AHBASH

  • warning !!! warning !!! ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!!

    ምጻችን ይሰማ ►►ማስጠንቀቂያ!!! ማስጠንቀቂያ!!! ሙስሊሞች ሆይንቁ!!►► ሰላማዊ የመብት ትግላችንን አሁንም የቀጠልን ብንሆንም ብዙ ስራ እንደሚጠበቅብን ግልፅ ሆኗል፡፡ መጅሊስና አጋሮቹ አሁንም አልተኙልንም፡፡ አሁን በሚገኙት የመጅሊስ አመራር አባላት ተስፋ የቆረጠው ፌዴራል ጉዳዮች ምርጫ አይቀሬ መሆኑን ተረድቶ ሁሉንም ሊያባርራቸው ወስኗል፡፡ ነገር ግን ምርጫውን አሁንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ!!! ምርጫውን የሚያስፈጽም ‹‹ገለልተኛ›› ሰው ስላስፈለጋቸው ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይህንንም ለማሳካት የአህባሽ ስልጠና እንደገና ሊሰጡ ሲሆን ኦሮሚያ፣ ደቡብ ክልል፣ አማራ ክልልና አሁን ደግሞ በወሰኑት መሠረት በአዲስ አበባ በአጠቃላይ 15 ሺህ ሰው ያህል ለማሰልጠን ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ አዲስ አበባን ሳይጨምር በክልሎቹ ለሥልጠና የተመረጡት 16 ያህል ቦታዎች ናቸው፡፡ ስልጠናው ላይ አህባሽ ላይ ለቀረቡት ውንጀላዎች ‹‹ምላሽ›› የሚሰጡ ሲሆን ስልጠናውን የሚወስዱት የመስጊድ ኢማሞችና ዱአቶች ናቸው፡፡ የአህባሽ ደጋፊ እንዲሆኑና ምርጫውን እንዲቆጣጠሩለት፣ ‹‹ወሃቢያ›› እንዳይመረጥ እንዲከላከሉለት ፌዴራል ጉዳዮች ቋምጧል!!! (መብቴን ያለ ሁሉ ለነሱ ወሃቢያ ነው!!!) በጀቱ በሙሉ በፌደራል ጉዳዮች ነው የሚሸፈነው፡፡ ታይም ቴብሉንም ሁሉ አውጥቶ ለመጅሊስ የላከው ፌዴራል ጉዳዮች ነው!!! ስልጠናውንም ሊጀምሩ ያሰቡበትን ጊዜ በማራዘም ሚያዝያ 10 እና 11 ሊጀምሩት ወስነዋል፡፡ በምርጫው በ‹‹ሱፊ›› እና ‹‹ወሃቢያ›› መካከል ቡድን ለመፍጠርና ክፍፍል ለመፍጠር ፈልገዋል!!! አላህ ስንት ተንኮላቸውን አፈረሰባቸው??? መቼ ይሆን ልብ የሚገዙት??? በክልሎች መጅሊስ ጠቅላይ ጉባኤ እየተካሄደ ሲሆን ትናንት በባህርዳር መስጊድ አስመርቀው ከፍተው ዛሬ ሲወያዩ ውለዋል፡፡ ስትራቴጂያቸውን ሲነድፉም ቆይተዋል፡፡ ኢህአዴግ አባላቱን ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያየ ቦታ ሰብስቦ ሲያወያይ የቆየ ሲሆን በበርካታ ቦታዎች ከአባላቱ ተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲቀርብበት ነበር፡፡ ነገር ግን በማስፈራራት እና እንቅስቃሴው የወሃቢይ አክራሪያን እንደሆነ በመናገር አንዳንድ አባላቱን ለማሸማቀቅ ‹‹ከሁለት አንዱን ምረጡ!›› እያለ ሲያስፈራራ ነበር፡፡ ጥናት ተብዬ ወረቀትም አቅርበዋል!!! በተለያዩ ቦታዎች የመጠይቅ ወረቀት (ኩዌሽነር) የበተኑ ሲሆን መንግስት ጣልቃ ገብቷል ወይ በሚል ለቀረበው ጥያቄ 99 በመቶው ‹‹አዎ! ጣልቃ ገብቷል!›› የሚል መልስ እንደሰጣቸውም ታውቋል!!! ግን እነሱ እውነት መስማት አይፈልጉም!! በተጨማሪም ከየቀበሌው 15 ሰዎችን ለምርጫው መልምለው ጨርሰዋል፡፡ የነሱ ፍላጎት ምርጫውን በቀበሌ አድርገው የሚፈልጉትን ሰው በገፍ ሊያሰርጉ ነው!!! እኛ ደግሞ መንፈሳዊ ማእከላችን መስጊድ እንጂ ቀበሌ ስላልሆነ ይህንን በፍጹም መቀበል የለብንም!!! መልካም የአላህ ባሪያዎች እና ታማኝ ሰዎቻችን የሚገኙት በመስጊድ ነውና ምርጫ በቀበሌ ምልመላ እንዳይሆንና ይህን መሰሉን ሸፍጥ እና መንግስታዊ ጣልቃ ገብነት ካሁኑ ለመከላከል ቁርጠኝነት ያሻናል!!! ፌዴራል ጉዳዮች ይህንኑ የሸፍጥ ስራውን በመቀጠል ለአውሮፓ ህብረት እና ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት ያስገባ ሲሆን በሪፖርቱም አገራችን ውስጥ በእምነት ግጭት ምክንያት የተቃጠሉ ቤተ ክርስቲያናትን እና ሌሎች የተከሰቱ ግጭቶችን በመዘርዘር ‹‹ሁሉንም ያደረጉት እነዚሁ ወሃቢዮች ናቸው፡፡ አሁን ዋና መናኸሪያቸው አወሊያ ሲመታባቸው ነው መብታችን ተጣሰ እያሉ የሚረብሹት፡፡ አሁን ግን እርምጃ ልንወስድባቸው ስለሆነ ሰብአዊ መብት ጣስክ ብላችሁ እንዳትረብሹኝ›› ሲሉ አቅርበዋል!!! ተመልከቱ ምን ያህል ለእስልምና ያላቸው ጥላቻ አይን ያወጣ ውሸት ውስጥ እንደጨመራቸው!!! ሰላማዊ ዜጎቻቸውን ለማጥቃት እና ህገመንግስታዊ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ የጠየቁ ሰዎችን በአክራሪነትና በውሸት በመወንጀል የፈለጉትን ለማድረግ አረንጓዴ መብራት እንዲበራላቸው ውጭ ሃገር ይለማመጣሉ!!! ተመልከቱ ፌደራል ጉዳዮች እየሰራ ያለውን! አንድ ሺ አንድ ሴራቸውን እስካሁን የመለሰባቸው አላህ አሁንም ይመልስባቸዋል እንጂ እንደነሱ ቢሆንማ ሰማይ በታረሰ ነበር!!! አላሁ አክበር! አላህን የያዘ አይወድቅም!!! ወደአላህ እያለቀስን የቻልነውን ልፋት እና ስራ ሁሉ ማከናወን፣ ለዲናችን ዘብ መቆም አለብን!!! አላሁ አክበር!!! ከዚሁ ምርጫ ጋር በተያያዘ ፌደራል ጉዳዮች አራት ሰዎችን በፌደራል ደረጃ ታዛቢና ተቆጣጣሪ እንዲሆኑለት መርጧል፡፡ እነዚህም አራት ሰዎች የሀጂ ሳኒ ልጅ የሆኑት ሃጂ መሃመድ ኑር፣ ግራዝማች ሀዲስ ኑርሁሴን፣ ኢንጅነር ተማምና ሀጂ ፈድሉ ይባላሉ፡፡ (ግራዝማች ሃዲስ በ1987 ግርግር ዋነኛ ተዋናይ የነበሩና መጅሊስ የአወሊያውን ተቃውሞ እንዲያደበዝዙ የፈበረከው የሽማግሌ ቡድን አባል ናቸው!) ልብ እናድርግ ሙስሊሞች ሆይ! አስመራጭ ኮሚቴውን የሚመርጠው ፌደራል ጉዳዮችም ሆነ አሁን ያለው መጅሊስ አይደለም!!! የመምረጥ መብቱ የህዝበ ሙስሊሙ ነው! በመሆኑም እኛ ከምንመርጠው ውጪ የፈለገ ጥሩ የሚመስል ወይም የሆነ ሰው ቢመጣ በፍጹም አንቀበልም!!! ይህንን በፍጹም እንዳንረሳ!!!! ሰዎቹ ጥሩ ቢሆኑም እንኳ የምንመርጠው እኛ እንጂ መነግስት አይደለም፡፡ ስለዚህ ካሁኑ ለሌሎች በማሳወቅ ምርጫችንን ከጣልቃ ገብነት መከላከል አለብን!!! አላሁ አክበር!!! ከሐጅ ጋር በተያያዘ ሌላ ጉድ አለላችሁ! ፌደራል መጅሊሶች በሐጅ ጉዳይ ለመደራደርና ለመፈራረም ወደሳኡዲ ሊሄዱ ነው! ለጉዞው የሚሄዱት አራት ሰዎች ሲሆኑ አህመዲን አብዱላሂ፣ አዛም እና የሐጅ አስፈጻሚው አቶ አማን ሁሴን ይገኙበታል፡፡ እዚያ መሀመድኑር የሚባል ኢትዮጵያዊ ነው እስከዛሬ ሙስናውን፣ የቤት ኪራዩን ሁሉ ሲያመቻችላቸው የቆየው፡፡ ይህ ሰውዬ ለራሱም 6 አባዱላ ሚኒባስ ያለው ሀብታም ነው፡፡ የሃጅ ሙስና ዋና አመቻች እሱ ነው፡፡ ሳኡዲ ውስጥ ተቃውሞ ይገጥመናል ብለው ስለፈሩ ሙፍቲ ሃጂ ኡመርን ይዘው ሊሄዱ ነው ያሰቡት፡፡ እሳቸው ይስማሙ አይስማሙ ቁርጡን ያወቅኩት ነገር ባይኖርም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚገኘው የአራቱም ሰዎች ፓስፖርት ግን ባለፈው ጁሙኣ ቪዛ ተመቶበታል፡፡ (የሁሉም መጅሊስ አመራር አባላት ፓስፖርት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው የሚቀመጠው!) ጉዞውም አፕል ሶስት ነው፡፡ ያሳዝናል! ሊባረሩ ጥቂት ጊዜ ቀርቷቸውም እንኳን ከሌብነታቸው መቆጠብ አይፈልጉም!!! አላሁ አክበር! ምን አይነት የብር ፍቅር ነው የያዛቸው???!!! ሙስሊም ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ! እስቲ እናስተውል… እኛ አወሊያ ተሰብስበን መፈክር ስላሰማን ብቻ ብዙ የሰራን መስሎን እንረካለን፡፡ አልሀምዱሊላህ አላህ አጅራችንን ያበዛዋል፡፡ ሙስሊሞችን ጠምዶ የያዘው ዶክተር ሽፈራውና ድርጅቱ ግን በርካታ ስራ በሚሊዮን ብር በጀት እየሰራ ነው!!! እኛ በጥቂት ነገር ስንረካ እነሱ ግን ወስጥ ለውስጥ ብዙ ድንጋይ ይፈነቅላሉ፡፡ አላህ እንደ የእጁጅና መእጁጅ ቁፋሮ መና እያደረገባቸው እንጂ!!! አሁንም ቢሆን ብዙ ስራ ይጠበቅብናል፡፡ ገና አስቸጋሪውን ትግል እየጀመርነው ነው! ተስፋ በፍጹም አንቆርጥም!!! እስከመጨረሻው አላህ ያደርሰናል… እስካሁንስ እዚህ የደረስነው በአላህ ፕሮግራም እንጂ መች በእኛ ልፋት ሆነና!!! ከምንጊዜውም በበለጠ ምርጫውን ለመጠምዘዝ የሚካሄዱትን ሸፍጦች ለመቃወም እና ሁሌም በሰላማዊና በሰላማዊ መንገድ ብቻ መብታችንን ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆን አለብን!!! እኔ ይኸው ለእናንተ መረጃውን በማድረስ ሃላፊነቴን ተወጥቻለሁ! ሁላችሁም ይህን ፅሁፍ ታግ እና ሼር በማድረግ፣ ፕሪንት አድርጎ በፎቶኮፒ ለሰዎች በማዳረስ በትእግስት ሃላፊነታችሁን ተወጡ!!! ‹‹አላህ ከትእግስተኞች ጋር ነውና!›› ‹‹የአላህን ሃይማኖት ብትረዱ አላህም ይረዳችኋል፡፡›› ቅዱስ ቁርአን Read more
  • good news ye shashemene mejlis be fedralu mejlis almeram ale!!!

    የሻሸመኔ መጅሊስ በፌደራሉ መጅሊስ እንደማይመራ ገለፀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 12/2004 በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሲመራ የቆየው የሻሸመኔ መጅሊስ ካሁን በኋላ በፌደራ ምክር ቤት እንደማይመራ ተናገረ፡፡ አዳማ ላይ በተደረገው የአህባሻ ስልጠና በኦሮሚያ መጅሊስ አመራሮች ውሃብይና አክራሪዎች በመባላቸው ልዩነት መፍጠሩን የሻሸመኔ የመጅሊስ ሀላፊዎች ገልፀዋል፡፡ የሻሸመኔ የእስልምና ጉዳይ የኦዲተር ኮሚቴ እንደገለፁት የፌደራልና የኦሮሚያ መጅሊሶችን የሚሠጡት የአህባሽ ስልጠና ባለመቀበላችን መዋቅሩን ያልጠበቀ የሥራ እግድ ደብዳቤ ተፅፎልናል ብለዋል፡፡ የፌደራልና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች በሻሸመኔ ከተማና በአርሲ ዞን ያሉ ሙስሊሞች ውሃቢይዎችና አሸባሪዎች ናችሁ ብለው መፈረጃቸውንም የኦዲተር ኮሚቴው ገልፀዋል፡፡ የሻሸመኔ ሙስሊም ነዋሪዎች በሁለቱም ነዋሪዎች መጅሶቹ ላይ ተቃውሞአቸውን እያቀረቡ ሲሆን የሻሸመኔ መጅሊስ ከህዝቡ ጎን ነው ሲሉ በኢትዮጲያ ደረጃ ለመንግስት ጥያቄ ያቀረበው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እንደሚደግፍም ጠቁመዋል፡፡ Read more
  • Media hula ye ethiopia muslim lay tenesa ende ? ሪፖርተሮች>>መንግሥት ጣልቃ ለመግባት ተገዷል ale

    የሙስሊሙ ማኅበረሰብን የሚያወዛግበው አክራሪነት ጣልቃ ገብነት ወይስ አስተምህሮ? SUNDAY, 18 MARCH 2012 00:00 BY HENOCK YARED , YEMANE NAGISH & SOLOMON GOSHU HITS: 853 View Comments ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በእስልምና ሃይማኖት ሥር ያሉ በዋህቢያንና በአሕባሽ አስተምህሮ የአካሄድ ልዩነታቸውን ቢያሳዩም፣ ልዩነቱ እየተካረረ በመሄዱ መንግሥት ጣልቃ ለመግባት ተገዷል፡፡ የቡድኖቹ መሠረታዊ ልዩነት ከዋነኛዎቹ የእስልምና አስተምህሮቶች (መዝሃብ) የተነሳ ቢሆንም፣ አንዱ አክራሪ ሌላው ለዘብተኛ ተደርጎ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ ቡድኖቹ በቁርአን፣ በሃዲስ (በነብዩ መሐመድ አስተምህሮት) ላይ ልዩነት የሌላቸው ሲሆን፣ በአተረጓጎምና በአስተያይ (ቂያስና ቂጅማ) ላይ እንደሚለያዩ ይነገራል፡፡ ከ7ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ ሃይማኖት ከፖለቲካ፣ ከማንነትና ከባህል ጋር ቁርኝነት ያለው ቡድን ሆኖ ቢቆይም በቅርብ ዓመታት ከውጭ ሲታይ ሃይማኖታዊ የሚመስል ውስጡ ግን ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ልዩነት በሁለቱ ቡድኖች መካከል ተፈጥሯል፡፡ ይህ ልዩነት ዓለም አቀፋዊ እንጂ አገር በቀል እንዳልሆነም ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ሪፖርተር ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ የታሪክ፣ የፖለቲካና የሕግ መነሻዎችን በማንሳት የሁለቱን ቡድኖች አለመግባባት ከራሳቸው አንደበትና የመንግሥትን ጣልቃ የመግባት ምክንያት ከመንግሥት አንደበት አንባቢው እንዲረዳ በሚከተለው መንገድ አቅርቦታል፡፡ በዓለም ታሪክ የመንግሥትና የሃይማኖት ተቋማት የእርስ በርስ ግንኙነት ጠንካራ በመሆን ለሺሕ ዓመታት ቆይቷል፡፡ በዚህም በአብዛኛው የመንግሥት ቢሮክራሲ አመራር በሃይማኖት ተቋማት የሚፀድቅበት ሁኔታ (The Divine Power Theory) ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ የእርስ በርስ ግንኙነት በአንዱ ወቅት የመንግሥት ቢሮክራሲው በሌላ ወቅት የሃይማኖት ተቋማቱ የበላይነት የሚይዙበት ሁኔታ ነበር፡፡ በ15ኛው ክፍለ ዘመን የተቀጣጠለው የህዳሴ ንቅናቄ ለመጀመሪያ ጊዜ የሃይማኖት ተቋማት ከመንግሥት ተለይተው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ጠቁሞ ነበር፡፡ ይህም ሃይማኖት መንግሥት በሳይንስ፣ በትምህርትና በዲሞክራሲ ጽንሰ ሐሳቦች ላይ ትኩረት እንዳይሰጥ ይከላከላል ከሚል መነሻ ሐሳብ የተሰጠ ነበር፡፡ ነገር ግን ሃይማኖትና መንግሥት ተነጣጥለው መሥራት አለባቸው የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ተቀባይነት ለማግኘትና የሕግ መሠረት ለመያዝ ተጨማሪ መቶ ዓመታትን ጠይቋል፡፡ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን መጠናቀቅ ተከትሎ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን ተቀባይነት ባላቸው መርሆዎች ለመምራት የተረቀቀውና እ.ኤ.አ. በ1945 ሥራ ላይ የዋለው የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር በአንቀጽ 1 ላይ ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ልዩነት/አድልኦ በዜጎች ላይ ሊፈጸም እንደማይገባ ያትታል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1948 የተረቀቀው ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ በአንቀጽ 18 ላይ የዜጎች የሃይማኖት መብት የማመንን ብቻ ሳይሆን እምነትን የመቀየር፣ ሃይማኖትን የማስተማር፣ ተግባራዊ የማድረግ፣ የማምለክና የመከተል ነፃነትን ጭምር እንደሚያጎናጽፍ አረጋግጧል፡፡ የዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ ቃል ኪዳን በአንቀጽ 18(3) ላይ መንግሥታት የሃይማኖት ወይም የእምነት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ከሕዝብ ደህንነት፣ ሰላም፣ ጤናና ሞራል አንጻር እንዲሁም የሌሎች ዜጎችን መሠረታዊ መብቶች ለመጠበቅ ገደብ ሊጥሉ እንደሚችሉና በእነዚህ ሁኔታዎች የመንግሥታቱ ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1981 የተረቀቀው ሃይማኖትና እምነትን መሠረት ያደረጉ ሁሉንም ዓይነት ያለመቻቻልና አድልኦ የማስወገድ የተባበሩት መንግሥታት ድንጋጌ በአንቀጽ 6 ላይ ዜጎች እንደ ግለሰብ የማመን፣ የማምለክና የመሰባሰብ መብት ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታቸውን ወይም እምነታቸውን በቡድን የማስተማርና መሪዎቻቸውን የማሰልጠንና የመመደብ፣ በሃይማኖት ጉዳይ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ግንኙነት የመፍጠር መብት እንዳላቸው ይገልጻል፡፡ በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ ሁኔታ የሃይማኖት ወይም የእምነት መብት የማመን፣ ያለማመንና እምነትን የመቀየር መብት (The right to believe, unbelieve and disbelieve) የተረጋገጠ ሲሆን፣ ይህ የመብት ጥበቃ በመንግሥትና በሃይማኖት ተቋማት ተለያይቶ መሥራት ላይ (Secularism) የተመሠረተ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከላይ የገለጽናቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ፈራሚ አገር ነች፡፡ መንግሥትና የሃይማኖት ተቋማት በአንደኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገባው የክርስትና እምነት ከአራተኛው ክፍለ ዘመን እስከ 1967 ዓ.ም. ድረስ የመንግሥት ሃይማኖት በመሆኑ አገሪቱ ለሌሎች እምነቶች የምትመች እንዳልነበረች የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡ ደርግ በሕግ የሃይማኖቶችን እኩልነት ቢያረጋግጥም፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) በተመሠረተበት ጊዜ በመንግሥት ምክር ቤት ሥር የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስቴር አቋቁሞ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በተግባር ያን ያህልም ለውጥ እንዳልመጣም ይነገራል፡፡ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ዜጎች ማንኛውንም እምነት የመከተል መብት እንዳላቸው፣ ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል መሆናቸውንና ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ መሆናቸውን በሕግም በተግባርም አረጋግጧል፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ከለላም ያለው መብት ሆኗል፡፡ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሥርም የሃይማኖቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አቋቁቋማል፡፡ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ለምን? የሃይማኖት ተቋማት የኅብረተሰቡን ሞራል፣ ሥነ ምግባርና መልካም እሴቶችን በማዳበር በጎ ተፅዕኖ በመፍጠር የመንግሥት አጋር መሆን ብቻ ሳይሆን የግለሰቦችን ነፃነትና ሰብዓዊ መብት በመግፈፍ በግለሰብና በማኅበረሰቡ ብሎም በመንግሥት ላይ አደጋ የመፍጠር አቅምና ጉልበቱ አላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የሚነሳው ትልቁ ጥያቄ የሃይማኖት ተቋማቱ መሪዎች በግለሰብ ደረጃ ወይም ደግሞ ተቋማቱ ይፋዊ በሆነ መንገድ በሃይማኖት ምክንያት የአገሪቱን ሕግ ከተላለፉ ከሕግ የበላይነት ሊያመልጡ ይችላሉ ወይ የሚል ነው፡፡ ሃይማኖቶች እርስ በርስና በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የታቀፉ ቡድኖች ግጭት የተለመዱ ቢሆንም፣ ከሃይማኖት ቡድኑ ውጪ አገርን፣ ሰብዓዊ መብትን፣ የግለሰብና የቡድን መብትን፣ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ደኅንነትን የመንካት አቅሙ ሰፊ ነው፡፡ በተለይ ሃይማኖታዊ አክራሪነት የሃይማኖት መብት አካል የሆነውን ያለማመንና ትችት የመሰንዘር ብሎም ከነበረበት የሃይማኖት እምነት ወይም ቡድን የተለየ ግለሰብና ቡድን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጭቆናዎች ባለፉት 20 ዓመታት እየጨመረ በመምጣት የዓለም ስጋት እስከመሆን ደርሷል፡፡ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች እርስ በርስና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ በፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያኖችና አሁን በቅርቡ ደግሞ በእስልምና እምነት ሥር ያሉት የዋህቢያና የአሕባሽ ቡድኖች ግጭትን ለማብረድ የኢፌዴሪ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ለመግባት ተገዷል፡፡ ለመሆኑ የመንግሥት ጣልቃ መግባት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ተቀባይነትስ አላቸው? 1. ብሔራዊ ደኅንነት ከላይ እንደተገለጸው መንግሥት የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ ሊገባ ይችላል፡፡ በእርግጥ በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የተነሳው የሐሳብ ልዩነት የመንግሥትንና የሕዝብን ሰላምን ደኅንነት አደጋ ላይ ጥሏል ለማለት የሚቻለው መቼ ነው? ለሚለው ጥያቄ ግልጽ የሆነ ምላሽ የለም፡፡ ቢሆንም የግልጽና ተጨባጭ አደጋ መለኪያ (Clear and Imminent Danger Test) ወይም የአደገኛ አዝማሚያ መለኪያ (Dangerous Tendency Test) እንደ ሁኔታው ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ በአንድ ሃይማኖት ውስጥም ሆነ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ባሉ የሃይማኖቱ መሠረታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ያሉ አለመግባባቶች ላይ ሐሳብን በነፃነት መግለጽና መደራጀት ብሎም በአስተምህሮቶቹ ዙሪያ ደጋፊ የማሰባሰብ የውትወታ ሥራ (Advocacy) የሃይማኖት መብት አካል ቢሆንም፣ ነፃ የሐሳብ ልውውጡ የአገርን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ ወደሚጥል ተግባር የሚቀየር ከሆነ (Adversive Advocacy) የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሞኑ በሁለት የተለያዩ የእስልምና ቡድኖች መካከል ያደረገው ጣልቃ ገብነት ከደኅንነትና ሰላም ጋር ብሎም ከሽብርተኝነት ጋር የተገናኘ ማስረጃ አግኝቻለሁ ማለቱ የግልጽና ተጨባጭ አደጋ መለኪያን መጠቀሙንና የሐሳብ ልዩነቱ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚለውጥ መሆኑን በተጨባጭ ማረጋገጡን በመግለጽ ጣልቃ ገብነቱ ተቀባይነት እንዳለው እየገለጸ ነው፡፡ 2. የግለሰቦች መብት ጥበቃ ዜጎች የመረጡትን እምነት የመከተል መብት ያላቸው ከሆነ ይህ መብት በእምነቱ ላይ ያላቸውን የሐሳብ ልዩነት የማራመድ መብትንና ጭራሹን ያለማመን መብትን ይጨምራል፡፡ አሁን በሁለቱ የእስልምና ቡድኖች መካከል የሐሳብ ልዩነቱን የሚያራምዱት ቡድኖች አንዱ አንዱን ‹‹እስላም አይደለም›› እስከ ማለት መድረሳቸውን የሚገልጹት አስተያየት ሰጪዎች፣ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት የአገሪቱን ሰላም ከማስከበር ዘሎ ለእምነቱ ተከታይ ግለሰቦች የሕግ ከለላ በመስጠት መብታቸውን ሊያስከብር እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ በዚህም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ተቀባይ የሚሆንበት ተጨማሪ ምክንያት ይጠቁማሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት መጅሊስ የአሕባሽ ትምህርትን አምጥቶ ሥልጠና እንዲሰጥ የተገደደበት ምክንያት የዋህቢያ ፀረ ዜጎች እምነትና እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት ይንቀሳቀስ በሚል ነው፡፡ አቶ መረሳ ረዳ በፌዴራላዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖትና የእምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጄነራል በጉዳዩ ላይ ያስጠኑት ጥናት እንደሚያመለክተው፣ የዋህቢያ አስተምህሮ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ለተከሰቱ ሃይማኖታዊ ግጭቶች መሠረት መሆኑን ነው፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንም የሚጥስ ነው፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት ከመጅሊስ ጋር በመተባበር የአሕባሽ ትምህርት እየሰጠ ያለው፣ በአመለካከት ደረጃ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ ንቃት ህሊና ከፍ ለማድረግ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ሰሞኑን በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ የሰጡት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሬድዋን ሁሴን ይህንን አስመልክተው፣ ‹‹ችግሩ ሃይማኖታዊ አይደለም›› ያሉበትን እንዲህ በማለት አስረድቷል፡፡ ‹‹በሸሪዓ ሕግ ነው የምተዳደረው ብለህ ከተነሳህ፣ ሽፋኑ ሃይማኖታዊ ነው፡፡ ይዘቱ ግን ሃይማኖት አይደለም፣ ፖለቲካ ነው፡፡ የሸሪዓ መንግሥት መመሥረት ፖለቲካ እንጂ ሃይማኖት አይደለም፡፡ እስልምና በሸሪዓ ካልታገዝክ አይልም፡፡ በሸሪዓ የመተዳደር አጀንዳ የሥልጣን ፍላጎት እንጂ የእስልምና ግዴታ አይደለም፡፡ የሥልጣን ጥያቄ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በሌሎች ሃይማኖቶችም በተለይ በኦርቶዶክስ ‹አንድ አገር፣ አንድ ሃይማኖት› የሚለው አስተሳሰብ በመጥቀስ፣ ‹‹ሽፋኑ ከእምነቱ ጋር ዝምድና የለውም፤›› ይላሉ፡፡ መንግሥት ዋህቢያ የሚባለውን እንቅስቃሴ እስላማዊ መንግሥትን መመሥረትን ጨምሮ የዜጎች ሕገ መንግሥታዊ የእምነት ነፃነት በመጣስ የራሱን ብቻ እንዲከተሉ የሚያስገደድ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ትምህርቱ ከሳዑዲ ዓረቢያ የመጣ ሲሆን፣ ሃይማኖትና ሥልጣን በጋራ ተደጋግፈውና ተስማምተው አንዱ ሌላውን ተሸክሞ የሚኖርበት መሆኑን ይገልጻል፡፡ የዋህቢያ ትምህርት፣ ባህላዊ የእስልምና እምነትን አስቀርቶ በቅዱስ ቁርአንና በኻዲስ ትምህርት የሚያምኑ አስተምህሮ መሆኑን የሚገልጹ ደጋፊዎቹ ደግሞ፣ የአሕባሽን ትምህርት ቅዱስ ቁርአን መሠረታዊ ማዕዘኖችን ይጥሳል በሚል ይቃወማሉ፡፡ መንግሥት፣ ከመጅሊስ ጋር በመሆን የአሕባሽ ሥልጠና ትምህርት መስጠቱ መፍትሔ እንደማይሆን ይገልጻሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ‹‹እስልምና ጉዳዮች›› እና ‹‹ሰላፍያ›› የመሳሰሉ ሚዲያዎች የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት አክርረው የሚቃወሙ ሲሆን፣ መንግሥት ከእምነት እጁን እንዲያወጣ ይጠይቃሉ፡፡ አቶ አደም ካሚል የተባሉት በሳዑዲ ዓረቢያ ላለፉት 30 ዓመታት የኖሩ ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ፣ በመንግሥት እየተፈጠረ ያለው ጥርጣሬና ችግር መነሻ የመጅሊስ ድክመት መሆኑን ለሪፖርተር ያስረዳሉ፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ መንግሥት ከሚለው በተቃራኒ የአሕባሽ ትምህርት መሠረታዊ የእስልምና እምነት የሚጻረር መሆኑን ነው፡፡ መፍትሔውም፣ መጅሊስ (እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት) ማጠናከርና በተማረ የሰው ኃይል እንዲሠራ ማድረግ ነው፡፡ እንደ እሳቸው እምነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስልምና መሠረት ያለውና የራሱ የፀና ትምህርት ስላለው በማናቸውም መጤ እምነቶች አይጠቃም፡፡ ዋህቢያ የሚባለው እምነት የለም የሚሉት እኚሁ ምሁር፣ አይዲዮሎጂው ግን ምንም ክፋት እንደሌለው ያስረዳሉ፡፡ መንግሥት አሕባሽ የተባለው አስተምህሮ ማምጣቱን በመቃወም፡፡ በአሁኑ ወቅት፣ በአወሊያ ትምህርት ማዕከል የተከሰተው ውዝግብ የዚሁ አካል ሲሆን፣ መንግሥት አንዳንድ ለውጦች ለማድረግና ሥርዓተ ትምህርቱን ለማድረግ የተንቀሳቀሰው የዋህቢያ ማፍለቂያ ቦታ ሆኗል በሚል ነው፡፡ የመንግሥትንና ሕገ መንግሥታዊ የዜጎች መብት የሚጥስ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በምክንያትነት እየጠቀሰ ሲሆን፣ መንግሥትን የሚቃወሙ በበኩላቸው በጣልቃ ገብነት እየወነጀሉ ነው፡፡ የአወሊያው ውዝግብ የሕዝበ ሙስሊሙን ወቅታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለማፈላለግ የተወከልኩ ኮሚቴ ነኝ፤ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ሙስሊሞች በተፈረመ ፒቲሺን ውክልና አለኝ፤ የሚለው ኮሚቴ በአወሊያ በየሳምንቱ ዓርብ መሰባሰብ ከጀመረ 10ኛ ሳምንቱን እንደያዘ ይናገራል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ መሐመድ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ጥያቄዎቻቸው የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ የአወሊያ ትምህርት ቤት በቦርድ ስለመመራትና የአሕባሽ አስተምህሮን በተመለከተ ነው፡፡ ‹‹አመራሮቹ የመጡት በ2001 ዓ.ም. ላይ ነው፡፡ የቀድሞዎቹ ሲታገዱ ባለአደራ ሆነው የመጡ እንጂ ውክልና ተሰጥቷቸው የመጡ አይደሉም፡፡ ዛሬ ነገ ምርጫ ይካሄዳል ቢባልም አልተካሔደም፤ የመጀመሪያው ጥያቄ ሕዝበ ሙስሊሙ የመረጣቸው መሪዎች ሊቀመጡ ይገባል የሚል ነው፡፡›› የአሕባሽ አስተምህሮን በተመለከተም፣ ‹‹አስተምህሮው ከእስልምና መሠረታዊ አስተምህሮ ወጣ ያለ ነው ብለን ነው የምናምነው፡፡ አስተምህሮው በራሱ በግሉ በአገሪቱ ውስጥ ሊንቀሳቀስና ተቋም መሥርቶ ሊያስተምር ይችላል፤›› ያሉት ኡስታዝ አቡበከር፣ አሕባሽ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የማይቀበለው አስተሳሰብ ነውና በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተቋም በሆነው መጅሊስ ከለላና መሪነት ይባስ ብሎ የማስገደድ ተግባር እየተፈጸመ ያለው የተወሰነ ፍላጎት ባላቸው የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አጋዥነት ሳይቀር በየመስጂዱ የሚሰጠው ትምህርት እንዲቆም እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ አወልያ ተቋምን በተመለከተም አወልያ በሕዝብ ለረዥም ጊዜ ሲመራ ቆይቷል፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መጅሊስ (እስልምና ጉዳይ) ተረክቦታል፡፡ ከተረከበው በኋላ ተቋሙን የማሳደግ ተግባር አልፈጸመም፡፡ ተቋሙን የበለጠ ከማሻሻል ያሉበትን ችግሮች ከመቅረፍ ይልቅ አሠራሩን የመቀየርና ይባስ ብሎ የማዳከም ሁኔታ ታይቶበታል ያሉት ገጽታውን በማመልከት ነው፡፡ ‹‹አወሊያ የሙስሊሙ ብቸኛና ትልቁ ተቋም ነው፡፡ ቢያንስ በውስጡ መስጊድ፣ ኮሌጅ፣ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታል፣ የሕፃናት ማሳደጊያና ሁሉን ነገር የያዘ የተሟላ ተቋም ነው፡፡ ይህን የያዘ ተቋም አላግባብ ዕርምጃ ሲወሰድበት ሙስሊሙ ማየት ስለማይችል አገራዊ ጥያቄ ሆኖ መጥቷል፡፡›› የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ስድስት ሰዓት የፈጀ ውይይት መደረጉን ያስታወሱት ኡስታዝ አቡበከር፣ በመድረኩ የተሰጠው ምላሽ የሚመስል ግን ማብራርያ የሚፈልግ ብዥታ እንዳለው የመጅሊስ ምርጫ ይካሄዳል ቢሉም መቼ እንዴት፣ በምን መልኩ ይካሄዳል? የሚያስመርጠውንስ ገለልተኛ ማን ይመርጠዋል ቢባል ምላሽ ያልተገኘበት በማለት ገልጸዋል፡፡ አወሊያን በተመለከተም ሕዝበ ሙስሊሙ የሚወክላቸው ሰዎችና ምሁራን በቦርድ እንዲመሩት ቢጠየቅም፣ ቦርዱን ማን ያስመርጣል? በሚለውም ስምምነት ላይ እንዳልደረሱና ድጋሚ ለውይይት ይጠራሉ ብንልም አልጠሩንም ብለዋል፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅልንም ጠይቀን ምላሽ እየጠበቁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው ሁኔታ ስለዋህቢያም ይነሳል ብለን ለጠየቅነውም ሰብሳቢው ሲመልሱ፣ ‹‹ዋህቢያ ስል ተቋማዊ ሆኖ ባለቤት ይዞ የመጣ አካል ካለ ያ አካል ነው ባለቤት ሆኖ የሚቀርበው፤ ነኝ የሚል አካል ካለ ዋህቢያ ነኝ ብሎ ስለሚያምንበት ሴክት መግለጽና ማስረዳት ግድ ይለዋል፣ ይገባዋል ብለን ነው የምናምነው፡፡ እዚህ ባለው ግን በአሕባሽና በመጅሊስ ላይ ባለው ሒደት ውስጥ ዋህቢያ የሚል ነገር የለም፣ ከሙስሊም ማኅበረሰብ ጋር እየተካሄደ ያለ ተቋምን ወይም መሠረታዊ እምነትን በተመለከተ እየተደረገ ያለ ፍጥጫ እንጂ ከሌላ ሴክት (የእምነት ክፍል) ጋር የተያያዘ አይደለም፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡ በወቅታዊ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤት አሕባሽ የሚባል ዲን (አስተምህሮ) እንደሌለ አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ‹‹አሕባሽ የሚባል ዲን በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ በማንኛውም ዓለም የለም፡፡ አሕባሽ ማለት ኢትዮጵያውያን ከሚል የመጣ ነው፡፡ የኢትዮጵያዊ ሼኽ የሚከተሉ ወይም እርሱ ያስተማራቸው በሚል አሕባሽ መጣ እንጂ ዲን ማለት አይደለም፤›› በማለት አብራርቷል፡፡ ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ ክልሎች እየተሰጠ ያለው ሥልጠናም የሙስሊሙን የዲን ዕውቀት ለማጐልበት ታስቦ ትክክለኛውን መንገድ እንዲይዙ ለማድረግ የተከናወነ እንጂ፤ አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት ሌላ እምነት ለመስበክ አይደለም፡፡ በምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሼክ ኢዘዲን አብዱል አዚዝ አገላለጽ፣ በትምህርት ሒደቱ ላይ በጠቅላላው ማስረጃ ተደርገው የተጠቀሱት ከቅዱስ ቁርአን ከኻዲስ፣ ከኢጅማዕና ከአራቱ መዛሂብ መሪዎች ሲሆን፣ ሥልጠናው እየተሰጠ ያለውም በፈቃደኝነት ነው፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤት በኡላማዎች የሚሰጠውን ትምህርት የተከታተለ መሆኑን የገለጹት የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ እንዳሉት፣ ሥልጠናውን በአሁኑ ጊዜ መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት ነብዩ መሐመድ እንደገለጹት አፍራሽ የሆኑ አስተሳሰቦች፣ ብቃትና ዕውቀት የሌላቸው፣ ያለፉትን ኡላማዎች የሚያጣጥሉ ሰዎች የሚመጡበት ወቅት በመሆኑ ነው፡፡ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሔድ ምክር ቤቱ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ መወሰኑንና ምርጫው በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወን በመሆኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራው እየተካሔደ መሆኑንና ኅብረተሰቡም ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ያመለከተው የኡላማዎች ምክር ቤት፣ ለዚህ ምርጫ የሚመጡ ሰዎች ለሙስሊም ኅብረተሰብም ሆነ ለአገራችን የሚበጁ፣ ሙስሊም ኅብረተሰቡን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የማይወስዱ ሰዎች መሆን እንዳለባቸው ጥሪ አድርጓል፡፡ አወሊያ ትምህርት ቤት ግን እንደሌሎች ትምህርት ቤቶችና መስጂዶች ሁሉ በመጅሊስ መተዳደር ያለበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ አያይዞም በአሁን ጊዜ ትምህርት ቤቱ መደበኛ ሥራውን እያከናወነ መሆኑን ተቋሙን ያስተዳድሩ የነበሩ ድርጅቶች የአገሩን ሕግ ተከትለው መሥራት ባለመፈለጋቸውና የሠራተኞችን ወጪ መሸፈን ባለመቻሉ የእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት በጀት መድቦ ሥራውን እንዲቀጥል ማድረጉን አብራርቷል፡፡ ትምህርት ቤቱ አፍራሽ ለሆኑ አስተሳሰቦች ሽፋን ሆኖ መቆየቱን የገለጸው የኡላማ ምክር ቤቱ መጋቢት 6 ቀን ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚነገረውንና የሚሠራውንም ነገር እያረጋገጠ መሄድ ይሻላል ነው የምንለው፤ ዝም ብሎ በተነሳው ወሬ ማጎብደድ አብሮ መጓዝ አይደለም፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ ወደ ግርግር የሚመሩ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡ ወይ ለጥቅማቸው ሲሉ ወይ ደግሞ ከውጭ የሚያገኙትን ነገር ፍለጋ በሙስሊሙ ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ስላሉ እነዚህን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፤›› በማለትም አሳስቧል፡፡ (ለዚህ ዘገባ ኃይሌ ሙሉ አስተዋጽኦ አድርጓል) Read more
  • AHBASH & SUFIYA

    አህባሽ እና “ሱፊያ” ኡባህ አብዱሰላም ሰዒድ (I want all of you to compare this article with what “Majlis” and Alquds says about “Sufi”) በቅርቡ የአንድ ታላቅ መስጊድ ኢማም በሱፊያ ላይ ያተኮረ ኹጥባ ማድረጋቸውን ሰማሁ፡፡ ታዲያ አንዳንድ የፌስቡክ ጓደኞቼ ኢማሙ “እኛ ወሀቢዎች አይደለንም፤ እኛ ሱፊ ነን፤ አሁን ጊዜው የሱፊያ ነው፤ ሱፊያ ደግሞ የሰሀባዎችና የነቢያችን መንገድ ነው፤ ወዘተ...” ብለው ተናግረዋልና ስለዚህ ጉዳይ የምታውቂው ነገር ምን አለ?” የሚል ጥያቄ አቀረቡልኝ፡፡ በሰማሁት አባባል በእጅጉ ተገረምኩ፡፡ አዘንኩ!! ምን እንደማደርግም ግራ ገባኝ፡፡ ኢማሙ እንዲህ አይነት ተራ ንግግር በኹጥባ ላይ ማድረጋቸውን ለማመን ቢከብድም በራሴ መንገድ ባደረግኩት የማጣራት ሙከራ ነገሩ እርግጥ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ በሌላ በኩል ለነዚያ ጓደኞቼ የሚሆን ምላሽ በዚያች ቅጽበት መስጠቱ ከበደኝ፡፡ ምክንያቱም የተሰውፍ መጽሀፍት በአጠገቤ የሉም (መካሺፉል ቁሉብ ከሚለው የኢማም አቡ-ሐሚድ አል-ገዛሊ መጽሀፍ በስተቀር)፡፡ በኢንተርኔት ላይ በተሰውፍ ስም የተለቀቁ ዌብሳይቶች ደግሞ ከጥቂቶቹ በስተቀር ምንም እምነት የሚጣልባቸው አይደሉም፡፡ ነገር ግን አህባሽ ሙስሊሞችን ከሚያጭበረብርባቸው ዘዴዎች አንዱ “እኛ ሱፊዎች ነን” የሚለው ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ስለማውቅ ዝም ከማለት የቻልኩትን ያህል ልጻፍላቸው በማለት ተነሳሁ፡፡ ወደ ዋናው ጽሁፍ ከመግባታችን በፊት ግን መጠነኛ ማሳሰቢያ አለኝ፡፡ ይህንን ጽሁፍ ስጽፍ መነሻ የሆነኝ በአብዛኛው ድሮ ካነበብኩት ሀሳብ የተረፈኝ መጠነኛ እውቀት እንጂ በቅርብ ጊዜ ያነበብኩት መረጃ አይደለም፡፡ ስለዚህ የመረጃ ክፍተት ሊኖር እንደሚችል አምናለሁ፡፡ የጽሁፌን መልእክት ለማገናዘብ የሚፈልግ አንባቢያ ሰይድ አቡል-አእላ መውዱዲ የጻፉትን Towards Understanding Islam፤ አቡል ሐሚድ አል-ገዛሊ የጻፉትን አል-ኢሕያእ ኡሉሙድዲን እና መካሺፉል ቁሉብ፣ ሼኽ አብዱልቃዲር አል-ጄይላኒ የጻፉትን “አል-ጉንያ ሊጣሊብ ጠሪቀል ሐቅ”፣ ታዋቂው ገጣሚ ፈሪዱዲን አጣር የጻፈውን “ተዝኪራቱል አውሊያ” ወዘተ.. የመሳሰሉ መጽሀፍትን መመርመር ይችላል፡፡ ተሰውፍ “ተሰውፍ” (Sufism) በጥሬ ትርጉሙ “ሱፍ መልበስ” ማለት ነው፡፡ በተገቢው መንገድ ሲተረጎም ግን “የልብ ጥራት” ማለት ነው፡፡ ሙስሊም የሆነ ሰው ልቡ በአካሉ ከሚያደርገው ኢባዳ ጋር በእኩል ሁኔታ እንድትራመድለት ሲፈልግ ልዩ ልዩ ጥበባዊ ዘዴዎችን የሚማርበት መንገድ ነው- “ተሰውፍ”፡፡ ይህም ልብን ከልዩልዩ የልብ በሽታዎች ማጥራት ማለት ነው፡፡ በቁርአንና በሀዲስ በስፋት እንደተገለጸው ሰዎች ከፈጣሪ ጋር ያላቸውን ትስስር የምታበላሽባቸው አንዲት አካል አለች፡፡ እርሷም ልብ ናት፡፡ ሙእሚኖች ቁርኣናዊ ግዳጃቸውን በተገቢው መንገድ ለመወጣት ከፈለጉ ልባቸውን ከበሽታ ማጥራት አለባቸው፡፡ በሌላ በኩል ፈጣሪያችን አላህ (ሱ.ወ.) ለምንሰራቸው መልካም ስራዎች የሚከፍለንን ምንዳ (አጅር) የሚወስነው የልባችንን ጥራት በመመዘን ነው፡፡ በከፍተኛ የልብ ጥራት የአንድ ብር ሰደቃ የሰጠ ሰው ከፍተኛ ሽልማት አለው፡፡ ሰውየው መካከለኛ የልብ ጥራት ካለው ሽልማቱ ያንስበታል፡፡ የልብ ንጽህናው በጣም የጎደፈ ሰው ደግሞ ሽልማቱ እጅግ ዝቅተኛ ነው (ሰውዬው መቶ ብር ቢሰጥ እንኳ በንጹህ ልብ አንድ ብር የሰጠውን ሰው ያህል ሽልማት አያገኝም)፡፡ ልቡ ሙሉ በሙሉ የቆሸሸ ሰው ግን ከአላህ ዘንድ ምንም ሽልማት አያገኝም፡፡ እንግዲህ ይህንን የልብ ጥራት ማምጣት የሚቻለው እንዴት ነው? ኡለማ ለዚህ ጥያቄ የሚሆን ምላሽ ሲፈልጉ ነው “ተሰውፍ” የሚባለው አስገራሚ (አንዳንድ ጊዜ አወዛጋቢ) ኢስላማዊ የትምህርት ዘርፍ የተወለደው፡፡ ተሰውፍን እንደ አንድ የትምህርት ዘርፍ አድርጎ ማስተማር መቼ እንደተጀመረ በትክክል አይታወቅም፡፡ በርካታ ምንጮች ታዋቂዎቹን የበስራ ምሁራን ሐሰን አል-በስሪንና ራቢአቱል አደዊያን እንደ ጀማሪዎች ይጠቅሳሉ፡፡ ለመጀመሩ ሰበብ የሆነውም በጊዜው የነገሰው የልዩ ልዩ ፊርቃዎች (ሺዓ፤ ኻዋሪጅ፤ ሙርጂአ፤ ጀሀሚያ፤ ሙእተዚላ፤ ቀደሪያ፤ ጀብሪያ ወዘተ…) ሽኩቻ እንደሆነ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡ በተሰውፍ ላይ የሚያተኩሩ መጽሀፍት መጻፉንም ማን እንደጀመረው በርግጥ አይታወቅም፡፡ እንደሚመስለኝ ከሆነ የተሰውፍ መጽሀፍት መጻፍ የጀመሩት ከሂጅራ በኋላ በ4ኛው መቶ አመት ገደማ፤ ማለትም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ900 አ.ል. በኋላ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በ10ኛው፤ በ11ኛውና በ12ኛው ክፍለ ዘመናት ፈሪዱዲን አጣር፤ አቡ ሀሚድ አል-ገዛሊ፤ አህመድ አል-ሪፋኢ፤ ሼኽ አብዱልቃዲር አል-ጁይላኒ ወዘተ… የመሳሰሉ ምሁራን በተሰውፍ ላይ ያተኮሩ በርካታ መጽሀፍትን አበርክተዋል፡፡ ተሰውፍና የልብ በሽታዎች ልባችን የሚቆሽሸው በተለያዩ በሽታዎች ነው፡፡ እነዚህ የልብ በሽታዎች ያሉበት ሰው ኢባዳውን በወጉ አያደርግም፡፡ ውሎውና ድርጊቶቹ ከኢስላማዊ አዳብ ጋር አይገጥሙለትም፡፡ ከግለሰቦችና ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ግንኙነትም የተስተካከለ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በዚህች አለም ብቻ ሳይሆን በወዲያኛውም አለም ታላቅ አደጋን ያስከትልበታል፡፡ ስለዚህ ከአደጋው ለመዳን ልቡን ከበሽታ ማጥራት ይጠበቅበታል፡፡ የሰውን ልብ ከሚያደርቁትና ኢማንን ከሚያጎድሉት በሽታዎች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ኒፋቅ፡- የሙናፊቅነት ስሜት ጡግያን፡- ጥመት ኪብሪያእ፡-ኩራት ጁብር፡ ትዕቢት ሪኣእ፡- ልታይ ልታይ ማለት ዘን፡- ከንቱ ጥርጣሬ ገፍላን፡- መሰላቸት ሻህዋእ፡- ከገደብ ያለፈ ስጋዊ ፍላጎት ወዘተ… አላህና መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ከነዚህ በሽታዎች እንድንጠቀቅ አስተምረውናል፡፡ የተሰውፍ ሰዎች ለነዚህ በሽታዎች የሚሆኑ መድሃኒቶችን ነው የሚያስተምሩት፡፡ የነዚህ መድሃኒቶች ምንጭ ቁርአንና ሱንና ነው፡፡ ልቡን ከነዚህ በሽታዎች ያጠራ ሰው ዒባዳውን በታላቅ ኹሹእ (የአላህ ፍራቻ) ማከናወን ይችላል፡፡ በተሰውፍ ከምንታከምባቸው መድሀኒቶች መካከል ከሁሉም የሚበልጠው “ዚክር” (አላህን ማስታወስ ) ነው፡፡ ቁርኣን “ልቦች በዚክር ይረጥባሉ” በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷልና!! እንግዲህ “ሱፊ” የሚባል ሰው ልቡን ከበሽታ ለመጠበቅ ሲል የተሰውፍን ጥበብ የሚከተል ማለት ነው፡፡ ይህ የተሰውፍ ጥበብ ደግሞ ከቁርአንና ከሀዲስ ጋር የማይጋጭ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ሰውየው ሌላውን ኢባዳ ትቶ ተሰውፍን ብቻ የሙጥኝ ብሎ መያዝ አይችልም፡፡ “ተሰውፍ” ሰውዬው በኢባዳ ላይ ብርቱ ሆኖ እንዲቆይ የሚረዱትን ጥበባዊ ዘዴዎች ያስተምረዋል እንጂ በራሱ የቆመ ለየት ያለ ኢስላማዊ ጎዳና ወይም የሸሪኣ ዘርፍ አይደለም፡፡ ማንም ሰው የተሰውፍ ዘዴዎችን ሳይማር ኢባዳውን ማድረግ ይችላል፡፡ “ልቤ በትእቢትና በኩራት ተወጥራለችና ምን ይበጀኛል?” ብሎ የሚጨነቅ ከሆነ መድሃኒቱን ከተሰውፍ መንገድ መፈለግ ይፈቀድለታል፡፡ እዚህ ላይ የታዋቂውን የሱፊ ጥበብ አዋቂ የሼኽ አብዱልቃዲር አል-ጄይላኒን ምሳሌዎች ልጥቀስ፡፡ ሼይኽ አል-ጄይላኒ “አል-ጉንያ ሊጣሊብ ጠሪቀል ሀቅ” በተባለ መጽሀፋቸው ውስጥ እንዲህ ይላሉ፡፡ መቼም ቢሆን አትማል፤ መማል ካስፈገለ ግን በአላህ ስም ብቻ ማል! በምላስህ አትዋሽ! ጥሩ ነገር ብቻ ተናገር! በመንገድህ ላይ በእድሜው ካንተ የሚያንስ ሰው ቢያጋጥምህ “ከርሱ የተሻልኩ” ነኝ ብለህ አታስብ፡፡ ከዚህ ይልቅ በልብህ “ይህ ልጅ በምድር ላይ የኖረበት ዘመን ከኔ እድሜ ያንሳል፡፡ ስለዚህ ሀጢአቱም ከኔ ያነሰ ነው” በል፡፡ በእድሜው ካንተ የሚበልጥ ሰው ከገጠመህ ደግሞ “ይህ ሰው በዚህች ምድር ላይ ከኔ እድሜ ለሚበልጥ ጊዜ ኖሯል፤ ስለዚህ ለአላህ ባደረገው ኢባዳ ከኔ ይበልጣል” በል እንጂ በመጥፎ ነገር አትጠርጥረወ፡፡ ደስ ይላል አይደል? ከማስደሰቱ ጋር መጠየቅ ያለበት ጥያቄ “ሼኽ አብዱልቃዲር የተናገሯቸው ነገሮች ከኢስላማዊው ሸሪዓ ጋር ይቃረናሉ ወይ?” የሚለው ነው፡፡ ሼኽ አብዱልቃዲር የጻፉት ነገር ከኢስላማዊ ሸሪዓ ውጪ አይደለም፡፡ ይልቅ ኢስላማዊ ሸሪዓን በትክክል ለመተግበር ያግዛል፡፡ ተሰውፍ ማለትም እንዲህ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ነው ሙስሊሞች ልባቸውን ከበሽታ የሚፈውሱባቸውን ልዩ ልዩ ምክሮች የሚሰጡ መጽሀፍት መጻፍ የተጀመሩት፡፡ አንዳንድ መምህራንም ሙሉ ጊዜያቸውን ለዚሁ ሰጥተው የማስተማሪያ ማእከላትን ያቋቋሙት ለዚሁ አላማ ነው፡፡ ተሰውፍ ሲበላሽ ጥንት በሰላማዊ ሁኔታ የተጀመረው ተሰውፍ ከዘመናት በኋላ መስመሩን ሳተ፡፡ ሰዎችን በሸሪአ ላይ የሚያበረታታ መሆኑ ቀርቶ ከሸሪአ የሚያስወጣ መሆን ጀመረ፡፡ ለምሳሌ፤ በተሰውፍ ስም ከሸሪአ ጋር የሚቃረኑ ተግባራትን መፈጸም ተጀመረ፤ ዳንስና ሙዚቃ እንኳ በተሰውፍ ስም ተፈቀዱ (ለምሳሌ በቱርክ ያሉትና “Whirling Dervishes” የሚባሉት የመውላዊ ጠሪቃ ተከታዮች የሚያደርጉትን የዳንስ ትርኢት “ዚክር” ነው ይሉታል፡፡ አስተግፊሩላህ!!) እንደ አል-ሀለጅ እና ኢብን አረቢ የመሳሰሉት “ሱፊ” ነን ባዮች ደግሞ ግልጽ የወጣ ኩፍር ውስጥ የሚያስገቡ ፍልስፍናዎችን በተሰውፍ ስም መጻፍና ማስተማር ጀመሩ፡፡ ለምሳሌ አለ-ሀለጅ “ማነው ሀቅ?” በሚል ጥያቄ ጀመረና “አነል ሀቅ”፤ ማለትም “አል-ሀቅ እኔ ነኝ” የሚል ፍልስፍና ላይ ደረሰ፡፡ እኛ ሙስሊሞች “አል-ሀቅ” የምንለው አላህን ብቻ ነው፡፡ ሰውዬው ግን ራሱን “አል-ሀቅ” ብሎ ጠራ፡፡ ይህንን እንዲተው ቢመከር እንቢ አለ፡፡ በዚህም የተነሳ በጊዜው የነበረው የባግዳድ ኸሊፋ በስቅላት ቀጣው፡፡ ከአይሁድና ክርስቲያን መነኮሳት ጋር የተቀራረቡ ሙስሊሞች በበኩላቸው በተሰውፍ ስም ምንኩስናን ወደ ኢስላም አስገቡ፡፡ አንዳንዶቹ ተሰውፍን ከልብ ንጽህና አርቀው ከአላህ ጋር በቀጥታ የምንነጋገርበት ጥበብ ነው እያሉ ከሸሪዓው ያነፈገጡ የግጥም ውዳሴዎችን የሚያቀርቡበት መድረክ አደረጉት፡፡ አንዳንዶቹ ከዚህም ራቅ ብለው ተሰውፍን ከአላህ በስተቀር ማንም ሊደርስበት የማይችለውን ስውር አለም (ገይብ) የሚመረምሩበት መነጽር አደረጉት፡፡ ተሰውፍ ኢስላማዊ ባህልን መከተል ሲገባው የባእዳን ባህል ተከታይ የሆነበት ሁኔታም ተፈጠረ፡፡ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ነገሩ ሁሉ ተቀየረና “ተሰውፍ” የአውሊያ መቃብሮች የሚመለኩበት የሽርክ ጋሻና መከታ ሆነ፡፡ ተሰውፍ በስተመጨረሻው ላይ እንደዚህ ውጥንቅጡ የወጣ ዝባዝንኬ ነገር ሆነ፡፡ ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው “ጠሪቃ” እና “ሀድራ” የሚባሉ ነገሮች መከሰታቸው ነው፡፡ “ጠሪቃ” የተሰውፍ ዚክር ከአንዱ ሼኽ ወደሚቀጥለው ሼኽ የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡ በጠሪቃው ውስጥ የሚታቀፉት ሼኾች እንደ ተማሪና መምህር ሳይሆን እንደ ጌታና ባሪያ ነው የሚተያዩት፡፡ ሀድራ ደግሞ አንድ ሼኽ ዚክርን የሚያስተምርበት ማእከል ማለት ነው፡፡ በኋላ ላይ ግን ሼኹ ራሱ የሚመለክበት ማእከል ሆኖ ተገኝ፡፡ ከዚህ ሌላ የሀድራ ሼኾች ራሳቸውን ወደ ፈውዳላዊ ባላባቶች እየቀየሩ ሀብት ያግበሰብሱ ገቡ፡፡ እነዚህን አላማዎች የሚደግፉላቸውን የቅጥፈት ወሬዎች፤ ተረቶች፤ ታሪኮች ወዘተ ማስወራት ጀመሩ፡፡ አላህ በቁርአኑ የተናገረው “የአላህ አውሊያ” የሚለው አባባል ትልቅ የማጭበርበሪያ ዘዴ ሆነ፡፡ በዚህ ውጥንቅጡ የወጣ ሁኔታ ውስጥ ነው በርካታ የተቃውሞ ድምጾች በተሰውፍ ላይ የተነሱት፡፡ ከነዚህ ድምጾች መካከል በጣም ከፍ ብሎ የተሰማው የሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ ድምጽ ነው፡፡ ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ በተሰውፍ ስም የሚነገድበትን አይን ያወጣ ኩፍር፤ ሽርክ፤ ቢድአና ባእድ አምልኮ በሀይለኛ ሁኔታ ተቃውሟል፡፡ ነገር ግን ኢብን ተይሚያህ አሁን እንደሚባለው ተሰውፍን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አላደረገውም፡፡ ሙስሊሞች በዚክር ከልብ በሽታ የሚፈወሱበትን “ተሰውፍ” በእጅጉ ደግፏል፡፡ ኢብን ተይሚያህ እነ ሼይኽ አብዱልቃዲር አል-ጀይላኒ ያስተማሩትን እውነተኛ ተሰውፍ በጣም ያበረታታ ነበር፡፡ እርሱ የተቃወመው በተሰውፍ ስም የሚካሄዱትን ከላይ የገለጽኳቸውን አስነዋሪ የሆኑ ኢ-ኢስላማዊ ድርጊቶችና አመለካከቶችን ነው፡፡ አህባሾችና የተሰውፍ አመለካከታቸው ከላይ የቀረበውን ትንተና ያነበበ ሰው አህባሾች በተሰውፍ ላይ ያላቸውን አመለካከት በቀላሉ ይረዳል ብዬ አምናለው፡፡ ስለዚህ ነገሩን በዚሁ እናሳጥረው፡፡ ለመሰናበቻ አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ በተለምዶ “ገሪባ” ሲባል ሰምታችኋል? ምን ማለት ነው? አህባሾች “ሱፊ” የሚሉት ልቡን ከበሽታ ለማንጻት የሚታገለውን እውነተኛ ሱፊ ሳይሆን ነፍሱን ለሼይኽና ለአውሊያ አምልኮ የሰጠውን እንደ “ገሪባ” አይነት ሰው ነው፡፡ የአውሊያ መቃብሮችን በየጊዜው እንድንዘይርና እንድንስም ለማድረግ ሲባል አህባሾች እንደ ምክንያት ከሚያቀርቡልን ሰበቦች አንዱ “ተሰውፍ” ነው፡፡ ነኡዙ ቢላህ!! በተሰውፍ ስም ግልጽ ሽርክ?? አላህ ከሽርክ ይጠብቀን!! በተሰውፍ ስም ሽርክን ከሚያበረታቱ አሳሳቾችም ይጠብቀን!! አሚን!!! Read more
  • be alamata 4 gelsboch taseru be ahbash mekniyat

    በአላማጣ ከተማ አራት ግለሰቦች መታሰራቸው ተገለፀ አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 4 2004 በአላማጣ አካባቢ የአህባሽን አስተምህሮት ለመስጠት የሄዱ ግለሰቦች ለማስተናገድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው፡ የአህባሽን አስተምዕሮት ለመስጠት አላማጣ አካባቢ ግለሰቦቹ የተንቀሳቀሱት ባለፈው ቅዳሜ ነበር፡፡ ሁለት ኢትጲያውያንና አንድ ሊባኖሳውያን የአህባሽ አስተምህሮት ለአምስት ቀናት በአላ አካባቢ ከሚገኘው መስጂድ ለመሰጠት ያሰቡት ጉዞ ግን አልተሳካም፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ የአካባቢው ሰዎች አስተምህሮቱን አንቀበልም በማለታቸው ነበር፡፡ አስተምህሮቱን በኃይል የመጫን እንቅስቃሴው ታዲያ እስር ማስከተሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ሁለት የመስጂድ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ግለሰቦችም መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡ Read more
  • SUNDAY, 11 MARCH 2012 ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በአፍራሽ ኃይሎች ብዥታ እንደተፈጠረበት የኡላማዎች ምክር ቤት አስታወቀ

    SUNDAY, 11 MARCH 2012 00:00 BY HAILE MULU HITS: 642 ethiopian reporter news - ‹‹አገሩ እየተበጠበጠ ያለው ከውጭ በሚመጣ ዕርዳታ ነው›› የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት - ‹‹የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጥያቄያችንን አልመለሰም›› የሙስሊም ማኅበረሰቡ ተወካዮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተለያዩ ቦታዎች እየሰጠ ያለውን ሥልጠና በማስመልከት በአንዳንድ ኃይሎች የሚናፈሰው አሉባልታ፣ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ ብዥታ የፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤት ገለጸ፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤቱ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ ክልሎች እየተሰጠ ያለው ሥልጠና የሙስሊሙን የዲን ዕውቀት ለማጐልበት ታስቦ ትክክለኛውን መንገድ እንዲይዙ ለማድረግ የተከናወነ እንጂ፣ አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት ሌላ እምነት ለመስበክ አይደለም፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤት በኡላማዎች የሚሰጠውን ትምህርት የተከታተለ መሆኑን የገለጹት የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሼክ ኢዘዲን አብዱልአዚዝ፣ በትምህርት ሒደቱ ላይ በጠቅላላው ማስረጃ ተደርገው የተጠቀሱት ከቁራን፣ ከሀዲስ ከኢጅማዕና ከአራቱ መዛሂብ መሪዎች መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ሥልጠናው እየተሰጠ ያለውም በፈቃደኝነት መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡ ዋና ጸሐፊው እንዳሉት፣ ሥልጠናውን በአሁኑ ጊዜ መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት ነብዩ መሐመድ እንደገለጹት አፍራሽ የሆኑ አስተሳሰቦች፣ ብቃትና ዕውቀት የሌላቸው፣ ያለፉትን ኡላማዎች የሚያጣጥሉ ሰዎች የሚመጡበት ወቅት በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ቀደም ሲል የነበሩትን ብርቅዬ ኡላማዎችን ፈለግ እንዲከተል ለማድረግ ታስቦ እንጂ፣ አዲስ እምነት የመጣ አለመሆኑን ሊያውቅ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡ በኡላማዎች ምክር ቤት የፈተዋ ዘርፍ ኃላፊ ሼክ ሙፍቲ አብዱልቃድር በበኩላቸው፣ በአሁኑ ጊዜ አገሩ እየተበጠበጠ ያለው ከውጭ በሚመጣ ዕርዳታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ትምህርት እየሰጡ ያሉት ኡላማዎች ከቁራንና ከሀዲስ ውጪ የተለየ ነገር ይዘው አለመምጣታቸውን የገለጹት ሼክ ሙፍቲ፣ በውጭ የገንዘብ ዕርዳታ የሚሽከረከሩት አንዳንድ ወገኖች የፈለጉትን ነገር ስላላገኙ ‹‹ኡላማዎች አዲስ ዲን (አስተምህሮ) ይዘው መጥተዋል፤›› በማለት ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ብዥታ ውስጥ የከተቱት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአወሊያ ትምህርት ቤት የሚሰበሰቡ ሙስሊሞች የእስልምና ምክር ቤቱ አስገድዶ እያስተማረ ነው የሚል ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ የኡላማዎች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼክ መሐመድ ሀሰን ግን የእስልምና ምክር ቤቱ ትምህርት የሚሰጠው በፈቃደኝነት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ኡላማዎች እያሉ ለምን ከሊባኖስ መሻሂዎችን አስመጣችሁ?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፣ ትክክለኛ ትምህርት እስካስተማሩ ድረስ ከየትም አገር ኡላማዎች መጥተው ቢያስተምሩ የሚያስከትለው ችግር እንደማይኖር ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ከሊባኖስ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች አገሮች የሚመጡ ኡላማዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አመልክተዋል፡፡ ‹‹የእስልምና ምክር ቤት ምርጫ መካሄድ አለበት፣ የአወሊያ ትምህርት ቤትም በመጅሊስ መተዳደር የለበትም፤›› በሚል በተደጋጋሚ እየቀረበ ያለውን ጥያቄ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የኡላማዎች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሼክ ኢዘዲን አብዱልአዚዝ፣ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. በተካሄደው የእስልምና ምክር ቤቱ ስብሰባ ምርጫ መካሄድ እንዳለበት መወሰኑንና ለዚህም ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አወሊያ ትምህርት ቤት ግን እንደ ሌሎች ትምህርት ቤቶችና መስጂዶች ሁሉ በመጅሊስ መተዳደር ያለበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በተያያዘ ዜና በብዙ ሺሕ በሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተወክለናል የሚሉ የኮሚቴ አባላት ለፌዴራል ጉዳዮች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ያልተመለሱላቸው መሆኑን አስታወቁ፡፡ በተከታታይ ለዘጠነኛ ሳምንት በአወሊያ ትምህርት ቤት በተካሄደው የጁማ ሶላት ተገኝተው ሪፖርት ያቀረቡት የኮሚቴ አባላት ለሙስሊም ማኅበረሰቡ እንደገለጹት፣ ‹‹የእስልምና ምክር ቤቱ እያስገደደ ማስተማሩን ያቁም፣ የመጅሊስ ምርጫ መካሄድ አለበት፤ አወሊያ ትምህርት ቤት የሕዝብ በመሆኑ በመጅሊስ ሥር መሆን የለበትም፤›› የሚሉ የመደራደሪያ ነጥቦች የቀረቡለት ፌዴራል ጉዳዮች አጥጋቢ ምላሽ መስጠት አልቻለም ይላሉ፡፡ እነኝሁ ተወካዮች እንደሚሉት፣ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ምርጫ ይካሄዳል ቢልም መቼና እንዴት እንደሚካሄድ አልገለጸም፤ አወሊያ ትምህርት ቤትም በተመረጡ የቦርድ አባላት ይተዳደራል ቢልም ቦርዱ ውስጥ ማን እንደሚካተት በግልጽ አልተናገረም፡፡ አህበሽ የተባለው አስተምህሮም አዲስ ነገር ባለመሆኑ በፈቃደኝነት ማስተማሩ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ‹‹ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ያቀረብነው ጥያቄ በቂ ምላሽ አላገኘም፤›› ያሉት ተወካዮቹ፣ ፌዴራል ጉዳዮች የመንግሥት አካል እንጂ መንግሥት ባለመሆኑ በቀጣይ የሙስሊም ማኅበረሰቡን ጥያቄ ይዘው ወደ ፓርላማ፣ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮና ወደሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በመውሰድ ሰላማዊ ትግል እንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል፡፡ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ሙስሊሞች በተፈረመ ፒቲሽን ውክልና አለን የሚሉት እነኝሁ የኮሚቴ አባላት፣ ከፌዴራል ጉዳዮች ጋር ሳይስማሙ እንደተስማሙ ተደርጐ በሚዲያ መግለጫ መሰጠቱን በመቃወም ለፌዴራል ጉዳዮች ደብዳቤ የጻፉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ለሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ የጻፉትንም ደብዳቤ በአወሊያ ትምህርት ቤት ለተሰበሰቡት የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ማንበባቸውንም አስታውቀዋል፡ bilal tube comment >> we are asking who is ethiopain ulema mekerebet they are same mejils enesu rasachewu meweged albeachew፡ Read more
  • ke 270,000 yemtegu yeharer newariwoch ahbashen teqawemu

    የመጅሊስን አመራር በማውገዝና የአህባሽን አስተምህሮት በመቃወም ከሐረር ክልል ከ270 ሺ በላይ ነዋሪዎች የተቃውሞ ድምፃቸውን አሰሙ መጅሊስን አመራር የአህባሽን አስተምህሮት በመቃወም ከሐረር ክልል ሙስሊሞች ቅሬታቸውን ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ፅ/ቤት ትላንት አቀረቡ፡፡ ተወካዮቹ መንግስተ ለህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ሰሞኑን ይፋ ያደረገው ምላሽ ስላላስደሰታቸው ቅሬታቸውን ለማቅረብ ተገደዋል፡፡ ምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ ሁሉሉም ወረዳዎች ጨምሮ ከሐረር ድሬደዋ ከተሞች የሚገኘውን ህዝብ ሙስሊም በመወከል የመጡት አራት ተወካዮች ናቸው ትላንት በህዝብ የተፈረመውን የተቃውሞ ፒቲሽን ያስገቡት ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክላላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት ተወካዮቹ ለሬዲዮ ቢላል እንደገለፁት የክልሉ ሕዝብ ይህንኑ የተቃውሞ ድምፅ ለክልሉ ምክር ቤት አመራሮች ቢያሳውቅም ምላሽ አላገኘም ፡፡ እናም ለፌደራል መንግስት ለማሳወቅ ተገደዋል በሃረርና አቅራቢያ የሚገኙ የኦሮሚያ ወረዳዎች ያቀረቡት ቅሬታ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ፅ/ቤት መግባቱን ነው የገለፁት ፡፡ በአወሊያ የህዝብ ንቅናቄ የተቋቋመው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ለመንግስት ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ የመንግስትን ምላሽ ሲጠባበቁ እንደነበር ተወካዩ ገልፀዋል፡፡ ይሁንና በመንግስት የተሰጠው ምላሽ አላረካቸውም ግልፅም አልሆነም እናም የህዝቡን ቅሬታ ለማወቅ መገደዳቸውን ነው ያመለከቱት፡፡ Read more
  • half million Ethiopian Muslim in awollya today 500,000 የሚጠጋ ሙስሊም ህብረተሰብን የአወልያ ዉሎ

    አላሁ አክበር!!!አላሁ አክበር!!! አምስ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሙስሊም ህብረተሰብን ያስተናገደዉ የአወልያ የጁምአ ዉሎ!!!! በዛሬዉ እለት በአወልያ አምስ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሙስሊም ህብረተሰብ ለጁምአ ሰላትእና ዉጤት ለመስማት እንደተገኘ ተገለፀ::የጁምአ ሁጥባ በአወልያ መስጂድ ምክትል ኢማም በኡስታዝ ሱለይማን የቀረበሲሆን ሁጥባዉም የአህባሽን ጥመት በማስመልከት የቀረበ ነበር::ሁጥባዉም እንደተናቀቀ የጁምአ ሰላት በኡስታዝ ሱለይማን ኢማምነት የተሰገደ ሲሆን በሰላቱም ላይ በተደረገዉ የቁኑት ዱአ የአብዛኛዉ ሙስሊም አይን በእንባ እንደታጠበ ተመልክቷል:: ሰላቱም ከተጠናቀቀ ቡሀላ መድረክ መሪዉ መድረኩንበመረከብ ህዝቡ አንድነቱን እስከመጨረሻዉ ለመጠበቅ እጅ ለእጅ በመያያዝ ቃልኪዳን እንዲገቡ በማድረግ ፕሮግራሙን መጀመሩን በተክቢራ አብስሯል::የመጀመሪያዉ ፕሮግራም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ከመንግስት ጋር የሙስሊሙ ተወካዮችያደረጉትን ዉይይት ምን ይመስል እንደነበር በደንብ አብራርቷል:: በፌደራልጉዳዮች ሚኒስተር ለኮሚቴዎቹ ተገብቶላቸዉ የነበረዉን ቃል በሙሉ ያልፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል:: ከዚህም መካከል የስም ማጥፉቱ እንደሚቆም እና ማንኛዉም ሰዉ አይታሰርም ብሎ ቃል የገባ ቢሆንም ከዛ ቡሀላ ግን በጣም ብዙ ሰዎች መታሰራቸዉን እና የኮሚቴዎቹን ስም ማጥፉት መቀጠሉንም ገልፀዎል::በየካቲት 26ቱም ስብሰባ ሚዲያዎች የቀረፁትን ለህዝብ ከመቅረቡ በፊት ኮሚቴዎቹ እንደሚያዩት ቃል ቢገባላቸዉም ስብሰባዉ ሳያልቅ ኮሚቴዎቹ ለመግሪብ ሰላት በወጡበት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ዴታአቶ ሙሉጌታ ለሚዲያ ዉጤቱን ማስተላፉቸዉን ጨምረዉ ገልፀዋል:: በሁለተኛዉ ፕሮግራም ህዝበ ሙስሊሙ በጉጉት ሲጠብቀዉ የነበረዉ የየካቲት ሀያስድስቱን የመንግስት ምላሽን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ሰብሳቢ በኡስታዝ አቡበከር አህመድ ቀርቧል:: በሪፓርቱም መሰረት መንግስት ሰጠሁት ያለዉ ምላሽ ሙስሊሙ የጠየቃቸዉን ጥያቄዏች በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም ሲዞዞር እንደነበር ገልፀዎል:: በመንግስት የተሰጠዉ ምላሽ እላዩ ሲታይ መልስ የሚመስል ነገር ግን ምላሹ ብዥታ ያለበት እና ጥልቅ ማብራሪያ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዎል:: ምላሾቹ ግልፅ ባለመሆናቸዉ እንዲብራሩ ቢጠየቁም እንዳልተብራራላቸዉ ገልፀዎል:: በመንግስት ምላሽ መሠረት የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ በተቻለ መጠን በፍጥነት በገለልተኛ ወገን ይካሄዳል የሚል የተዳፈነ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አህባሽን በተመለከተ አህባሽ አዲስ ሳይሆን የቀድሞዉን እስልምና የሚያስተምር ነዉ:: በማንም ሰዉ ላይ ጫናም ሆነ ግዳጅ አላደረገም ስለዚህ አህባሽ ይቀጥላል ማለታቸዉን እና አወልያ አክራሪዏችን ሲፈለፍል የኖረ ተቖም ስለነበር መጅሊስ ተረክቦት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱቀጥሎ ሳላ ለህዝብ ይሰጥ ብሎ ማለቱ ተገቢአይደለም በመሆኑም በመጅሊስ ስር እንዳለይቀጥላል በማለት መንግስት ምላሹን የሰጠመሆኑን ገልፀዎል:: በዉይይቱ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ዉይይቱን ወደሌላ አቅጣጫ ለመዉሰድ ጥረት ሲያደርጉእንደነበር ጨምረዉ ገልፀዎል:: በዉይይቱ መጨረሻ ላይም ኮሚቴዎቹ መንግስት የሰጠዉምላሽ ለጥያቄዎቻችን የተሟላ ምላሽ ባለመሆኑ ለሚቀጥለዉ የመንግስት አካል እስከ ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ድረስ ጥያቄዎቹን እንደሚያቀርቡ በመግለፅ ስብሰባዉን መጨረሳቸዉን እስታዉቀዋል:: ኡስታዝ አቡበከር ሪፓርቱን ከጨረሰ ቡሀላኡስታዝ በድሩ ሁሴን ለፌደራል ጉዳዮች የገባዉን የኮሚቴዉን አቖም የሚገልፅ ደብዳቤ ለህዝቡ አንብበዋል:: በመጨረሻም የመጅሊስን ታሪክ እና ግድፈቶች በማስመልከት ሀሰን አሊ ፕሮግራም አቅርቧል:: የዛሬዉ ተአምራዊ የአወልያ ሰልፍ ዱአ በማድረግ ተጠናቖል:: ሁለተኛዉየትግል ምእራፍ መጀመሩም የዛሬዉ የአወልያ ዉሎ አሳይቶናል:: Read more
  • Action Plan to Combat the Corrupt Majlis and its Ahbashism Campaign

    (by Anti-Ahbash Group) Foreword This action plan is presented for discussion. It focuses mainly on the activities we should carry out in the ongoing struggle. We need members to discuss it thoroughly. The Amharic Version of this Action plan will be presented as well Insha Allah. May Allah Help us. I. Activities we do within the Muslim Ummah 1. We continue the awareness creating on the deviances and heretical teachings of Ahbash and the illegitimacy of the Majlis. We should increase the awareness creating activities through out the whole of the country by expanding its modes which include a) Internet: -expand the magnitude from the facebook groups to other social networking sites, bloggers, websites, etc… b) Publication and distribution of pamphlets and brochures (but with considerable care) c) Publication and distribution of books d) Using the Muslims newspapers and magazines e) Discussions in “masjid” and our neighborhood jama’a f) Others…. 2. Bringing more and more distinguished personalities to the struggle. We should reach distinguished personalities of the following sorts a) Well respected Ulama, writers and Da’is b) Well-known persons in the business community c) Well-known Muslim activists and humanitarians d) Other well-known Ethiopian Muslims (for example, Muslim athletes, footballers, journalists, travelers etc… ) 3. Reaching all Muslims Ethiopian individuals and groups in Diaspora and making them to play their role in our cause. 4. Bringing all active da’wa groups and study circles, under the same objective 5. Reaching the traditional Muslim social institutions (called “idir” in Amharic) and making them to have their part (if it is possible). II. The Aweliya Demonstration We will continue the non-violent massive rally at Aweliya up to the final end (Unless we are forced to stop because of the restraints which might happened) III. Appealing to all concerned bodies of the Federal and Local government 1. Appealing to the prime minister of the federal government of Ethiopia. a) Writing a formal letter to the prime minister b) Collecting petitions and submitting to the prime minister office c) Collecting online petitions and submitting to the prime minister office 2. Notifying the nine regional governments and the two city councils of the truths of our problems. 3. Appealing to the representatives of opposition parties in the parliament so as to raise our question in the parliament IV. Exposing our case to other Ethiopians and the media. 1. Exposing our case to non-Muslim Ethiopians and telling them the reality of our case 2. Exposing our case to the local private media 3. Exposing our case to the international media (press, Radio, TV, Websites etc…) V. Exposing our case to internationally renowned Muslim Institutions 1. Appealing to influential Muslim educational institutions like Al-Azhar University, Medina Islamic University etc… 2. Appealing Institutions like World Union of Muslim Ulama VI. Exposing our case to human rights groups, internationally renowned Muslim Institutions and directly concerned foreign governments 1. Exposing our case to domestic human rights organizations such as a) The Ethiopian Human Rights commission (a government organization) b) The Ethiopian Human Rights council (non-governmental) 2. Exposing our case to international human rights organizations such as Amnesty international, human rights watch etc.. 3. Appealing to the State Department of the United States (because many people speculated that it was the wrong assumptions made by the USA and the policy advice it gave to the government of Ethiopia that allowed “Al-Ahbash” to have a power on the Council of Islamic Affairs. The cables we read on wikileaks site support this hypothesis). Conditions of the Struggle 1. We seek to achieve our demand through legal and non-violent ways. 2. We rely on ourselves. We allow primarily the Ethiopian and Ethiopian-born Muslims to have direct participation in the struggle. But we will accept the assistants of other nationals, governments and organizations according to the legal grounds of Ethiopia. 3. In any case, we must show the concerned bodies that we are reflecting the feeling of the majority (not the minority as “Ahbash” and Majlis say). 4. We will show all parties that the Ethiopian Muslims are non extremist, non-violent good citizens who were brought up through excellent Islamic ethics. May Allah Help Us. Amiin!! Read more
  • ሙስሊሙ ምን ታስቦለት ይሆን?

    ሙስሊሙ ምን ታስቦለት ይሆን? በትላንትናው ዕለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተወካዮቻችንን ከሰዓት በኋላ ከማናገሩ በፊት ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ከመጅሊስ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጎ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጦላቸውና ለኮሚቴው የሚሰጠውን መልስም ጭምር አሳውቋቸው እንደነበር ታወቀ፡፡ በሌላ በኩል አቶ ጸጋዬ ቅዳሜ ቀን አቶ አህመዲን ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን መንግስት የሰጣቸውን የቤት ስራ ባግባቡ እንዳልተወጡ ወቀሳ ተሰንዝሮባቸው ለወደፊት እንዲያስተካክሉና መንግስት በአቶ አህመዲን ላይ ከፍተኛ መተማመን እንዳለው ማብራራቱን ከመጅሊስ አካባቢ የተገኙ ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ተጠራርገን መውጣታችን ነው ብለው ስጋት ላይ የነበሩት መጅሊሶች ከመንግስት መተማመኛ ስለተሠጣቸው በደስታ መጅሊስ ጊቢ ውስጥ አርደው መደገሳቸውን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ እንደዚሁም የመስጂድ ኢማሞቻችን በግድ ስለ አህባሽ እንዲያስተምሩ የተደረገባቸው ጫና አላንስ ብሎ አሁን ደግሞ ሙስሊሙ ጥያቄው ስለተመለሰ ለህዝቡ የእንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልእክት በግድ እንዲያስተላልፉ እየታሰበ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም የአህባሽ ስልጠና በሰፊው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ለየካቲት ወር ብቻ 12 ሚሊየን ብር በጀት ተይዞ በአምቦ በውቅሮ በሻሸመኔና ሌሎችም ቦታዎች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል የመጪውን ጁሙዓ የአወሊያ ፕሮግራም ለማሰናከል ከሰላት በፊት መድረክ መሪዎችንና የተወሰኑ የኮሚቴው አባላትን ለተወሰነ ሰዓት አግቶ ለመልቀቅ እቅድ የተያዘ በመሆኑ ሁላችንም በንቃት በመከታተል ይህ እኩይ ዐላማ እንዳይሳካ ጥረት ማድረግና ነቅተን መጠበቅ አለብን፡፡ Read more

Latest Articles

Most Popular