medresawoch bcha new cariculemu mestekakel alebet yemil melash setewal. mjilis mengest alewu egna allah alen tegelun eskemecheresha enqetelalen Read more
-
alimu yedin temert endayastemru tekelekelu
አሊሙ የዲን ትምህርት እንዳያስተምሩ ታገዱ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ፊንፍኔ ወረዳ በሚገኘው ቡራዮ ኑር መስጂድ ጀመዓ አባላትን የዲን ትምህርት ሲያስተምሩ የነበሩት ዓሊም በክልሉ መጅሊስ አላግባብ መታገዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ ከስምንት ወራት በፊት ከኢማምነታቸው በክልሉ መጅሊስ አላግባብ እንዲነሱና በሌላ እንዲተኩ ከተደረገ በኋላ ሰሞኑን ደግሞ ቅሪአት እንዲያቆሙ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡ ቀደም ሲል ከኢማምነታቸው እንዲነሱ ሲደረግ የአካባቢው ጀመዓ አባላት ሠላምን በመውደዳቸው መቆየታቸውን ጠቁመዋል በአሁኑ ወቅት የአካባቢው ወጣቶች ያላቸውን የዲን እውቀት እንዲያስተላልፉ የክበቡ መጅሊስ አገዳ መጣሉ እንዳስቆጣቸው ገልጸዋል፡፡ ዓሊሙ ባቸው ተቀባይነት የቸካባቢው ህብረተሰብ በ180 ሺ ብር ወጪ የመኖሪያ ቤት እንደገዛላቸው አስታውቀዋል፡፡ ሼህ ሀሰን መሐመድ በበኩላቸው በመጅሊሱ አመራር አላግባብ ተፅዕኖ እደተደረገባቸው ይገልፃሉ፡፡ ውሃብይና አክራሪ በሚል ታርጋ ከኢማምነታቸው ካነሷው ወራት ቆይተውል፡፡ የቀበሌ አስዳደር አካላትም ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባቸው መሆኑን ተናግረዋል በጉዳዩ ዙሪያ የኦረሮሚያ መጅሊስን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም፡ Read more -
ye alquds gazeta wana azegaje serawun leqeqe alqudsm yetesasate zena yawetal ale
የአልቁዱስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በፍቃዱ ስራን ለቀቀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል የካቲት በማሪያ አልቅዱስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሥር በየሳምንቱ ጁምዓ ለንባብ የምትበቃው የአል-ቁድስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሥራውን ማቆሙን አስታወቀ፡፡ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ አቶ መሐመድ ዳውድ ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት ሥራውን በፈቃዱ ሊለቅ የቻለው ጋዜጣው በተከታታይ እያወጣ ያለውን የተሳሳተ መረጃ በመቃወም ነው፡፡ በጋዜጣው ላይ ሲወጡ የነበሩት ዘገባዎች ሆኑ መጣጥፎች በተመለከተ ምንም አይነት እውቅና እንደሌለው የጠቀሰው የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ በስሙ ለተፈጠረው ስህተት ሕዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ ጠይቋል፡፡ በጋዜጣዋ ላይ ካለፉት 7 ወራት በላይ በዋና አዘጋጅነት ስሙ ቢጠቀስም የዋና አዘጋጅነት ሚና እዳልነበረው አቶ መሀመድ አስታውቀዋል፡፡ የአል-ቁድስ ጋዜጣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወቅታዊ የህዝበ ሙስሊሙን ጉዳዮች ላይ የተሳሳቱና ምንጫቸው በትክክል ያልተጠቀሱ ከወገንተኝነት ያልፀዱ ዘገባዎችን በተከታታይ በማውጣቱ በህዝበ ሙስሊሙ በሰፊው ሲወገዝ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ Read more -
be alem lay yeminoru ethiopian yemuslimun teyaqe degefu
ኢትዮጵያውያኑ የህዝበ ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እንደሚጋሩት ገለፁ፡፡አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል የካቲትበላስ ቬጋስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች በአወሊያ ተቋም ተማሪዎችና መላውሙስሊም ህብረተሰብ መብቱን ለማስከበር ሠላማዊ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ ፡፡በላስ ቬጋስ ነቫዳ የሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች ሰሞኑን በወቅታዊ የኢትዮጵያውያንሙስሊሞች ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያኑ ነቫዳ ላይ ፌብሩዋሪ 22 2012 አስቸኳይስብሰባ በማካሄድ በወቅታዊ የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ውይይታቸውን ሲያጠቃልሉባወጡት ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫም በአወሊያ ተቋም በተማሪዎችና በመላው ህዝበ ሙስሊም የተጀመረውን መብትንየማስከበር ሰላማዊ ትግል እንደሚጋሩት አስታውቀዋል ፡፡የመጅሊሱ አመራር የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የተወሰነ ቡድንጥያቄ እንደሆነና የተወሰኑ የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ነው በማለት ህዝቡን ከማደናገር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል ፡፡የኢትዮጵያ እስልምናጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራር አባላት የህዝቡ ተቀባይነት የሌላቸው በመሆኑ ቦታውን ለቀው በህዝበ ሙስሊሙ በሚመረጡሕጋዊ መሪዎች እንዲተኩም አጥብቀው ጠይቀዋል ፡፡በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ሕገመንግስቱ ላይ የተቀመጠውንየእምነት ነፃነት በመተላለፍ በእስልምና ኃይማኖት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አጥብቀው እንደሚቃወሙ በአቋም መግለጫቸውአመልክተዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያን ሙስሊሞች ባወጡት በዚሁ የአቋም መግለጫ በህገመንግስቱ መሰረት የኢትዮጵያሙስሊሞች ኃይማኖታዊ ግዴታዎቻቸውን ያለ አንዳች ገደብና ተፅዕኖ በነፃነት እንዲተገብሩምጠይቀዋል ፡፡ለአብነትም የአበባበስ ፣በጋራ በትምህርት ተቋማት ውስጥ መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው ሲሉ ጠቅሰዋል ፡፡በቀጣይ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጀመሩትንየመብት ማስከበር እንቅስቃሴ በሰላማዊና በተደራጀ መልኩ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁመዋል ፡፡ኢትዮጵያውያኑና ኢትዮአሜሪካውያን ሙስሊሞች በአገር ቤትና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ከሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ጋር በመተባበር ከሰላማዊ ትግሉ ጎንእንደሚሰለፍምአረጋግጠዋል ፡፡ለሰላማዊና ለተደራጀው ቀጣይ ትግል አመቺ ይሆን ዘንድም ልዩ ኮሚቴ አቋቁመው መንቀሳቀስ መጀመራቸውንኢትዮጵያውያኑና ኢትዮ አሜሪካውያኑ ለሬዲዮ ቢላል ዛሬ በላኩት በዚሁ የአቋም መግለጫቸው አስታውቀዋል ፡፡Read more -
be neqemet ketema temariwoch hijab tekelekeleu
-
A new petition has started>> a letter to prime minister meles zenawi
A new petition has started. Please read the following pettion letter. Then click the link and sign the on line petition. (The letter is written in diplomatic way to assist the work of our committee).
ለክቡር አቶ መለስ ዜናዊ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር
አዲስ አበባ
አቤት ባዮች እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ስንሆን የአቤቱታችንን ፍሬ ነገር እንደሚከተለው አቅርበናል።
በኢትዮጵያ ህዝቦች ይሁንታና ንቁ ተሳትፎ የጸደቀው የኢ.ፌዴ.ሪ ህገ-መንግስት ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት ማንጸባረቅና የአምልኮ ስርዓታቸውን ያለ አንዳች ገደብ ማከናወን እንደሚችሉ የታወጀበት የህዝቦቻችን የቃል-ኪዳን ሰነድ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት የአምልኮ ስርዓታቸውን በነጻነት ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ሙስሊሞች በሙሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወከሉበትን የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በማቋቋም ለእምነታቸውም ሆነ ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ተግባራትንም ሲፈጽሙ ኑረዋል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በሀገሪቱ ሙስሊሞች የእምነት ነጻነትና የዜግነት መብቶች ላይ ታላቅ አደጋ የደቀነ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል። ይህንን እንቅስቃሴ ፊታውራሪ ሆነው በመምራት ላይ ያሉትም ህዝበ ሙስሊሙ ባልተሳተፈበት ሁኔታ ተመራርጠው የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በሞኖፖል የተቆጣጠሩት ጥቂት የአመራር አካላት ናቸው።
እነኝህ ግለሰቦች ከሀይማኖታዊ አባት በማይጠበቅ መልኩ በቡድንተኝነት ስሜት እርስ በራሳቸው ሲጠቃቀሙና ሌሎችን እያሳደዱ ሲያጠቁት ከርመዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለሀገራችን ሙስሊሞች ባዳ የሆነውና “አል-አሕባሽ” የሚባለው የእምነት አንጃ የሚያራምደውን ርዕዮት እንድንከተል ለማድረግ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። ህዝበ ሙስሊሙ በማያውቀው መድረክ በወሰኑት ውሳኔ የሀገራችንን መስጊዶችና መድረሳዎች በጠቅላላ በዚህ አንጃ ተከታዮች ቁጥጥር ስር ለማስገባት ሰፊ ዘመቻ እየተካሄደ ነው።። የነርሱን ህገ-ወጥ አካሄድ የማይቀበሉትን በሙሉ በጽንፈኝት በመፈረጅ የጥቃት በትራቸውን ያሳርፉበታል። ለዚህ እንዲያመቻቸው በማሰብም “ወሀቢያ” እና “ኸዋሪጃ” ለተሰኙ አደናጋሪ ቃላት ያሻቸውን ትርጉም እየሰጡ በጨዋነትና በመቻቻል ባህላቸው ዓይነተኛ ተጠቃሽ የሆኑትን የሀገራችንን ሙስሊሞች በአደባባይ በአክራሪነት ፈርጀዋል። በቅርበት ለሚያውቋቸው የመንግስት ባለስልጣናት የሀሰት መረጃዎችን በመስጠት በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲዎች በሚማሩ ሙስሊም ወጣቶች ላይ ልዩ ልዩ እቀባዎች እንዲጣሉ አድርገዋል። በዚህም ወጣቶቻችን አምልኮአቸውን በነጻነት እንዳያካሂዱ ከፍተኛ ችግር ተፈጥሯል።
ክቡር ሆይ!
የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራር አካላት የሚያካሄዱትንና አድማሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማስፋት ላይ ያለውን ይህንን ህገ-ወጥ ዘመቻ በጭምምታም ቢሆን ያውቃታል ብለን እንገምታለን። ሆኖም ከታች ካሉት የመንግስት መዋቅሮች ጋር በመወያየት ችግራችንን ልንፈታው እንችላለን በሚል ተስፋና እምነት ጉዳዩን ወደርስዎ ከማምጣት ተቆጥበን ቆይተናል። በተጨማሪም በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ የህዝበ ሙስሊሙን ሙሉ የእምነት መብት በይፋ በመቀበል ብቸኛ በሆነው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስትና በሙስሊም ዜጎቹ መካከል ጸንቶ ያለውን ወዳጅነት ለመሸርሸር የሚፈልጉ ሀይሎች ነገሩን እያራገቡ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሊነዙበት ይችላሉ በሚል ፍራቻ ወደርስዎ አላቀረብነውም። ይሁንና ከታች ያሉት የመንግስት አካላት እንደተመኘነው ችግራችንን ሊፈቱልን አልቻሉም። ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ደግሞ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት አመራሮች የአወሊያ እስላማዊ ኮሌጅን የመሳሰሉ የእምነት ተቋሞቻችንን እራሳቸው ባመጡት አዲስ አንጃ ስር ለማስገባት የሚያደርጉት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ህሊናችንን እረፍት ነስቶታል። ስለሆነም ለችግራችን አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠን ለመጠየቅ አቤቱታችንን ለርስዎ ማቅረቡ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኖ አግኝተነዋል። በዚሁ መሰረት ክቡርነትዎ ካለዎት ህገ-መንግስታዊ ሃላፊነት በመነሳት ጉዳዩን አይተው
1. የም/ቤቱ አመራሮች ለ“አል-አሕባሽ” አንጃ በመወገን ሙስሊሙ በጠቅላላ የአንጃው ተከታይ እንዲሆን ለማድረግ በሚል የሚያካሄዱትን ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ እንዲያቆሙልን
2. የም/ቤቱ አመራሮችና ተከታዮቻቸው በወሰዷቸው ህገ-ወጥ እርምጃዎች ከስራ ገበታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በአፋጣኝ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ፣
3. በም/ቤቱ አመራሮች የተዘጉት የአወሊያ እስላማዊ ኮሌጅና ሌሎች እስላማዊ ተቋማት ተከፍተው መደበኛ ስራቸውን እንዲጀምሩ
4. የም/ቤቱ አመራር አባላት ምርጫ የሁሉንም ሙስሊሞች ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ በአስቸኳይ እንዲካሄድ
5. የም/ቤቱ አመራር አካላት በተለያዩ መድረኮች ሲሰጧቸው ለነበሩት የተሳሳቱ መግለጫዎች ሙስሊሙን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ
የሚያዝ ቀጥተኛ አመራር እንዲሰጡልን፣ ይህንን ማድረጉ አስቸጋሪ ከሆነ ግን በህገ-መንግስቱ በተሰጠን መብት መሰረት ከ“አል- አሕባሽ” ጋር አንድ አይነት ርዕዮትና የእምነት ፍልስፍና የማንከተለው ብዙሀኑ ሙስሊሞች የምንሰባሰብበት አዲስ ምክር ቤት ለመመስረት እንድንችል ፈቃድ እንዲሰጠን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ከሰላምታ ጋር
http://www.change.org/petitions/prime-minister-of-the-federal-democratic-republic-of-ethiopia-hear-the-voices-of-ethiopian-muslimsRead more -
yederes leredio fana azegage
ይድረስ ለፋና 98.1 ጋዜጠኛው ብሩኬ
ውድ ብሩኬ መቼም የጋዜጠኝነትን ሀ ሁ ላንተ ማስቆጠር አልችልም ፡፡እምነቴም በማላቀው ነገር እንዳላወራ ማዕቀብ ጥሎብኛል፡ግን የአቶ አህመዲንን ንግግር ስታዳምጥ ተረት ተረት እንደምተወድ ተረዳሁና አንድ ተረት ጸፍኩልህ በውስጥ አንተን ታገኘዋለህና አንብበው
አንድ ሞኝ አሽከር የነበረው ሰው ነበር አሉ፡፡ ይኼ አሽከር አድርግ የተባለውን ካልሆነ በቀር አስቦ፣ አውጥቶ እና አውርዶ፣ ብሎም አመዛዝኖ የሚሠራው ሥራ አልነበረም፡፡ ምን ጊዜም የሚጠብቀው የአለቃውን ትእዛዝ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ትክክል ነገር ማለት ጌታው ያዘዘው ሲሆን፣ ስሕተት ማለት ደግሞ እርሱ ያልነገረው ነገር ማለት ነው፡፡ ዓላማው ጥሩ ነገር መሥራት ወይንም አዲስ ነገር መሥራት ሳይሆን አለቃውን ማስደሰት ብቻ ነበር፡፡
ጌታው ከሳቀ ይስቃል፣ ካለቀሰ ያለቅሳል፣ ከተደሰተ ይደሰታል፣ ካዘነም ያዝናል፡፡ የወደደውን ይወድዳል የጠላው ይጠላል፡፡ ለርሱ የመደሰቱንም ሆነ የማዘኑን፣ የመሳቁንም ሆነ የማልቀሱን ምክንያት ማወቅ አይጠበቅበትም፡፡ ዋናው ነገር ጌታው መሳቁ ወይንም ማልቀሱ ነው፡፡ አንዳንዴ ሰዎች የሳቀበትን ምክንያት ሲጠይቁት «ጌታው ሳቁኮ አላያችሁም» ይላል፡፡ በዚህም የተነሣ ሰዎች «እንዳሉት»ብለው ይጠሩት ነበር፡፡
አንድ ቀን ጌታው እና እንዳሉት ወደ መንገድ ወጡ፡፡ እርሱ በእግሩ ከኋላ እየተከተለ፤ ጌታው ደግሞ በፈረስ ከፊት እየበረሩ፡፡ መንገድ ላይ ጌታው የገንዘብ ቦርሳቸውን ጣሉት፡፡ እንዳለውም ቦርሳውን አልፎት ሄደ፡፡ጌታው ያሰቡበት ከተማ ገብተው ኪሳቸውን እስኪቀደድ ቢበረብሩ ቦርሳቸውን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም ወደ እንዳሉት ተጠጉና «የገንዘብ ቦርሳ አላየህም» አሉት፡፡ እንዳሉት «አይቻለሁ፣ መንገድ ላይ ጥለውታል» አላቸው፡፡
ጌታው ደንግጠው እና ተናድደው «ታድያ ለምን አንሥተህ አልሰጠኸኝም» አሉት፡፡ እንዳሉት ደንግጦ አሰበ፣ አሰበ፣ አሰበ፡፡ ግን የተሰጠው መመርያ አልነበረም፡፡ ተከተለኝ ከማለት በቀር የነገሩት ነገር አልነበረም፡፡ «እንዴ እርስዎ የገንዘብ ቦርሳዬ ሲወድቅ አንሥተህ እንድትሰጠኝ መች አሉኝ» አላቸው፡፡ እርሳቸውም «በል ከዛሬ ጀምሮ እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካየህ ሰብስበህ እንድትሰጠኝ» አሉት፡፡ ከእሺ በቀር ሌላ የማያውቀው እንዳሉት በጸጋ ተቀበለ፡፡ በቀጣዩ ጊዜ ጌታውን ተከትሎ መንገድ ጀመረ፡፡ መመርያው በልቡ ነበር፡፡ የሚያሳስበው የተነገረው ነገር ነው፡፡ በልቡ ውስጥም ከተነገረው ነገር በቀር ምንም ሌላ ነገር አልነበረም፡፡ የርሱ ልብ አዲስ ነገር አያመነጭም፤ አዲስ ነገር ማመንጨት የሚችሉት የርሱ አለቃ ብቻ ናቸው፡፡ የርሱ ሥራ ያለ ጥርጥር ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት ማለት ብቻ ነው፡፡ ለምን? ማለት አያውቅም፡፡ ለምን? ማለት ከጀመረማ አሽከር አይሆንማ፡፡ አሽከር ደግሞ ይጠይቃል? ይጠየቃል እንጂ? አሽከር ደግሞ ያስባል? ይታሰብለታል እንጂ? አሽከር ደግሞ ይመረምራል? ይመረመራል እንጂ? አሽከር ደግሞ ይገመግማል? ይገመገማል እንጂ? አሽከር ደግሞ ያፈልቃል? ይፈልቅለታል እንጂ? ምን ሲባል፡፡ እናም ተከትሎ ሄደ፡፡ የታዘዘው ትእዛዝ ብቻ ነበር ትዝ የሚለው፡፡ «እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካገኘህ ሰብስበህ እንድትሰጠኝ» የሚለው፡፡ ይህ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ አንዳች ነገር እንዲወድቅ ተመኘ፡፡ ያለበለዚያማ ትእዛዝ ፈጻሚ ላይሆን ነው፡፡ የሚወድቅ ነገር ከሌለማ እርሱ የወደቀን ሰብሳቢ መሆኑ እንዴት ይታወቃል? ስለዚህ ለመሰብሰብ ሲባል ብቻ መጣል አለበት፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አንዳች ነገር መውደቅ ጀመረ፡፡ እርሱም እያነሣ በቀረጢት ከተተ፡፡ ሲወድቅ ሲያነሣ፣ ሲወድቅ ሲያነሣ፣ ሲወድቅ ሲያነሣ በመጨረሻ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡ አለቃውም «እህሳ፣ ዛሬስ የወደቀ ነገር የለም?» አሉት፡፡ «አለ እንጂ» አላቸው፡፡ ደንግጠው ኪሳቸውን ዳበሱት፡፡ ቦርሳቸው ከነገንዘቡ እንዳለ ነው፡፡
«ምንድን ነው የወደቀው?» አሉት ጌታው፡፡ እንዳሉት ግን ቀረጢቱን ይዞ መጣ፡፡ ሲከፍተው የፈረሱ ፋንድያ ነበር፡፡ አለቃው ተናደዱ ፡፡
«ይህንን ምን ሊጠቅምህ ሰበሰብከው?» አሉትም፡፡
«እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካገኘህ ሰብስብ ብለውኛላ» አላቸው፡፡ እውነቱን ነው፡፡ አሽከር አንድ ነገር ይጠቅማል፣ አይጠቅምም፤ ያስፈልጋል፣ አያስፈልግም ብሎ እንዲወስን ማን ፈቀደለት? አሽከር ማለት የታዘዘውን ብቻ የሚፈጽም ማለት ነው፡፡ አሽከር ከአንገት በታች እንጂ ከአንገት በላይ አለው እንዴ? ከአንገቱ በላይ ያለው ከአለቃው ዘንድ ነውኮ፡፡
«በል» ከዛሬ ጀምሮ የምታነሣው ቦርሳዬ፣ ካባዬ፣ ባርኔጣዬ፣ ጅራፌ፣ ገንዘቤ፣ እንዲሁም ከፈረስ ዕቃዬ አንዱ ነገር ከወደቀ ብቻ ነው»፡፡ እንዳሉት በፈገግታ ተቀበለ፡፡ ግን ፈራ፡፡ ይህንን ዝርዝር ቢረሳውስ፡፡ ቁጭ ብሎ በአንድ ወረቀት ላይ ጻፈው፡፡ መጻፍ ብቻ አይደለም እንደ ደጋገመው፡፡ በሄደበት፣ በተቀመጠበትም ይህንኑ ዝርዝር ብቻ ነበር የሚናገረው፡፡ ሰው ለሚጠይቀው ማናቸውም ነገር መልሱ ይሄ ዝርዝር ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ዝርዘሩን የሰጡት አለቃው ናቸዋ፡፡
ከሰዎች ጋር ሲያወራ በየንግግሩ ጣልቃ ዝርዝሩን ማንሣት አለበት፡፡ አብረውት የሚያወሩት ሰዎች ግራ ይገባቸዋል፡፡ ለርሱ ግራ ቢገባቸው፣ ቀኝ ቢገባቸው ግዱ ነው፤ ዋናው የአለቃውን ትእዛዝ አለመርሳቱ፣ እርሱንም የንግግሩ ማሟሻ ማድረጉ ነው፡፡ እርሱ ዋጋውን ከአለቃው እንጂ ከሕዝቡ አልያም ከህሊናው አያገኝ፡፡ ሌሎች ሰዎች ቢወዱት እንጂ አይሾሙት፤ ቢያደንቁት እንጂ አያበሉት፡፡ እንጀራውም ሹመቱም ያለው በአለቃው ዘንድ ነው፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ መንገድ ተጓዙ፡፡ እንዳሉት እና አለቃው፡፡ በሄደበት መንገድ ሁሉ የሚጓዝበትን አካባቢ፣ ዛፎቹን እና እንስሳቱን፣ መንደሩን እና መስኩን አያይም፡፡ እየደጋገመ የሚያየው ዝርዝሩን ነው፡፡ አንዴ ዝርዝሩን፣ አንዴም መንገዱን ያያል፡፡ ከዝርዝሩ መካከል መሬት የወደቀ እንዳለ ብሎ፡፡
እርሱም ዝርዝሩን እንዳየ አለቃውም እንደሸመጠጡ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡
«እህሳ ዛሬስ የወደቀ ነገር አለ?» አሉት፡፡ «የለም፤ ከዝርዝሩ ውስጥ የወደቀ ነገር የለም» አላቸው፡፡ ለእርሱ ዋናው የሚጠቅም ነገር ወድቋል? የሚለው አይደለም፤ ከዝርዝሩ መካከል፤ ከታዘዘው መካከል ወድቋል ወይ? የሚለው ነው፡፡ ከዝርዝሩ ውጭ ምን ነገር አለ? ማንኛውም ነገር ያለው በዝርዝሩ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ከዝርዝሩ ውጭ ያለ ነገር አንድም እንዳለ አይቆጠርም፤ ያለበለዚያም የማይጠቅም ነገር ነው፡፡ ዋናው ዝርዝሩ ነው፡፡ እናም
ደስ አለው፡፡ ከዝርዝሩ መካከል የነጠበ ነገር የለምና፡፡
«ዝርዝሩን ይጠብቅልን» ብሎ ጸልዮ ተኛ፡፡ ያለ ዝርዝሩ እንዴት መኖር ይቻላል፡፡
ከብዙ ጊዜ በኋላ እንዳሉት እና አለቃው ለአራተኛው ጉዟቸው ተነሡ፡፡ እርሳቸውም ፈረሳቸውን እርሱም ዝርዝሩን አዘጋጁ፡፡
ሄዱ፡፡ ሸመጠጡ፡፡ እርሳቸው ፊት ፊታቸውን፣ እርሱም ዝርዝሩን እያዩ፡፡ ዋናው ዝርዝሩ ነው፡፡
ሲሄዱ፣ ሲሄዱ፣ ሲሄዱ
መንገድ ላይ ፈረሱ አደናቀፈውና አለቃውን ይዟቸው ወደቀ፡፡ ፈረሱም የሲቃ ድምጽ አሰማ፡፡ ጌታውም ጮኹ፡፡
«አንሣኝ አንሣኝ» እያሉ ጮኹ አለቃው፡፡
እንዳሉት ዝቅ ብሎ በእጁ ያለውን ዝርዝር አየ፡፡ አለቃውን ሲወድቁ እንዲያነሣ የሚያዝ በዝርዝሩ ውስጥ የለም፡፡
«አላነሣዎትም» አላቸው፡፡
«ለምን ለምን፤ ኧረ ተላላጥኩልህ አንሣኝ» አሉት በልመናም በትእዛዝም፡፡
«የለም አለቃው በዝርዝሩ ውስጥ እርስዎ የሉም»
በመካከል ፈረሱ ተነሣ፡፡ አሽካካ፡፡ አለቃው ግን ሰውነታቸው ተላልጦ እየደማ እዚያው ያቃስቱ ጀመር፡፡
ፈረሱ መንገዱን ይዞ ሸመጠጠ፡፡ አለቃው እጃቸውን እያርገበገቡ «እባክህ ስለ ፈጠረህ አምላክ አንሣኝ» እያሉ እንዳሉት ለመኑት፡፡ እርሳቸው ያንን ዝርዘር ሲሰጡት ቃላቸውን ለማስጠበቅ እና ከቃላቸው እንዳ ይወጣ እንጂ እርሳቸው ሊወድቁ እንደሚችሉ መች ገመቱ፡፡ ደግሞስ አለቃ እወድቃለሁ ብሎ እንዴት ይገምታል፡፡ አለቃ አይደሉ፡፡
አሁንም እጃቸውን እያርገበገቡ ለመኑት «አንሣኝ አንሣኝ እባክህ» እንዳሉት ግን ፈረሱን ተከትሎ አሁንም ዝርዝሩን እያየ ትቷቸው ሮጠ፡፡
ብቻውን «እንዴ እዚህ ዝርዝር ውስጥ የሌሉትን እንዴት ብዬ ላንሣቸው፡፡ በኋላ ደግሞ ከዝርዝሩ ውጭ አነሣህ ብለው ራሳቸው ቢቆጡኝስ፡፡ እኔ ካዘዙኝ ውጭ ሠርቼ ዐውቃለሁ? አሁን ማንን ክፉ ለማድረግ ነው» እያለ እያጉረመረመ ፈረሱን ተከትሎ ነጎደ፡፡ብሩኬ በአንተና በእናዳሉት መካከል ምን ልዩነት ያለ ይመሰልሀል?ስማችሁ ብቻ ነው የሚለያየው አይደል ?ካልተቀየምከኝ እኔም እንዳሉት አልኩህ፡፡
“እውነት በዶዘር ቆፍረው ብትቀብርዋትማ አንድ ቀን በአካፋ ቆፍራም ቢሆን መውጣትዋ አይቀርም” Read more -
Allahu akber Allahu akber
አላሁ አክበር!!! አላሁ አክበር!!! በዛሬዉ እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በድል በትግል አዳራሽ የኢህአዴግ ሙስሊም አባለት ከክፍለ ከተማዉ የኢህአዲግ ዎና ስራ አሰፈፃሚ ጋር ዉይይት አደረጉ::በዉይይቱ መጀመሪያ ላይ በአወልያ እየተካሄደ ስላለዉ ሰላማዊ እንቅስቃሴን በመተቸት ገለፃ የተደረገ ሲሆን ለታዳሚያን መድረኩ ከተከፈተ ቡሀላ ግን አስገራሚ ትእይንቶች የታየበት እንደነበር ተገልፆል::በዛሬዉ ስብሰባ ከፍተኛ ተቃዉሞአቸዉን ሲያሰሙ የነበሩት እናቶች እና አባቶች ነበሩ::አንዲት እናት እንባ እየተናነቃት ያቀረበችዉ የተቃሞ ንግግር በስብሰባዉ የተገኘዉን ህዝብ በጣም የነካ እንደነበር ተገለፆል:: ከተሰብሳቢዎች የተነሱት ነጥቦች መካከል መጅሊስ አይወክለንም! ምርጫም ማካሄድ አይችልም! አስመራጮችን መምረጥ ያለብን እኛ ሙስሊሞች ነን!መንግስት ወሀብያ ሱፊያ የሚባሉ ጉዳዬች ዉስጥ መግባቱ ተገቢ አይደለም! የአወልያ የሙስሊሞች ሀብት ነዉ በመሆኑም ለሙስሊሙ ሊመለስ ይገባዎል የሚሉ ወሳይ ነጥቦችን የኢህአዴግ ሙስሊም አባላት ያነሱ ሲሆን የአዲስ ክ/ከተማ የኢህአዴግ ዎና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን መንግስቱ የተነሱት ጥያቄዎች በሙላ ተገቢ መሆናቸዉን ያመኑ ሲሆን መንግስት በማንኛዉም ሁኔታ ከህዝብ ጋር በመሆኑ የህዝቡን ጥያቄ ይመልሳል:: ህዝበ ሙስሊሙ ነፃ በሆነ መልኩ መሪዎቹን መምረጥ አለበት:: አስመራጮቹንም መምረጥ ያለበት ህዝበ ሙስሊሙ ብቻ ነዉ:: መንግስት የህዝበ ሙስሊሙ ዉክልና ከሌለዉ አካል ጋር ከንግዲህ አብሮ አይሰራም በማለት የስብሰባዉ ተሳታፊዎቹን ሀሳብ በመጋራት ስብሰባዉ በህዝበ ሙስሊሙ ድል አድራጊነት በድል ተፈፅሟል::አላሁአክበርby abu dawd Read more -
Facebook yaneqaneqeu tewuld na ye ahbash fetena
“ፌስቡክን ያንቀጠቀጠው ትውልድ” እና የአል-አሕባሽ ፈተና
ኡባህ አብዱሰላም ሰዒድ
የኢህአዴግ መሪዎች የነበሩበትን ትውልድ “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ይሉታል። በዘመኑ እንደተራራ ገዝፈው ይታዩ የነበሩትን የደርግ ጄኔራሎች ባልጠበቁት መንገድ እያዘናጉ ጉድ እንደሰሩት ለመግለጽ የፈጠሩት ስም ነው። ከ2010 ማገባደጃ ጀምሮ በዐረብ ሀገሮች ሲካሄዱ የነበሩትን ሰላማዊ ንቅናቄዎች የመሩት የፌስቡክ ወጣቶች መሆናቸው ያስገረማቸው ታዛቢዎች ደግሞ እኔ ላለሁበት ትውልድ “ፌስቡክን ያንቀጠቀጠው ትውልድ” የሚል ስም ሰጥተውታል። እኔም እነርሱ በሰጡን ስም መጠራቱን ወድጄዋለሁ።
ይህ ትውልድ አስገራሚ ተግባራትን የከወነው በውጪው ዓለም ብቻ አይደለም። በሀገራችንም ለዝክር የሚበቁ ታሪኮችን እያስመዘገበ ነው። ለምሳሌ ፌስቡክን ያንቀጠቀጠው ትውልድ የዓለም ሙስሊሞችን ግራ ሲያጋባ የኖረውን የአሕባሽ ቡድን ጉድ ሰርቶታል። በሌላ ዓለም ያልተቻለው አሕባሽ በሀገራችን ቅትረ-ቀላል ሆኗል። አንዳንድ ኩነቶችን ቀንጨብ እያደረግኩ ላሳያችሁ።
አል-አሕባሽ የርስ በርስ ጦርነት በበጣጠቃት የሊባኖስ መዲና ውስጥ ሲቋቋም የተከተለው የገለልተኝነት ስልት በጣም ጠቅሞታል። ህዝቡ እንደ ነጻ አውጪ የሚመለከተው የሶሪያ ጦር ሀይል ጠንካራ ክንድ ታክሎበት “ዘመናዊ የእስልምና ቡድን አሁን ተገኘ” የሚሉ ወጣት ደጋፊዎችን በብዛት አፍርቷል። ወደ ሀገራችን ሲመጣ ግን ጉዳዩ ሌላ ሆኖ ነው የተገኘው። የሀገራችን ወጣቶች ሰምተው የማያውቋቸውን እንደ “የብሪታኒያው ሰላይና የሙሐመድ አብዱልወሃብ ሚስጢር”ን የመሳሰሉ ታሪኮች እየደሰኮረ ወጣቶቻችን ለማማለል ቢሞክርም አልቀናውም። (“የነቢዩን ጸጉር ተመልከቱ” የሚለው ቀሽም ቲያትር ደረጃውን ያልጠበቀ የህጻናት ካርቱን ፊልም በመሆኑ በዚህ ጽሁፍ ሳልጠቅሰው አልፈዋለሁ።).
አንጃው ለራሱ ከፍተኛ ግምት ይሰጣል። ዓለም በተራቀቀበት ዘመን እንኳ ብልጣብልጥ ሆኖ ሙስሊሞችን መሸወድ የሚችል ይመስለዋል። ታዲያ ወጣቶቻችን ጉድ ሰሩት። የኢማም አቡል ሐሰን አል-አሽዓሪን የአቂዳ ትምህርት ለማስጠበቅ ብርቱ ትግል የሚያደርግ ሳተና በመምሰል የሙስሊሞችን ድጋፍ ለማሰባሰብ ቢሞክርም ማንም አልሰማውም። ከዚህ ይልቅ ወጣቶቻችን የኢማም አል-አሽዓሪ ትምህርት በስፋት ከሚሰጥበት የአል-አዝሀር ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ ፈትዋ አምጥተው “የኑፋቄና የጥመት ቡድን ነህ” የሚል መርዶ ነገሩት። “ሱፊ ነኝ፤ ወሃቢዎች መውሊድ አይከበርም ይላሉ” እያለ ቢያላዝንም በዓለም የታወቁ የሱፊ ማዕከላት በአሕባሽ ላይ ያስተላለፉትን ውግዘት አሰሙት። “ወሃቢዎች ሙጀሲማ ናቸው፤ አላህን ከሰው ልጅ ጋር ያመሳስላሉ” እያለ ቢያወናብድም “አሊ ኢብን አቡ ጣሊብ በሰው መልክ የተገለጸው አምላክ ነው” ከሚሉት የሶሪያ መሪዎች ጋር ያለውን ግልጽ የወጣ ፍቅር በመንተራስ “ስለሙጀሲማ ለማውራት ከፈለግክ ትክክለኛ ምሳሌ ማድረግ የነበረብህ የሶሪያ የአሊዊ ፊርቃ ተከታዮችን ነው” አሉት። ከሁሉም የባሰው መርዶ ደግሞ በፌስቡክ ላይ ተነገረው። ወጣቶቻችን “አሕባሽ ADL የተባለው የጽዮናዊያን ድርጅት አባል ነው” የሚል በማስረጃ የተረጋገጠ ሚስጢር በማውጣት በህዝብ ፊት አዋረዱት። ይህንን ታላቅ መርዶ የነገሩት የውጪ ሀገር ሰዎች ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ነን። (ለዝርዝሩ ይህንን ሊንክ ይከተሉ www.adl.org/philadelphia/coalition.asp)
ወገኖቼ! አሕባሽ የተስፋዬ ሀገር ናት በሚላት ኢትዮጵያ ውስጥ ሺህ ምንተሺህ አባላት አፈራለሁ የሚል ሀሳብ ነበረው። ግን ወጣቶቻችን ውርደት አከናንበውታል። አምባሳደር ዴቪድ ሺንና ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊች አሕባሽን የሚያንቆለጳጵሱበትን ትክክለኛ ምክንያት ለመረዳት የቻልነው አንጃው ዘንድሮ በሀገራችን ውስጥ ይፋ ዘመቻ ከጀመረ በኋላ ነው። ከዚህ በፊት “ጽዮናዊው Anti-Defamation League (ADL) የአል-አሕባሽ የጡት አባት ይሆናል” የሚል ጥርጣሬ ኖሮን አያውቅም። በዚያ ላይ እስላማዊ ነኝ የሚል ቡድን ከግብረ-ሰዶማዊያን ጋር ጥምረት ይመሰርታል የሚል ግምት በማንም አእምሮ አልነበረም (ከጽዮናዊው ADL ጋር ጥምረት የፈጠሩ ድርጅቶችን በሚያሳየው ዝርዝር ውስጥ የግብረሶዶም መብት ተከራካሪ ድርጅቶችም እንደሚገኙበት ልብ በሉ”) ። ግን ሆነና ተገኘ። አሕባሽም ተዋረደ። በኢማም አል-አሽዓሪና ኢማም ሻፊዒ ስም እያጭበረበረ ወደ ሽርክ፣ ባእድ አምልኮና ቢድዓ ሊያስገባቸው የተመኛቸው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ዋጋውን ሰጡት።
አሁን አሕባሽ በኢትዮጵያ ውስጥ ምን ይቀረዋል? ሌላ እድል መሞከር ወይስ አርፎ ወደመጣበት መመለስ? እርግጠኛውን ነገር አላህ ነው የሚያውቀው። በኔ በኩል ሌላ ታክቲክ ይዞ የሚመጣ ይመስለኛል። ያኔ ደግሞ እኛም ሌላ ስልት ቀይሰን እንጠብቀዋለን። ኢንሻ አላህ!!!
ድል የኢስላም ነው!! አላሁ አክበር!!
Read more